Ethio travel news

Ethio travel news Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Ethio travel news, Travel Service, Addis Ababa.

28/09/2020

የሀገር ውስጥ ቱሪዝምን እንዴት ማስፋፋት ይቻላል?
========================
የሀገር ውስጥ ቱሪዝም የአለም አቀፉ ቱሪዝም ችግር በሚያጋጥመው ጊዜ እንደ ሾክ አቭዞርቨር የሚያገለግል ብቻ ሳይሆን በሁሉም መስክ ምትክ የማይገኝለት አማራጭ ነው ።
አሁን የአገር ውስጥ ቱሪዝም እንዴት ለማሳደግ እንደሚቻል ሀሳብ ለመሰንዘር ስለመጣሁ ስለጥቅሞቹ በሌላ ጊዜ እናውራለን።
ትላንት ቀን ላይ የሄኖክን ማታ ላይ የአስቻለውን ዝግጅቶች ለተመለከተ እንዲሁም የባላገሩ ተሾመን መነቃቃት ለተመለከተ እና ዮድ አቢሲኒያን የባህል ምግብ አዳራሽን ትጋት ላየ የሀገራችን ቱሪዝም እምቅ ሀብት እንዴት ጥቅም ላይ ሊውል እንደሚችል ያስባል ።,ለዚህም
1.የሀገር ውስጥ የቱሪዝም የፕሮሞሽን ስራዎች አጠናክሮ መቀጠል።
በዚህ ዘርፍ በቴሌቪዥን በሬድዮ እና በህትመት የሀገራችን የቱሪዝም ሀብቶችን ለሚያስተዋውቁ ግለሰቦችና ድርጅቶች ድጋፍ ማድረግ።
በዚህ በኩል የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር መስሪያ ቤት እና ቱሪዝም ኢትዮጵያ በምሽቱ ፕሮግራሞች የወሰዱት ተነሳሽነት የሚደነቅ ነው። ሆኖም እነዚህ መስሪያ ቤቶች ዘላቂ ድጋፍ መስጠት የሚያስችል በቂ አቅም ስለሌላቸው እንዲሁም አደረጃጀታቸው ሩቅ ስለማያደርሳቸው በተለየ መንገድ የፕሮሞሽኑ ስራ እንዲቀጥል የቱሪዝም ፕሮሞሽን ፈንድ በቦርድ ተደራጅቶ መንግስትና ግለሰቦች እንዲሁም ድርጅቶች ወደዚህ ቋት ፈሰስ በማድረግ ቦርዱም በቀረበለት ፕሮፖዛል መሰረት ፈንዱን ያከፋፍላል ።በዚህም በፊልም ስራ: በሙዚየም ጥበቃ :በሚዲያ ስራ በፊልም ስራ በአዳራሽ ኪራይ ስራ ላይ ያሉ ሌሎችም ተጠቃሚ ይሆናሉ።
መንግስት በፍጥነት ሊተግብረው የሚችል በመሆኑ ወደ ተግባር መግባት ይቻላል። የአለም ባንክም ይህን አካሄድ ይቀበላል ።
2.Incentive Travel የማትግያ ጉዞ
በተለያዪ ድርጅቶች እና አቅም ባላቸው ተቋማት አማካኝነት የሚዘጋጁ ጉዞዎች ሲሆኑ በተለይም አመታዊ የጉዞ ፕሮግራሞች በመደገፍ ይከናወናል።
ለምሳሌ የዳሽን ባንክ አመታዊ በአል ሲያዘጋጅ 500 ለሚሆኑ ሰራተኞች ላሊበላ ደርሶ መልስ ፕሮግራም ቢያዘጋጅ ለሠራተኛው ማትጊያና ማነቃቂያ ይሆናል ። ላሊበላ ብቻ ሳትሆን በሰንሰለቱ ውስጥ ያሉ ይጠቀማሉ።
ከዚህም በላይ ሰራተኛው ቤተሰቡን ጭምር በማስጎብኘት ለልጆችም ጭምር ይተላለፋል ።
ሰራተኛውም ለጉዞ ቁጠባ ማድረግ ይጀምራል ።
ኢሰማኮም ለሠራተኞች በየአመቱ የደመወዝ ጭማሪ ጥያቄ በተጨማሪ የጉዞ ድጋፍ መጠየቅ ልማዱ ያደርጋል ።በሬ አርዶ ከመብላት ባለፈ የማትጊያ ጉዞ ያስፈልጋል ።
3.በየዩኒቨርሲቲው ያሉ የተማሪ መኝታ ቤቶች እና የአንደኛ ደረጃን ጨምሮ ያሉ ትምህርት ቤቶች ለሀገር ውስጥ ጎብኚዎች ክፍት ማድረግ አለባቸው ። በቁጥር በጾታ በእድሜና በገቢ አንጻር ለተከፋፈሉ ለተለያዩ የሀገር ውስጥ ጎብኚዎች እንዲያገለግሉ መስራት ያስፈልጋል።
ፍራሽና ድስት ማከራየት ገቢ ነው።
4.የመጓጓዣ አውቶቡሶችን ከቀረጥ ነጻ እንዲገቡ የማበረታቻ ሥራ አጠናክሮ መቀጠል። በየአመቱ ዘመናዊ አውቶቡሶች ማስገባት ግዴታ የማድረግ ስራ አለምአቀፍ ማህበረሰብ እየጠየቀ ነው። የ2018 ሞዴሎች የኬኒያ ቱሪዝም መወዳደሪያ ሆኖአል።
5.የጉዞ ነርሶችን ማዘጋጀት
እነዚህ ነርሶች በተለየ ሁኔታ የሰለጠኑ ለተማሪዎች እና ለቡድን ተጓዦች የሚሆኑ ለድንገተኛ ጊዜ የሚሆኑ ናቸው።
6.የቱሪዝም ፖሊሶች አስፈላጊነት አጠያያቂ ባይሆንም ለማንኛውም መሰልጠን አለባቸው ።
በግብጽ ጉብኝት ሳደርግ ወጪውን የሸፈንኩት ከኪሴ ነው ።
7.ሆቴሎች በቡድን ለሚመጡ ኢትዮያውያን ጎብኚዎች ዝግጅት ማድረግ አለባቸው ።ይቅርታ አድርጉልኝና እኛ ኢትዮጵያውያን በቡድን ለመጓዝ የሚያስፈልገው ዲስፒሊን የለንም ።ብዙ መማር ያስፈልገናል።ለቡድኑ ተጓዥ ሲባል የግል ፍላጎትን መግታት ያስፈልጋል። ለምሳሌ ሰአት ማክበር መነጠል እና ሌላ ቦታ መሄዴ እንዲሁም ያለልክ መሸመት እና ሌሎችም።
8.በሀይማኖት ምክንያት የሚደረጉ ጉዞዎች በየደረሱበት ለአካባቢው ማህበረሰብ ድጋፍ የሚያደርጉ እንጂ ችግር /ሸክም መሆን የለባቸውም።አክሱም የሚጓዙ ምግብ ከአክሱም ከተማ አቅራቢዎች መግዛት አለባቸው። አክሱም ትርፏ የፕላስቲክና ሌሎቾ ቆሻሻ ሳይሆን ገንዘብ መሆን አለበት። በድንኳን ማደር ሀይማኖታዊ ግዴታ አይደለም። ድንኳን ጊዚያዊ ማረፊያ እንጂ ማደሪያ ማብሰያ እና ሌላም መሆን የለበትም። የማህበር የጉዞ ፕሮግራሞች የተሻለ እንዲሰሩ መታገዝ አለባቸው ።በዘፈቀደ ተጠያቂነት በሌለበት ሁኔታ የሚደረገው ጉዞ ወደ መስመር እንዲገቡ ያስፈልጋል ።መኪኖቻቸው የማይመጥኑ ተጓዦች ምግብ ሳያገኙ የሚሄዱበት ወይም ጥራት የሌለው ምግብ የሚያቀርቡበት ሁኔታ መሻሻል አለበት። ቦታውን ከማሳለም ባለፈ ታሪክ ነጋሪ ባህል አስተማሪ መሆን ያስፈልጋቸዋል ። ብቻ ህግ ያግዳቸው። ግርግሩን መስቀል አደባባይ ጸሀይ ሳይወጣ ሄዶ ማየት ነው። ቤተክርስቲያንም አታውቃቸውም ። ጥሩ ጅምሮች እንዳሉ አውቃለሁ።ሁሉም ግብር የማይከፍሉ መሆናቸውንስ? መንግስት ሆይ ሰምተሀል።
6.ገጠሩን በቱሪዝም እናልማ የሚለው መሪ ቃል ለኔ አሻሚ ትርጉም ቢሰጠኝም ለገጠሩ የሚሰራ የልማት ስራ በቱሪዝም መደገፉን እመርጣለሁ።
ጨምሩበት
ሰላም
መልካም የቱሪዝም ቀን
አስራት በጋሻው
ከኤርፖርት ሲቲ
ቦሌ ቡልቡላ

29/08/2020

Statement

We would like to inform our esteemed customers to/ from Shanghai that our flight from Addis Ababa to Shanghai will be suspended for a week from August 31 due to the China Civil Aviation Authority’s new rule on travel to China. However, We are discussing with the Chinese authorities to restore the flights.
We invite our esteemed passengers to visit our website for travel updates and flight restrictions:

Delivery
13/02/2020

Delivery

Ethiopian coffee
14/12/2019

Ethiopian coffee

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethio travel news posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category