29/03/2023
ጉዞ ወደ ዲማ ቅዱስ ጊዮርጊስ የሴቶች አብነት(የቆሎ) ትምህርት ቤቶች
የቆሎ ተማሪዎች መርጃ ህብረት ከ ሰከላ ሃይኪንግ ጋር በመተባበር የተዘጋጀ
ለመመዝገብ
+251 921147545
+251 912458538
+251 910804563
ዲማ ቅዱስ ጊዮርጊስ
ዲማ ቅዱስ ጊዮርጊስ ገዳም የሚገኘዉ በምስራቅ ጎጃም ዞን በእነማይ ወረዳ ዉስጥ ሲሆን ከብቸና ወደ ደብረ ወርቅ በሚወስደዉ መንገድ 16 ኪሎ ሜትር በመጓዝ ጠልማ ቀበሌ ላይ ሲደርሱ በስተምስራቅ አቅጣጫ ተገንጥለው 12 ኪሎ ሜትር ከተጓዙ በኋላ ያገኙታል፡፡
የገዳሙ መጠሪያ ስያሜ ደብረ ድማህ ሲኾን ትርጓሜዉም ራስ ማለት ነዉ፡፡ይህም በጊዜዉ የጎጃም ማዕከል የሚለዉን ለማመላክት እነደነበር አባቶች ይገልጻሉ፡፡ሌላዉ ትርጓሜ ደግሞ ዲማ ማለት ደመወ ከሚለዉ የግዕዝ ቃል የተገኘ ሲኾን ደመወ ማለት ደም /ቀይ/ ማለት ነዉ፡፡ይህ ስያሜም የተሰጠበት ምክንያት ቀደም በገዳሙ አካባቢ ትልልቅ ቀይ ዛፎች ስለነበሩ ከዚያ ጋር ተያይዞ የተሰጠ ስያሜ እንደኾነ ይገለጻል፡፡
ዲማ ጊዮርጊስ የተመሰረተው በ1297 ዓ.ም የቀድሞ ስማቸው አባ በኪሞስ በኋላ ግን ተከስተ ብርሃን በተባሉ አባት አማካኝነት በአጼ ዐምደ ጽዮን ዘመነ መንግሥት የተመሠረተ ሲኾን ከ900 ዓመት በላይ ያስቆጠረ ታላቅ ገዳም ነው።
ዲማ ቅዱስ ጊዮርጊስ እና የአብነት(የቆሎ) ትምህርት ቤቶች
ዲማ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ከጥንት እስከ አሁን ድረስ ትምህርቶችን እየሰጡ ከሚገኙ ጥንታዉያን አብያተ ክርስቲያኖች ውስጥ ከቀዳሚዎች የሚመደብ ነው። በቤተክርስቲያኑ አራቱም ጉባኤያት እየተሰጠ ሲሆን ንበባ ቤት፣ ዜማ ቤት፣ ቅዳሴ ቤት፣ አቋቋም፣ ቅኔ ቤት፣ መጻሕፍት ቤት (ሐዲስ፣ ብሉይ፣ ሊቃውንትና መነኮሳት) የሚሠጥበት ነው።ብዛት ያላቸው መምህራንና አሁንም እያፈራ የሚገኝ ነው።
የሴቶች የአብነት (የቆሎ) ትምህርት ቤት
ዲማ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን በእማሆይ ኅሪት ሴቶችን ብቻ እያስተማረ የሚገኝ ትምሀርት ቤት ነው። በዚህ ትምህርት ቤት ንባብ ቅኔና መጻሕፍትን መማር ለሚፈልጉ ሴቶች በማስተማር የሚገኝ ትምርት ቤት ነው። ትምህርት ቤቱ በአሁን ሰዓት ሃምሳ ሴቶች ተማሪዎች እየተማሩ የሚገኝ ነው።