Tour in Ethiopia ቱር ኢትዮጵያ

Tour in Ethiopia ቱር ኢትዮጵያ This page promotes and offers History ,Culture, Religion, Architecture, Wildlife, Scenic and other Interesting things in . Love and peace �
(3)

We consult, arrange and conduct your next trip! Contact us for your domestic travel arrangements.

HAPPY  We are back dear followers. Soon with the latest updates.  Stay Tuned!
21/04/2024

HAPPY
We are back dear followers. Soon with the latest updates. Stay Tuned!

02/03/2022
14/01/2022

Largest lip plate: 19.5 cm (7.7 in) by Ataye Eligidagne, as measured in Ethiopia in 2014.

📷 Abraham Joffe

A member of the Surma tribe, Ataye previously held this record at 15 cm, but she exceeded it by 4.5 cm. She was photographed by Australian film-maker Abraham Joffe - this photo features in the book.

Normally worn for decoration, for the Surma people of southern Ethiopia the significance of wearing lip plates is a financial one. The process of inserting these plates (made by the women themselves from local clay, which are then coloured with ochre and charcoal and fire-baked) begins approximately a year before marriage and the final size indicates the number of cattle required by the girl's family from her future husband for her hand. For example, a plate measuring 15 cm (6 in) in diameter - the previous record holder - would require a payment of 50 cattle.

    ❤ⒽⒶⓇⒺⓇⒺⓉⒽⒾⓄⓅⒾⒶ❤የ21 አመቱ ምዕራባዊ ወደ ተቀደሰችዉ  የምስራቋ ገነት ለመምጣት በባህር ላይ ካደረገዉ ጉዞ በተጨማሪ 20 ቀናትን በፈረስ መጓዝ ነበረበት። ምንም አላቅማማም፤ አ...
30/12/2021




❤ⒽⒶⓇⒺⓇⒺⓉⒽⒾⓄⓅⒾⒶ❤

የ21 አመቱ ምዕራባዊ ወደ ተቀደሰችዉ የምስራቋ ገነት ለመምጣት በባህር ላይ ካደረገዉ ጉዞ በተጨማሪ 20 ቀናትን በፈረስ መጓዝ ነበረበት። ምንም አላቅማማም፤ አደረገው ፤ጨ እንደደረሰም በበጎነት እና በፍቅር ዝናብ ሀረር ድካሙን አራገፋ ተቀበለችዉ ። እንግዳ ተቀባይነታቸዉ ፣ ፈገግታቸዉና እንክብካቤያቸዉ አስደነቀዉ። እዚህ የእኔ ብቻ የሚባል ነገር እንሌለ ተረዳ ። እንኳን የሰዉ ልጅን ጅብን ያክል ክፉ አዉሬ (ጅብ እንኳን ሰዉን የራሱን ልጅ እንደማያምን ልብ ይሏል) አልምደዉ አብረዉ ሲኖሩ በዐይኑ በብረቱ ተመለከተ። ተረጋግቶ ዙሪያውን ሲቃኝ ከእርሱ ዉጭ ሌሎች ነጣ ያለ የቆዳ ቀለም ያላቸዉ አርመኖች፣ አረቦች፣ ህንዶች፣ ግሪኮች እና ሌሎች የዉጭ አገር ዜጎች -------- ሲያሻቸዉ አረብኛ ፣ ኦሮምኛ ፣ አማርኛና ሀደሬኛ እየቀላቀሉ በፈገግታ ሲያወሩና ሲገበያዪ ተመለከተ። የእስልምና የክርስትና እና ካቶሊክ አማኞችን በቅጥሩ ዉስጥ በመቻቻል ሲኖሩ አስተዋለ:: ወዲያውም አለ ለራሱ ለእኔ ትክከለኛዉ ቦታ ይሄ ነው (c'est le bon endroit pour moi) ። እስከለተ ሞቴ ላልተውሽ ላትተዊኝ ሲል ቃል ተገባባ - ታዋቂዉ ገጣሚ ጀን ኒኮላስ አርተር ራምቦ (Arthur Rambud)- ከዉቧ ከሀረር ኢምሬት ጋር !!

አርተር ወትሮም ገራገር እና ቀና ነበርና እንደ አጋጣሚ ደ'ሞ ሀረር ነዉ እና የመጣዉ ለመግባባት አፍታም አልወሰደበትም ። አንድ ከጡብ የተሰራች አነስተኛ ቤት ገዝቶ ቡና እና አጣን ወደ ወጭ አገር በመላክ ንግድ ተሰማራ ። ታዲያ ወደ ሀገር ዉስጥም ነፍጥ (riffle ) በማስገባት ይሸጥ ነበር። በጥቂት ጊዜም ባለጸጋ በመሆን አሁን "ራምቦ ሀዉስ" ተብሎ የሚጠራውን ያማረ ፎቅ ከአንድ ህንዳዊ ገዛ ።

አርተር በየጊዜው ለቤተሰቦቹ በሚጽፋቸው ደብዳቤዎች ስለ ሀረር ህዝቦች ደግነት ፣እንግዳ ተቀባይነት ፣ ሰለ ፀሀያማዉ የአየር ሁኔታ ምቹነት ፣ ልዪ ባህል ፣በግንብ ስለታጠሩት መንደሮች ፣ የተሳለጠች የንግድ መናሀሪያ መሆኗን እና ስለ ተለያዪ ነገሮች ይጽፍላቸዉ እንደነበር የቀድሞ አሰሪዉና ዘመዱ አልፍሬድ ባድሬይ ይናገራል ።

ጀን ኒኮላስ አርተር ራምቦ በጥቅምት 14 ቀን 1854 እኤአ የተወለደው ቻርሊቬ -ሜዘሪ ፤ፈረንሳይ ሲሆን አባቱ ካፒቴን ራምቦ (ወታደር ) ፤ እናቱ ወ/ሮ ሜሪ ካትሪን ይባላሉ ። በልጁነቱ ጎበዝ ተማሪ የነበረና ብዙ ሽልማቶችን ከት/ቤት የሚሰበሰብ ትጉህ እና ጎበዝ ተማሪ ነበር። በለጋ እድሜው ታዋቂ የሆነበትን "Illumination" ጨምሮ ከ7 በላይ የግጥም መጽሀፍትን አሳትሟል። ሪያሊዝም የተባለውን የጽሑፍ ዘዉግ ይከተልም ነበር።

የኮሌጅ ትምህርቱን በማቋረጥ በፍራንኮ- ፐርሽያ ጦርነት አገሩን በወታደርነት አገልግሏል። የትዳር ህይዎቱ ብዙም ግልጽ ያልሆነዉ አርተር ለጥቂት ጊዜ በጋብቻ የቆየና ኢሳቤላ የተባለች ልጅ ቢወልድም ልደቷን እንኳን ሳያከብር ከአገር እንደወጣ ይነገራል። ሀረር እያለ ለልጁ እና ለሚስቱ በርካታ የግጥም ደብዳቤ ቢጽፍላቸዉም ባልታወቀ ምክንያት ወይም ቤተሰቦቹን ጥሎ በመሰደዱ ጓደኞቹ ደብዳቤዎቹን አያደርሱለትም ይባል ነበር ።

በሀረር ቆይታው" A Season in Hell" የተባለ የግጥም መጽሐፍ ጽፏል። በተለያዬ አህጉሮች እየተዘዋወረ ነገዷል። ወደ ፈረንሳይ ግን የሄደው በህይወቱ አንዴ ለዚያዉም ለቀብሩ ብቻ ነበር ። አርተር የደረሰበት የእግር ህመም ወደ ካንሰር በመቀየሩ ወደ ትዉልድ አገሩ ፈረንሳይ ለተሻለ ህክምና ቢሄድም ከዉብ የሀረር ትዝታዎቹ ጋር በህዳር 10 ቀን 1891 እኤአ እስከ ወዲያኛው አሸልቧል ። በሞቱ የመጨረሻ ደቂቃዎች "ወደ ሀረር እመለሳለሁ....... ፤ ቃልኪዳኔን አልረሳም፤ የምስራቋ ኮኮብ ት...ናፍቂኛለሽ........" በሚያሳዝኑ ቃላት የተናገራቸው ነበሩ ።

በአሁኑ ወቅት አርተር ራምቦ ይኖርበት የነበረው ከወይራ እና ጥድ ጣዉላ የተሰራ ፤ በቀለም የሽበረቁ የመስታዉት መስኮቶቹ ያሉት ይሄዉ ልዪ የኪነ ህንጻ ጥበብ የተንጸባረቀበት ቤት ወደ ሙዚየምነት የተቀየረ ሲሆን በዉስጡም የአርተርን ህይወት የሚዘክሩ ጽሁፎች እና ራሱ አርተር ያነሳቸው ፎቶግራፎች ይገኛሉ ። በርካታ ክፍሎች ሲኖሩት ሶስቱ ክፍሎች ወደ እንግዳ መቀበያ (guest house) ተቀይሮ አገልግሎት አየሰጠ ይገኛል ::

# #

እንደተለመደው .......ለሌሎች ያካፍሉ። እናመሰግናለን !!

The 17thC magnificent castle of  Challenge us  Name which of the 6 castles (pic) reside in the royal compound?
23/12/2021

The 17thC magnificent castle of
Challenge us
Name which of the 6 castles (pic) reside in the royal compound?

Visit  !via Afar Bureau of Culture and Tourism
20/12/2021

Visit !
via Afar Bureau of Culture and Tourism

የገጻችን ቤተሰቦች ክብረት ይስጥልን 5ሺህ አብረን ብዙ እንጓዛለን !Tnx for following us!
23/10/2021

የገጻችን ቤተሰቦች ክብረት ይስጥልን
5ሺህ
አብረን ብዙ እንጓዛለን !
Tnx for following us!



  ETHIOPIAVia Afar Bureau of Culture and Tourism
09/10/2021


ETHIOPIA
Via Afar Bureau of Culture and Tourism

Ambassador   (Former Canada Ambassador) has appointed as the new Ethiopian Tourism Minister.We wish you a very successfu...
06/10/2021

Ambassador (Former Canada Ambassador) has appointed as the new Ethiopian Tourism Minister.
We wish you a very successful period and we hope TOURISM will become a big economic contributor to the country.
Good Luck!



Abiy Ahmed Ali (Phd) named the new PM of Ethiopia 🇪🇹 . The Grand ceremony will take place on the country's biggest squar...
04/10/2021

Abiy Ahmed Ali (Phd) named the new PM of Ethiopia 🇪🇹 . The Grand ceremony will take place on the country's biggest square, expected 500000 or more attendees to be a part.
CONGRATULATIONS!3🇪??



 - the Oromos Thanks Giving DayFestival of Love, Peace and UnityHappy Holiday!               #ኢሬቻ
01/10/2021

- the Oromos Thanks Giving Day
Festival of Love, Peace and Unity
Happy Holiday!


#ኢሬቻ

 (Aka  ,  ,   or   Birds)🐦🐦🐦🐦🐦🐦🐦🐦🐦🐦የመስቀል ወፍ ለወራት ጠፍቶ ቆይቶ አዲስ ዓመት ሲገባ በተለይ ደግሞመስከረም ሲጋመስ እንደሚከሰት በብዙዎች ዘንድ ይታመናል።በአባባልም አ...
30/09/2021


(Aka , , or Birds)
🐦🐦🐦🐦🐦🐦🐦🐦🐦🐦
የመስቀል ወፍ ለወራት ጠፍቶ ቆይቶ አዲስ ዓመት ሲገባ በተለይ ደግሞ
መስከረም ሲጋመስ እንደሚከሰት በብዙዎች ዘንድ ይታመናል።
በአባባልም አንድ ሰው ለረጅም ጊዜ ጠፍቶ ቆይቶ ድንገት ሲከሰት ' ምነው
የመስቀል ወፍ ሆንክ' ይባላል። ይህም ለረጅም ጊዜ ሳይታዩ ወይም ጠፍቶ ቆይቶ
መታየትን ለማመልከት ማህበረሰቡ የሚጠቀምበት አባባል ነው።
አእዋፋትን በቅርበት የሚያጠኑት አቶ ይልማ ደለለኝ ግን "እነዚህ የመስቀል ወፍ
ተብለው የሚታወቁት አእዋፋት እንደሚባሉት ለረጅም ጊዜ ተሰውረው ቆይተው
በመስቀል ሰሞን የሚከሰቱ ሳይሆኑ ዘወትር አብረውን የሚኖሩ ናቸው" ይላሉ።
እንደባለሙያው ከሆነ በኢትዮጵያ በመስቀል ወፍ ስም የሚታወቀው አንድ አይነት
ዝርያ ያለው ወፍ ብቻ ሳይሆን ቁጥራቸው ከአራት በላይ የሆኑ የተለያዩ ዝርያ
ያለቸው አእዋፋት እንደሆኑ ይናገራሉ።
ለዚህም እንደምሳሌ የሚጠቅሱት ቁራ በሚል የሚጠሩ አእዋፋት ቢኖሩም
በውስጣቸው የተለያዩ ዝርያዎች እንዳሉት ሁሉ የመስቀል ወፍ ውስጥም
የተለያዩ የወፍ አይነቶች መኖራቸውን ነው።
ከእነዚህ የመስቀል ወፎች መካከልም አዘውትረን የምናያቸው በቅርብ
የምናውቃቸው ትንንሽዬዎቹና ድንቢጥ ተብለው የሚታወቁት አእዋፋትም
በመስቀል ወፍነት ከሚጠሩት ውስጥ ይካተታሉ።
እንደየቋንቋውና እንደየአካባቢው እነዚህ ወፎች የየራሳቸው ስያሜና መጠሪያ
ሊኖራቸው እንደሚችል የሚጠቅሱት አቶ ይልማ የመስቀል ወፍ የሚለው ግን
በርካታ አይነት ወፎች በውስጡ አካትተዋል ይላሉ።
በእንግሊዝኛው እነዚህ አዕዋፋት ኢንዲጎ በርድስ፣ ዋይዳ፣ ቢሾፕ ወይም ዊዶ
በርድ ተብለው እንደሚታወቁ በእነዚህ ውስጥም የተለያዩ ዝርያዎች መኖራቸውን
ያስረዳሉ።
~ ወፎቹ የሚታዩበት ጊዜ ~
እነዚህ የመስቀል ወፍ ተብለው የሚጠሩት አእዋፋት በስፋት ታይተው በበርካቶች
ዓይን ውስጥ የሚገቡት የክረምቱ ወራት አብቅቶ የበጋው ወቅት በሚጀምርበት
ጊዜ ነው።
አእዋፋቱ በአብዛኛው ዘር በል በመሆናቸው በዚህ ወቅት ደግሞ የሚደርሱ
ሰብሎች በስፋት የሚገኙበትና ወፎቹም የሚራቡበት አመቺ ወቅት በመሆኑ
በስፋት እንደሚታዩ አቶ ይልማ ይናገራሉ።
እነዚህ አእዋፋት ባሕሪያቸው ከአንድ አካባቢ ወደሌላ አካባቢ ወቅቶችንና የአየር
ሁኔታዎችን እየተከተሉ የሚሰደዱ በመሆናቸው በሌሎች ሃገራት ውስጥም
ይገኛሉ።
አቶ ይልማ እንደሚሉት የተለያዩ አእዋፋት በተለያዩ ወቅቶች በተለይ ከሰሜናዊ
ንፍቀ ክበብ ወደ አፍሪካ የሚመጡ ሲሆን በሌላ ጊዜ ደግሞ ወደዚያው
የሚሄዱም አሉ።
ወደ ኢትዮጵያ ወቅቶችን ጠብቀው የተለያዩ ወፎች ከመካከለኛው ምሥራቅ፣
ከስካንዴኔቪያን ሃገራት፣ ከምስራቅ አውሮፓ ሃገራት እንዲሁም ከሩሲያ የሚመጡ
እንዳሉና እነዚህም በስደተኛ ወፍነት በባለሙያዎች እንደሚታወቁ ይገልጻሉ።
የመስቀል ወፍ ተብለው የሚታወቁት አብዛኞቹ ግን በኢትዮጵያ ውስጥና
በዙሪያዋ ባሉ ሃገራት ውስጥም እንደሚገኙ ይነገራል። ስለዚህ አእዋፋቱ
ከኢትዮጵያ ባሻገር በኬንያ፣ በኡጋንዳና በታንዛንያ ውስጥ እንደሚገኙ
ይጠቅሳሉ።
~ አብረውን ያሉ ግን እንግዶች ~
አቶ ይልማ እንደሚሉት በልምድ እንደምንለው የመስቀል ወፍ ለረጅም ጊዜ
ጠፍተው ቆይተው በመስቀል ወቅት የሚከሰቱ እንዳልሆኑና በዙሪያችን አብረውን
የሚኖሩ ናቸው።
አእዋፋቱ አዲስ የሚሆኑብን አብረውን በዙሪያችን በሚቆዩበት ጊዜ የሚኖራቸው
ገጽታ በመስከረም ወር ላይ በተፈጥሯዊ ሂደት ቀለማቸው ተለውጦ አይነ ግቡ
ስለሚሆኑ የዚያ ወቅት አዲስ ክስተት እንደሆኑ ስለሚታሰብ ነው።
"ለዚህም የአዕዋፋቱን ተፈጥሮ መረዳት ያስፈልጋል" የሚሉት አቶ ይልማ እነዚህ
ወፎች ላይ ይህ ተፈጥሯዊ ለውጥ የሚታየው በዋናነት በመስከረም ወር ላይ
የሚራቡበት ጊዜ በመሆኑ ነው። ይህ ደግሞ ከመስቀል በዓል ጋር ተቀራራቢ
በመሆኑ የተለየ ገጽታን ተላብሰው እንዲታዩ ያደርጋቸዋል።
~ የተፈጥሮ ሂደት ~
በመስከረም ወር ላይ እንስት አእዋፋቱ እንቁላል ለመጣል የሚዘጋጁበት በመሆኑ
ተባዕቱ ለእሱና ለተጣማሪው እንዲሁም ለሚፈለፈሉት አእዋፋት
የሚያስፈልገውን ምግብና መጠለያን በሚያገኝበት ቦታ ላይ አንድ የተወሰነ
አካባቢን ከልሎ ይይዛል።
የመራቢያ ጊዜ በመሆኑ ወንዱ ይህንን በሚያደርግበት ወቅት የላባው መጠን
ይረዝማል ቀለሙም ይቀየራል። ቀለሙ ደማቅና ውብ ስለሚሆን የሰዎችን አይን
በመሳብ እንደ አዲስ ወፍ ሊታይ ይችላል ይላሉ አቶ ይልማ።
ይህ ቀለምም ከሩቅ የሚታይ እንደሚሆን የሚናገሩት ባለሙያው በተለይ ፀሐይ
በሚያገኘው ጊዜ በማንጸባረቅ ትኩረት የመሳብ አቅም አለው።
በተጨማሪም ለውጡ የሚከሰተው በመራቢያ ጊዜ በመሆኑ እንስት ወፎችን
ለመሳብና ለማማለል ከመጥቀሙ በተጨማሪ በአንጸባራቂ ውበቱ በቀላሉ
ስለሚታይ፣ እንዲሁም በዚህ ላይ ዝማሬን ስለሚጨምር ሌሎች አእዋፋት
የእርሱን አካባቢ እንዲርቁ ያስችለዋል።
እንግዲህ ይህ የአእዋፋቱ ሥነ አካላዊ ለውጥ ነው በሌለው ጊዜ በአካባቢያችን
ይኖሩ የነበሩትን እነዚህን አእዋፋት ለረጅም ጊዜ ጠፍተው በመስቀል ወቅት ብቅ
ያሉ እንዲመስሉ ያደረጋቸው ይላሉ አእዋፋቱን በቅርበት የሚያጠኑት አቶ ይልማ
ደለለኝ።
ባለሙያው እንደሚሉት "በአካባቢያችን ያሉትን አእዋፋት በቅርበት የመከታተል
ልምድ ስለሌለንና ክረምቱ አልፎ መስከረም አጋማሽ ላይ አእዋፋቱ ላባቸው
በቀለማት አሸብርቆ በቀላሉ አይናችን ውስጥ ሲገቡ በዙሪያችን የነበሩት ወፎች
ሳይሆኑ ጊዜ እየጠበቁ ብቅ የሚሉ ይመስሉናል።"
ቀለማቸውና ዝማሬያቸው ከአዲስ ዓመትና ከመስከረም የፀሐይ ወቅት ጋር
ተዳምሮ ከሚፈጠረው መልካም ስሜት ጋር የሁሉንም ቀልብ ስለሚስቡ ሁሉም
ይመለከታቸዋል ሁሉም አዲስ ወፍ የመስቀል ወቅትን ጠብቆ እንደመጣ
ይታመናል።
የመስቀል ወፍ ብለን የምንጠራቸው አእዋፋት ከሌሎች ለየት የሚሉት ተባዕቶቹ
በጣም ደማቅ ቀለም ሲኖራቸው፣ ሴቷ ግን ቡኒ ወይም ወደ ግራጫ የሚያደላ
ቀለም ነው ያላት፤ በመራቢያ ወቅት ወንዱ ከበርካታ እንስት አእዋፋት ጋር
የመሆን ባሕሪ እንዳለውም አቶ ይልማ ይጠቅሳሉ።
ስለዚህ የአእዋፋት አጥኚ የሆኑት አቶ ይልማ ደለለኝ እንደሚሉት የመስቀል
ወፎች ለረጅም ጊዜ ሳይታዩ ቆይተው መስከረም ወር ላይ የሚከሰቱ ዓመታዊ
እንግዶች ሳይሆኑ አብረውን ቆይተው በተፈጥሮ ሂደት የላባቸው ቀለም የሚቀየር
ቤተኛ አእዋፋት ናቸው ማለት ነው።
ምንጭ፦ ቢቢሲ አማርኛ



30/09/2021

የኢትዮጵያ አየር መንገድ “SKYTRAX” በ2021ዓ.ም ባዘጋጀው ምርጥ የአለማችን አየር መንገዶች ውድድር በአራት ዘርፎች ሽልማቶችን ለመቀዳጀት በቅቷል። "በአፍሪካ ምርጥ አየር መንገድ" ዘርፍ ለተከታታይ አራት አመት ፣ "በአፍሪካ ምርጥ ቢዝነስ ክላስ" ዘርፍ ለተከታታይ ሶስት አመት፣ "በአፍሪካ ምርጥ ኢኮኖሚ ክላስ" ዘርፍ ለተከታታይ ሶስት አመት እና "በአፍሪካ ምርጥ የበረራ መስተንግዶ ሰራተኞች" ዘርፍ አንደኛ ለመሆን ችሏል።

አየር መንገዳችን በSKYTRAX ምርጥ የአለማችን 100 አየር መንገዶች ዝርዝር ውስጥም በ37 ኛ ደረጃ ለመቀመጥ የቻለ ሲሆን ውድድሩ በአለማችን ላይ የሚገኙ ከ350 የሚልቁ አየር መንገዶችን ያሳተፈ ነው።

https://www.worldairlineawards.com/award-winners-for-2021/

Dr  , the Minister of Ethiopian   , will lead the Addis abeba City Culture, Tourism and Art Office as announced on Today...
28/09/2021

Dr , the Minister of Ethiopian , will lead the Addis abeba City Culture, Tourism and Art Office as announced on Today's (28 Sep. ) City Hall council openings and welcoming of the newly elected council members.

While before her current position, Her Excellency Dr. Hirut Kassaw was served as an assistant professor in Bahirdar University and Led the office of the Amhara Tourism and Culture 2015-18. She was awarded by the Pacific Travel Writers Association (PATWA) at the International Tourism Bourse (ITB) in Berlin in 2020 and She was also awarded as "2019 Best Tourism Minister"which is from Street of Gold Foundation.

Good Luck!


growth

እንኳን አደረሳችሁ መልካም የመስቀል በአል ✞The finding of the True CrossUNESCO inscribed World Heritage #መስቀል  #ኢትዮጵያ  #ደመራ
26/09/2021

እንኳን አደረሳችሁ
መልካም የመስቀል በአል ✞
The finding of the True Cross
UNESCO inscribed World Heritage
#መስቀል #ኢትዮጵያ #ደመራ

Dr. Setor Abra Norgbe, won the Ghana Most Beautiful   2021 contest. She received the Most Eloquent Award. She wore beaut...
15/09/2021

Dr. Setor Abra Norgbe, won the Ghana Most Beautiful 2021 contest. She received the Most Eloquent Award. She wore beautiful Ethiopian costume and spoke amazing facts about Ethiopia🇪🇹

Warmest thoughts and best wishes for a Happy New Year. May peace, love, and prosperity follow you always!Visit Ethiopia ...
10/09/2021

Warmest thoughts and best wishes for a Happy New Year. May peace, love, and prosperity follow you always!
Visit Ethiopia and be seven years younger!*
Photo: Hilina Tafesse

09/09/2021
Today is pagume (ጳጉሜ) 1st. The 1st day of the 13th month. Nominated this day as ''Ethiopian Day'' የኢትዮጵያዊነት ቀንፍቅርና ሰላም ለ...
06/09/2021

Today is pagume (ጳጉሜ) 1st. The 1st day of the 13th month. Nominated this day as ''Ethiopian Day'' የኢትዮጵያዊነት ቀን
ፍቅርና ሰላም ለኢትዮጵያችን ! 💚💛❤

  በጦርነቱ ጉዳት የደረሰበት፤ በ320 ዓ.ም የተመሰረተ ጥንታዊ ገዳምጨጨሆ መድኃኒዓለም ሙሉ ሥሙ የበቅሎ አግድ ጨጨሆ መድኃኒዓለም ይባላል፡፡ ቤተ ክርስቲያኑ በቅሎ አግድ የተባለበት ምክንያት...
31/08/2021


በጦርነቱ ጉዳት የደረሰበት፤ በ320 ዓ.ም የተመሰረተ ጥንታዊ ገዳም

ጨጨሆ መድኃኒዓለም ሙሉ ሥሙ የበቅሎ አግድ ጨጨሆ መድኃኒዓለም ይባላል፡፡ ቤተ ክርስቲያኑ በቅሎ አግድ የተባለበት ምክንያት ከአጼ ቴዎድሮስ ታሪክ ጋር ይገናኛል፡፡

በአካባቢው በሚነገረው አፈ ታሪክ መሰረት አጼ ቴዎድሮስ ወርቂት ከምትባል የወሎ ገዥ ጋር ጦርነት ለመግጠም ሲገሰግሱ በጌምድርን ጨርሰው ወደ ወሎ ከመሻገራቸው በፊት ጨጨሆ ላይ ያርፋሉ፡፡ በዚያም እያሉ “ጨጨሆ መድኃኒዓለም ስለት ሰሚ ነው፤ ሱባዔ ገብተው ፀሎት ቢያደርጉና ተስለው ቢሄዱ ድል የርዕስዎ ይሆናል” ይባላሉ፡፡ አጼውም “መኑ ከማከ ዘንበሌከ/ሁሉ በደጅህ . . . . ቅሩብ እግዚአብሔር ለየዋሃነ ልብ/ እግዚአብሔር ለልበ ቅኖች ቅርብ ነው፤ ይሰማል” በማለት ፀሎት አደረሱ፤ ድል አድርገው ከተመለሱም በቅሏቸውን ለጨጨሆ መድኃኒዓለም ለመስጠት ተሳሉ፡፡

ወሎ ተሻግረውም ድል አደረጉ፡፡ ከድል በኋላም ወደ ጎንደር ሲመለሱ ጨጨሆ ላይ ወርደው ወደ ጦርነት ሲሄዱ ድል ከቀናኝ በቅሎየን እሰጣለሁ ብለው መሳላቸውን አስታወሱ፡፡ በስለታቸው መሰረት በቅሏቸውን ለቤተ ክርስቲያኑ መስጠት አልፈለጉም፡፡ በምትኩም የበቅሎዋን ዋጋ በሽማግሌ አስገምተው ለጨጨሆ መድኃኒዓለም በማስገባት ወደ ጎንደር ጉዞ ለማድረግ ተነሱ፡፡ በዚህ ጊዜ የአጼ ቴዎድሮስ በቅሎ ቤተ ክርስቲያኑ አፀድ ገብታ አልወጣም ትላለች፡፡ ብዙ ቢጣር በቅሎዋ ግቢውን አለቅ አለች፡፡ የአገር ሽማግሌዎችም ንጉሡ ስለታቸውን በገንዘብ ለውጠው ቢከፍሉም መድኃኒዓለም በቅሎዋን አግዶ አስቀራት በማለት ከዚያን ዘመን ጀምሮ ቤተ ክርስቲያኑ በቅሎ አግድ መድኃኒዓለም ተብሎ እንዲጠራ ሆነ፡፡

የበርካታ ቅርሶች ባለቤት የሆነው ጨጨሆ መድኃኒዓለም በደቡብ ጎንደር አስተዳደር ዞን ላይ ጋይንት ወረዳ የሚገኝ ሲሆን ከአዲስ አበባ 754 ኪ.ሜ፣ ከባህር ዳር 195 ኪ.ሜ፣ ከደብረ ታቦር 90ኪ.ሜ ይርቃል፡፡

ዛሬ ላይ በጦርነቱ ይህ ታላቅ ገዳም ጉዳት ደርሶበታል ። ጦርነቱ ለቅርሶቻችን ህልዉና ስጋት ከሆነ ቆይቷል :: እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ በቅርሶቻችን ላይ የሚደርሰዉን ጉዳት እያወገዝን በጦርነቱ ቀጠና ዉስጥ የሚገኙ ቅርሶቻችን ላይ አስፈላጊዉን ጥበቃ በመንግሥት በኩል ሊደረግ ይገባል ስንል እናሳስባለን ።

#ጨጨሆ
#በቅሎአግድ

04/08/2021
መተሃራ ከተማን የሚያጠፋት፤ የአዋሽ ወንዝ ስጋት አሲዳማዉ ሃይቅ -  #በሰቃየበሰቃ ሃይቅ አንድ ደሴት ሲኖረዉ ጥልቅ እና ጨዋማ ሃይቅ ነዉ። የጨዋማነት መጠኑ10.7 Ds/m ነዉ።  መገኛዉ ከ...
04/08/2021

መተሃራ ከተማን የሚያጠፋት፤ የአዋሽ ወንዝ ስጋት
አሲዳማዉ ሃይቅ - #በሰቃ

የበሰቃ ሃይቅ አንድ ደሴት ሲኖረዉ ጥልቅ እና ጨዋማ ሃይቅ ነዉ። የጨዋማነት መጠኑ10.7 Ds/m ነዉ። መገኛዉ ከአዲስአበባ ደቡብ ምስራቅ 200 ኪሜ ርቀት በታላቁ ስምጥ ሸለቆ መካከል መተሃራ አካባቢ ሲሆን በ950 ሜ የባህር ጠለል ከፍታ ላይ ይገኛል።

ሃይቁ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየሰፋ በመምጣቱ በቅርበት የምትገኘዋ የመተሀራ ከተማ ከ20-30 አመታት ድረስ ሊያጠፋት ይችላል ተብሎ ይገመታል ።

ባለፉት 50 አመታት ዉስጥ ሃይቁ ከነበረበት 3 ኪሜ ስኩዌር ስፋት ወደ 10500 ስኩዌር ስፋት አድጓል። ከነበረበት %ያክል እንደማለት ነዉ። ሃይቁ በእሳተገሞራ ፍንዳታ የተፈጠረ ሲሆን በምድር ዉስጣዊ ሃይል መብላላት ምክንያት እጅግ በጣም ተስፋፊ ሃይቅ ነዉ።

ከሃይቁ በጣም መስፋፋት እና አሲዳማነት አንጻር ከአዋሽ ወንዝ ጋር የሚቀላቀል ከሆነ ለበርካታ የጥጥ እና ስኳር እርሻ አምራቾች ከፍተኛ ስጋት የሚፈጥር ሲሆን 1200 ኪሜ የሚጓዘዉ እና ከ10 ሚሊዮን ህዝብ በላይ በወንዙ በእርሻ እና አሳ ምርት ለሚተዳደሩ ገበሬዎች እና አርብቶ አደሮች ግብአቶች ስጋትንም መፈጥሩ እሙን ነዉ።

ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ ጥቅም ጋር የሚያያዘዉ የዚህ ሃይቅ መስፋፋት ለአካባቢው የከርሰ ምድር ዉሃ ስጋት ከሆነ ቅየት ብሏል።

በርካታ ነዋሪዎችን በሃይቁ መስፋፋት ምክንያት ተፈናቅለዋል። የአዲስ አበባ -ድሬዳዋ ጅቡቲ የባቡር ሃዲድ ድሮ ከነበረበት ቦታ በሃይቁ መስፋፋት የቀየረ ሲሆን የባቡር መንገዱን ጨምሮ አዲስ አበባን ከምስራቁ ኢትዮጵያ የሚያገናኘት የአስፓልት መንገድም አደጋ ተጋርጦባታል።

ከዚህ ዉጭ ግን ሃይቁን ከአካባቢው ያማረ መልክአ ምድር ጋር አያይዞ ማየት እና ፎቶ ማንሳት መንፈስን ያድሳል።

ተጨማሪ መረጃዎችን እና ሳይንሳዊ ትንታኔዎችን ያጋሩኝ።
ⓒጎቾ ወርቁ

31/07/2021
Ethiopia's   upset world champion and world record holder Joshua Cheptegei to claim 10,000m gold in Tokyo's first athlet...
30/07/2021

Ethiopia's upset world champion and world record holder Joshua Cheptegei to claim 10,000m gold in Tokyo's first athletics final.
Congrats Ethiopiaye 🇪🇹

Read more https://www.bbc.com/sport/olympics/58029093

 #ሽሞ ከድሬዳዋ የመንገድ ላይ ምግቦች መካከል ግብአቶች፦  አደንጓሬ ፣ ድንች ፣ባሮ ሽንኩርት፣ ዝንጅብል ነጭ ሽንኩርት ፣የተፈጨ ቃሪያ ፣ ሚጥሚጣ ፣ጨዉ ፣ ዘይት  one of the stree...
30/07/2021

#ሽሞ ከድሬዳዋ የመንገድ ላይ ምግቦች መካከል
ግብአቶች፦ አደንጓሬ ፣ ድንች ፣ባሮ ሽንኩርት፣ ዝንጅብል ነጭ ሽንኩርት ፣የተፈጨ ቃሪያ ፣ ሚጥሚጣ ፣ጨዉ ፣ ዘይት

one of the street foods in the pearl of the valley, Diredewa
So Hot and Spicy

 #ሽሞ ከድሬዳዋ የመንገድ ላይ ምግቦች መካከል ግብአቶች፦  አደንጓሬ ፣ ድንች ፣ ነጭ ሽንኩርት ፣ዝንጅብል፣ የተፈጨ ቃሪያ ፣ ሚጥሚጣ ፣ጨዉ ፣ ዘይት  one of the street foods ...
30/07/2021

#ሽሞ ከድሬዳዋ የመንገድ ላይ ምግቦች መካከል
ግብአቶች፦ አደንጓሬ ፣ ድንች ፣ ነጭ ሽንኩርት ፣ዝንጅብል፣ የተፈጨ ቃሪያ ፣ ሚጥሚጣ ፣ጨዉ ፣ ዘይት

one of the street foods in the pearl of the valley, Diredewa
So Hot and Spicy

  የጉዞ መረጃ፣ ትዝብት እና ሙያዊ እይታዎች የቁልቢ ገብርኤል ቤ/ክ በራስ መኮነን ወልደሚካኤል ለአድዋ ጀግኖች መታሰቢያ የተሰራ ሲሆን አሁን ያለው ግዙፍ ቤ/ክርስቲያን በልጃቸዉ  በአፄ ሀይ...
27/07/2021


የጉዞ መረጃ፣ ትዝብት እና ሙያዊ እይታዎች

የቁልቢ ገብርኤል ቤ/ክ በራስ መኮነን ወልደሚካኤል ለአድዋ ጀግኖች መታሰቢያ የተሰራ ሲሆን አሁን ያለው ግዙፍ ቤ/ክርስቲያን በልጃቸዉ በአፄ ሀይለስላሴ በ1954 አም የተሰራ ነዉ።

ከአዲስ አበባ 465 ኪሜ ከድሬዳዋ 60 ኪሜ ርቀት ይገኛል። ለኦርቶዶክስ አማኞች ይህ ቅዱስ ቦታ ትልቅ ዋጋ ያለዉ ሲሆን አማኞች በአመት 2 ጊዜ (ታህሳስ 19 እና ሃምሌ 19) ሃይማኖታዊ ጉዞ እና ክብረበአል ይታደማሉ::

ስለት የሚሰማ ቤተክርስቲያን እንደሆነ በርካታ አማኞች ይናገራሉ። ለመፀለይ ፣ ለስለት እና ስለታቸዉን ለማስገባት ከመላዉ ኢትዮጵያ በየአመቱ ከላይ በተጠቀሱት ቀናት በ100 ሺዎች የሚቆጠሩ ምእመናን ደጁን ይረግጣሉ።

ቤተክርስቲያኑ በ2300 ሜ ከፍታ ከባህር ጠለል በላይ ሲገኝ ዙሪያዉን እጅግ የሚያምር እና መንፈስ ን የሚያድስ መልክአምድር መመልከት ይቻላል::

ቱር ኢትዮጵያ የዘንድሮውን አመታዊ የቁልቢ ክብረ በአል ላይ የተገኘ ሲሆን የሚከተሉትን ነጥቦች ለመታዘብ ችሏል።

1. ከፍተኛ የንግድ ትእይንት ከቤተክርስቲያኗ በቅርብ ርቀት (ከ10ሜ ጀምሮ) ይፈጸማል ። ይህም ሁኔታ የተጓዦችን የእንቅስቃሴ ነጻነት የሚጋፋ ከመሆኑ በተጨማሪ ሃይማኖታዊ ዋጋዉን ይቀንሰዋል ብለን እናስባለን።

2. ደረጃውን የጠበቀ መንገድ እና የመኪና ማቆሚያ አለመኖሩ

3. ቁልቢም ሆነ በቅርብ ርቀት የሚገኙ ከተሞች ላይ የማረፊያ እና ደረጃዉን የጠበቀ የምግብ እና መጠጥ እንዲሁም ሌሎች አገልግሎቶች አለመኖር መታዘብ ችለናል ።

4. ፍተሻ ቦታ ላይ ለተከለከሉ እና ወደ ቤተክርስቲያኒቷ ቅጥር ግቢ መግባት ለሌለባቸዉ እቃዎች በአደራ መልኩ የማስቀመጫ ቦታ ወይም ሳጥን አለመኖሩ

5. የጸጥታ ሃይሎች ትጋታቸዉን ብናደንቅም ተጓዦችን በማመናጨቅ እና ስርአት በሌለዉ መልኩ ማስተናገድ

6. የኮቪድ ፕሮቶኮሎች ማክበር ላይ ከፍተኛ የሆነ መዘናጋት መኖሩን መታዘብ ችለናል ::

ያደነቅናቸዉ ነገሮች

1. አቢሲኒያ ባንክ ጊዚያዊ የባንክ አገልገሎት ሲሰጥ ማየታችን

2. NTOን ጨምሮ ጥቂት የጉዞ አዘጋጅ እና አስጎብኚ ድርጅቶች በርካታ እንግዶችን ይዘዉ መምጣታቸዉ

3. የምእመናኑ የእርስ በርስ መረዳዳት እና መከባበር በአሉን በደመቀ እና አንዳችም የደህንነት እና የጸጥታ ችግር ሳይፈጠር መጠናቀቁ

በመጨረሻም ትዝብታችንን እና የመፍትሔ ሀሳቦቻችንን በስፍራዉ ላገኘናቸዉ የቤ/ክርስቲያኗ አስተዳዳሪ ፣ ለፀጥታ ሃይሎች ፣ ለአካባቢው ተወላጆች እና ለአንዳንድ ተጓዦች አካፍለናል::

ቅርሶቻችን ሃላፊነት በሚሰማው መልኩ እንጎብኝ።
እስቲ የዚህ አመት ክብረ በአል ላይ የታደማችሁ ሀሳባችሁን አካፍሉን ።

From today's  ETHIOPIA - Long Lives 🇪🇹
22/07/2021

From today's
ETHIOPIA - Long Lives 🇪🇹

ታሪካዊው የዶዶታ መስጊድ**************************ቅርስ የምንለው አንድም በተፈጥሮ የታደልነው አልያም ካለፈው ትውልድ የወረስነውን የሰዎችን የፈጠራ ስራ ባህላዊና ታሪካዊ ውጤት...
20/07/2021

ታሪካዊው የዶዶታ መስጊድ
**************************
ቅርስ የምንለው አንድም በተፈጥሮ የታደልነው አልያም ካለፈው ትውልድ የወረስነውን የሰዎችን የፈጠራ ስራ ባህላዊና ታሪካዊ ውጤት እንደሆነ ባለሙያዎች ይናገራሉ ፡፡ ከሰዎች የፈጠራ ውጤት አንዱ ሃይማኖታዊ ማምለኪያ ሥፍራን የመገንባት ተግባር ነው፡፡ በዛሬው ፁሁፌ ኢትዮጵያ ውስጥ ካሉት የአምልኮት ሕንፃዎች መካከል አንዱ የሆነውን እድሜ ጠገቡን የደዌ "ዶዶታ" መስጊድ በወፍ በረር አስቃኛቹሃለው፡፡
በኢስላማዊው ዘመን አቆጣጠር በ1176 ዓመተ ሒጅራ አካባቢ ከ(353 ) ዓመት በፊት እንደታነፀ ይነገርለታል፡፡ የዶዶታ መስጊድ የሚነኘው በአማራ ክልላዊ መንግስት በኦሮሞ ዞን ከሚሴ በ"ደዌ ሃረዋ" ወረዳ የሚገኝ ሲሆን ከዞኑ ዋና ከተማ ከሚሴ ተነስተው በምሥራቅ አቅጣጫ በሚወስደው የጠጠር መንገድ በ40 ኪ,ሜትር ርቀት ላይ ይገኛል ፡፡
የመስጊዱ አሰራር እጅግ የሚደንቅ ነው ከውጭ በኩል ሲለካ የ3.30 ሜትር ከፍታ ፣ በውስጥ በኩል የ2.50 ሜትር ከፍታ ያለው ሲሆን መግቢያና መውጫ ሁለት በሮችም አሉት ። ጣሪያውን የሚሸከሙ 27 ያህል ምሰሶዎች አሉት ፡፡ የመስጊዱ ግድግዳ አስደናቂ ውፍረት ያለው ሲሆን በአንደኛው በር በኩል ያለው ብቻ የ3.10 ሜትር ስፍት ያለው መሆኑ ቅረወሱን ልዩና አስገራሚ ያደርገዋል።
ታሪካዊው የዶዶታ መስጊድ የተገነባው ሸህ የሱፍ /አባ አስያ/ በተባሉ ግለሰብ ሲሆን ያለማንም ረዳት እንደተሠራም ይነገራል፡፡ ሸህ የሱፍ በአርጐባ "አሬራ ፋራ" ተብሎ በሚጠራ አካባቢ እንደተወለዱም ይነገራል፡፡ ሸህ የሱፍ መስጊዱን ገንብተው ለመጨረስ 18 ዓመታት ወስዶባቸዋል፡፡
ወደ መስጊዱ ለመድረስ ከ ከሚሴ ከተማ ተነስተው, በ"ዲቢኛ" በኩል አድርገው "ቦራ" ከደረሱ ተቃርበዋል , በ"አልዬ" አልያም "ጎኒ" በሚባሉ መንደሮች አድርገው ወደ አካባቢው እንደደረሱ የመንገዱን ቀኝ ጠርዝ ይዘው በሰልፍ የተደረደሩ ትላልቅ ድንጋዮች ያገኛሉ፡፡ የአካባቢው ማህበረሰብ እንደሚናገሩት ድንጋዮቹ ለመስጊዱ ሥራ የተዘጋጁ እንደነበሩና መስጊዱ በማለቁ ምክንያት ይቁሙ ተብለው የቆሙ እንደሆነ በአፈታሪክ ይነገራል፡፡
ግድግዳው የተሠራው ሙሉ በሙሉ ከድንጋይ ግንብ ሲሆን ጣሪያው በወይራ እንጨት ርብራብ ተደርጐ ከእንጨቱ ላይ በድንጋይ ኮረት፣ በአሸዋ ተሞልቶ በመጨረሻም በአፈር የተደለደለ ነው ። ጣሪያውን ከውጪ ሲመለከቱት ሜዳ እንጂ ቤት አይመስልም ከዚህ አንፃር ለመናፈሻነትም ያገለግላል ። የዶዶታ መስጊድ ጥንታዊ በመሆኑ በውስጡ አያሌ እድሜ ጠገብ የስነ ፁሁፍ ውጤቶች ይገኙበታል።
ይህ ብቻ አይደለም መስጊዱ በርካታ ጥንታዊ ኪታቦች /ሃይማኖታዊ መጻሕፍት/ 1480 ዓመት ያስቆጠሩ መሆናቸው የመስጊዱን ጥንታዊና ታሪካዊ ስለመሆኑ ጉልህ ማሳያዎች ናቸው ፡፡የሃይማኖት አባቶች እንደሚናገሩት መስጊዱ ከመሠራቱ በፊት በአካባቢው ሸህ አሊ ወሌ የሚባሉ አባት ነበሩ፡፡ ከእለታት አንድ ቀን ለካዳሚዎቻቸው /አገልጋዮቻቸው/ የሱፍ የሚባል ሰው እንዲጠራላቸው መልዕክት አስተላለፉ፡፡ መልዕክቱ ወደ ሕዝቡ ተሠራጭቶ 21 የሱፊዎች ወደ ሸህ አሊ ወሌ እንደመጡ ይናገራሉ፡፡
ከመጡት የሱፎችን ሁሉ አንተ አይደለህም እያሉ ሲመልሱ በመጨረሻ ሸህ የሱፍ /አባ አስያ/ ሲመጡ በእኔ ቦታ እርሱን አስቀምጫለሁ በማለት ለካዳሚዎቻቸውና ለአካባቢው ታላላቅ ሰዎች አሳወቁ፡፡ ከዚህ በኋላ ሸህ የሱፍ /አባ አስያ/ የራሳቸውን እንቅስቃሴ የቁርዓን ትምህርት ፣ ፊቅህ እና ሌሎች ኢስላማዊ ትምህርቶችን በመስጠት ጀመሩ፣ የቁርአን ተፍሲር /ትርጉም/ን በእጃቸው በመፃፍ ማህበረሰቡን በስፍት እንዳገለገሉ የአካባቢው ሽማግሌዎች ይናገራሉ ፡፡

ሸህ የሱፍ በአርጐባ፣ በባቲ አካባቢ ገርፋ፣ ኤጀርቱ ፣ በከሚሴና፣ ሾንኬ ፣ እንዲሁም ደዌ ውስጥ ጂባ በተባለ ቦታ መስጊድ በመሥራት እንደኖሩ ይነገርላቸዋል፡፡ በጊዜው የእስልምና ሕጐች ጠበቅ በማድረግ ጀመአ የማይወዱትን ሶላት የማይሰግዱትን በእስራት ይቀጡ ነበር፡፡
ሸህ የሱፍ (አባ አስያ) ዶዶታ ሲመጡ አካባቢው ኦሮሞዎች የሚኖሩበት ጫካ ስለነበር መስጊድ እንዲሠሩ ፈቃድ ጠይቀው ተፈቀደላቸው፡፡
መስጊዱን ሲሠሩ ከአካባቢው ተወላጅ "ጃሌ" የተባለ ግለሰብ ካዳሚያቸው ከመሆን በስተቀር ሥራ ሲሠሩ አንድም ሰው ከአጠገባቸው እንዲቀመጥ እንደማይፈቅዱ ይነገራል፡፡ በአካባቢው የሚገኙ የእስልምና አባቶች እንደሚናገሩት መስጊድ የተሠራው በድንጋይ ካብስለነበር አንድ ድንጋይ ሲያስቀምጡ፣ 100 ጊዜ ምሕረትን እንለምናለን፣ 100 ጊዜ ከአላህ በቀር ጌታ የለም፣ 100 ጊዜ የጠራህ ጌታ ነህ፣ 100 ጊዜ ነህ፣ 100 ጊዜ ምስጋና ላንተ ይሁን ካሉና ሁለት ረካዕ ከሰገዱ በኋላ ወደ ሥራው ያመሩ እንደነበር ይወሳል፡፡ የመስጊዱ ሥራ እስኪጠናቀቅ በእያንዳንዱ ድንጋይ መካከል ከላይ የተጠቀሰውን ቃል ይጠቀሙ እንደነበርም ይገልፃሉ፡፡
የግንቡን ሥራ ለ18 ዓመታት ብቻቸውን ካከናወኑ በኋላ ግንቡን በመጨረስ ወደ ጣሪያ ሥራ ተሸጋግረው ሶስት ምሰሶዎችን እንደተከሉ ድንጋይ እጃቸውን መቷቸው ተሰበሩ፡፡ በዚህ ጊዜ አላህ የመስጊድ ሥራ በቃህ ማለቱ ነው ብለው ሥራቸውን አቆሙ፡፡ ከተወሰነ ጊዜ በኋላ አረፉ ( ወደ አኺራ) የሄዱ ሲሆን ዶሪሀቸው /መቃብራቸው/ በመስጊዱ አጠገብ ይገኛል፡፡
ከሕልፈታቸው በኋላ ልጃቸው አባ ዑመር ሸህ አህመድ የጣሪያውን ሥራ አጠናቀው መስጊዱ አሁን የያዘውን ገፅታ እንዲይዝ አድርገውታል፡፡ መስጊዱ በደወይ ውስጥ መጀመሪያ ቁርአን የተቀራበት ሸሪአ የተቋቋመበት የቁርአን ትምህርትና የሸሪአ ደንብ ለሕዝብ የተሠራጨበት በመሆኑ በእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች ዘንድ ከፍተኛ ግምት ይሰጠዋል፡፡ በአሁኑ ጊዜ መስጊዱ በአገልግሎት ላይ ሲሆን የነቢዩ መሐመድ መውሊድና የኢድ አልፈጥር (ረመዳን) በዓላት በድምቀት ይከበሩበታል፡፡

ይህ የአገር ሃብት የህዝብ ቅርስ ለመጪው ትውልድ ይተላለፍ ዘንድ በቂ ጥበቃና እድሳት ሊደረግለት ይገባል። በውስጡ ያሉትም ታሪካዊ የጥንት ኪታቦች / መፅሃፎች / በክብር ሊቀመጡ ይገባል ። ታሪክ የሌለው ህዝቡ የመጣበትን አያውቅም የሚሄድበትንም አቅጣጫ በቅጡ አይረዳም እና ያከባቢያችንን ታሪክ በጋራ እንድንጠብቅ አደራ በማለት የዛሬውን የዶዶታ መስጊድ ቅኝቴን በዚሁ ጨረስኩኝ።
Abudi Moha

Address

Haile Selassie Street
Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Tour in Ethiopia ቱር ኢትዮጵያ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Tour in Ethiopia ቱር ኢትዮጵያ:

Share

Category