Visit Gojjam

Visit Gojjam ይህ ገፅ የጎጃም የቱሪስት መስህቦችን ማስተዋወቂያ ገፅ ነው።

  ...  #ጋመች➖➖➖➖➖➖➖➖◉ “አመን ወንዛወንዙ ያሳምራል ገላ ...” ተብሎ ከሚዘፈንላት ባለምርጥ ውኃ - ዳንግላ ከተማ 25 ኪሎሜትር አካባቢ ርቆ በዛው በዳንግላ ወረዳ ሊጋባ ቀበሌ ከት...
19/10/2022

... #ጋመች
➖➖➖➖➖➖➖➖

◉ “አመን ወንዛወንዙ ያሳምራል ገላ ...” ተብሎ ከሚዘፈንላት ባለምርጥ ውኃ - ዳንግላ ከተማ 25 ኪሎሜትር አካባቢ ርቆ በዛው በዳንግላ ወረዳ ሊጋባ ቀበሌ ከትሟል - ጋመች ፏፏቴ!

◉ ፏፏቴው ግዮን ከሰከላ ተነስቶ ሲገሰግስ ሜጫና ዳንግላን የሚያዋስንበት ቦታ ላይ የሚገኝ የግዮን - ዓባይ ገፀበረከት ነው! ዓባይ የአገር ሲሳይ .... 💙

◉ ከቱሪዝም መስኮቶች ርቆ ብዙ ዘመናትን ተደበቀ! ዛሬ ግን አይኖች ጎበኙት - በእይታ ራዳር ውስጥም ገባ “ድብቁ” ፏፏቴ - ጋመች!!

 ➖➖➖➖➖◉ ይሄ አስገራሚ ተፈጥሮ የሚገኘው በምዕራቡ የጎጃም ክፍል ውስጥ ሰከላ ወረዳ ላይ ነው።◉ ቦታው ከፍ ያለ ትልቅ ተራራ ጫፍ ላይ ተፈጥሮ ለመተላለፊያ ይሆን ዘንድ በልኩ ያዘጋጀችው ይ...
25/09/2022


➖➖➖➖➖

◉ ይሄ አስገራሚ ተፈጥሮ የሚገኘው በምዕራቡ የጎጃም ክፍል ውስጥ ሰከላ ወረዳ ላይ ነው።

◉ ቦታው ከፍ ያለ ትልቅ ተራራ ጫፍ ላይ ተፈጥሮ ለመተላለፊያ ይሆን ዘንድ በልኩ ያዘጋጀችው ይመስላል!🥰 ቦታው ወዲህ ውበት ወዲያ ደግሞ መነፅር ነው!

  ... 💙➖➖➖➖➖➖◉ በሀገራችን ከሚገኙ የከፍተኛ ቦታ ሐይቆች አንዱ ጉደራ ሐይቅ ሲሆን በምዕራባዊው የጎጃም ክፍል በማህፀነ ግዮኗ  #ሰከላ ወረዳ ውስጥ ይገኛል!◉ ይህ ውብ ሐይቅ ከወረዳው...
20/09/2022

... 💙
➖➖➖➖➖➖

◉ በሀገራችን ከሚገኙ የከፍተኛ ቦታ ሐይቆች አንዱ ጉደራ ሐይቅ ሲሆን በምዕራባዊው የጎጃም ክፍል በማህፀነ ግዮኗ #ሰከላ ወረዳ ውስጥ ይገኛል!

◉ ይህ ውብ ሐይቅ ከወረዳው መዲና #ግሽዓባይ በደቡባዊ አቅጣጫ 19 ኪሎሜትር ርቀት ላይ በሰከላ ከፍተኛ ቦታዎች በአንዱ አሰዋ ዘገዛ ቀበሌ ላይ ተደላድሎ ሰፍሯል!💙 ሐይቁ 1.5 ኪሎሜትር ስፋት አለው!

◉ ይሄ ሐይቅ ለወረዳው ትልቅ የመስህብና የልማት አቅም መሆን የሚችል ያልተሰራበት የወደፊቱ ጥሬ ገንዘብ ነው!🥰

  🙏➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖◉ ብሔረ ህያዋን አጼ መልካ ስላሴ አንድነት ገዳም በምስራቅ ጎጃም   ወረዳ  #ደጎልማ በሚባል ቀበሌ ዉስጥ ከደብረ ኤልያስ ከተማ ምዕራብ አቅጣጫ 35 ኪ.ሜ ርቆ...
19/09/2022

🙏
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖

◉ ብሔረ ህያዋን አጼ መልካ ስላሴ አንድነት ገዳም በምስራቅ ጎጃም ወረዳ #ደጎልማ በሚባል ቀበሌ ዉስጥ ከደብረ ኤልያስ ከተማ ምዕራብ አቅጣጫ 35 ኪ.ሜ ርቆ ይገኛል።

◉ ገዳሙ የሚገኝበት ቦታ ዝቅተኛና ለም ሆኖ በአራት አቅጣጫ በሰንሰለታማ ጎራዎች የተከለለ ነው! ገዳሙ በወንዞች የተከበበ ገነት ነው! በደቡብ #የተጥማ በሰሜን #የተምጫ እና በስተምዕራብ ደግሞ ከተገናኙበት ቦታ ከፍ ብሎ ይገኛል፡፡

◉ በገዳሙ ዉስጥ በርካታ መነኮሳት የሚገኙ ሲሆን እናትና አባት የሌላቸዉ ህፃናት ማረፊያና ማሳደጊያም ነው፡፡ ገዳሙ የመንፈሳዊ ማዕከልነቱ ብቻ ሳይሆን በልማትም ከፍተኛ እንቅስቃሴ የሚደረግበት እና በርካታ የልማት ስራዎች የሚከናወኑበት ገዳም ነዉ፡፡

◉ በተለይም በግብርና ስራ እንደ ሰርቶ ማሳያ ማዕከልነት ማገልገል የሚችል እና ዉጤታማ የሆኑ በርካታ የግብርና ስራዎች እየተሠሩበት የሚገኝና ልምላሜ የማይለየዉ የበርሃ ገነት ነዉ፡፡

◉ በአጠቃላይ ገዳሙ በአቀማመጡ፣ የልማት እንቅስቃሴ እና በፈዋሽ ፀበሉ ታዋቂ የሆነ እምቅ የመስህብ ሀብት ነው፡፡

◉ የገዳሙ ዓመታዊ ክብረ በዓል ጥር 7 እና ሀምሌ 7 ቀን ይከበራል!!

  ➖➖➖➖➖➖◉ ይሄ ውብና ማራኪ አይነ ግቡ ምድር በጎጃም ክፍለሐገር እነሴ ውስጥ የሚገኝ ነው - አባ ምኒዮስ - ጎንቻ!!◉ ለኢኮ ቱሪዝምና ሀይኪንግ (ጉዞ)  ወዳጆች አመችና ተመራጭ ቦታ ነ...
18/09/2022


➖➖➖➖➖➖

◉ ይሄ ውብና ማራኪ አይነ ግቡ ምድር በጎጃም ክፍለሐገር እነሴ ውስጥ የሚገኝ ነው - አባ ምኒዮስ - ጎንቻ!!

◉ ለኢኮ ቱሪዝምና ሀይኪንግ (ጉዞ) ወዳጆች አመችና ተመራጭ ቦታ ነው! በዛ ላይ የዳበሩ የታሪክ ዘለበቶቹ የማይጠገቡ ናቸው!

 ➖➖➖➖➖▣ የዓባይ ሸለቆ በምስራቃዊው የጎጃም ክፍል በተለይ መልክዓምድራዊ አቀማመጡ ለአይን ማራኪ ብቻ ሳይሆን የመንፈስ ውስጠትን የሚይዝ አንዳች ነገር ያለው ነው!▣ ይህ ረዥም ሸለቆ መልክ...
18/09/2022


➖➖➖➖➖

▣ የዓባይ ሸለቆ በምስራቃዊው የጎጃም ክፍል በተለይ መልክዓምድራዊ አቀማመጡ ለአይን ማራኪ ብቻ ሳይሆን የመንፈስ ውስጠትን የሚይዝ አንዳች ነገር ያለው ነው!

▣ ይህ ረዥም ሸለቆ መልክዓምድራዊ አቀማመጡ ብቻ ሳይሆን በያዘው ብዝሃ ህይወትና የማዕድን ክምችትም ተወዳዳሪ የለውም! ሸለቆው የወደፊት የምርምርና የሀብት ማዕከልም ነው!

▣ ከገንጅ እስከ ጎንጅ፤ ከሁለት እጁ እስከ እነብሴ፤ ከሸበል እስከ ደጀን፤ ከአዋበል እስከ ጎዛምን፤ ከደብረ ኤልያስ እስከ ቡሬ ... የትየለሌ ርቀት! የብዝሃ ህይወት ማማ! የማዕድናት ጉዝጓዝ - ዓባይ ሸለቆ!🥰

▪  ...  #ጎጃም! 💙    ➖➖➖➖➖➖➖➖➖◉ ባህር ዳር ከተማን የሚያውቅ ሰው “አሲኗራ” የሚል የሆቴል ስም አንብቦ ይሆናል! ምናልባትም በስያሜው ተወዛግቦ ሊያውቅ ይችል ይሆናል!◉ የሆቴሉ...
26/07/2022

▪ ... #ጎጃም! 💙
➖➖➖➖➖➖➖➖➖

◉ ባህር ዳር ከተማን የሚያውቅ ሰው “አሲኗራ” የሚል የሆቴል ስም አንብቦ ይሆናል! ምናልባትም በስያሜው ተወዛግቦ ሊያውቅ ይችል ይሆናል!

◉ የሆቴሉ ስያሜ ከዚህ ተራራ ስም የተወሰደ ነው! ተራራው በምዕራባዊው የጎጃም ክፍል ሰሜን አቸፈር ወረዳ ከጣና ሐይቅ ብዙም ሳይርቅ ከዱርቤቴ - ይስማላ - ቁንዝላ በሚወስደው መንገድ ግርጌ ላይ ይገኛል!

Address

Bahir Dar

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Visit Gojjam posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category


Other Tour Guides in Bahir Dar

Show All