ባሕር ዳር- 𝙗𝙖𝙝𝙞𝙧 𝙙𝙖𝙧

ባሕር ዳር- 𝙗𝙖𝙝𝙞𝙧 𝙙𝙖𝙧 Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from ባሕር ዳር- 𝙗𝙖𝙝𝙞𝙧 𝙙𝙖𝙧, Travel Company, BAHIR DAR, Bahir Dar.

 ! በዛሬው ቀን የአማራ ክልል ፖሊስ የልዩ ኀይል አባላት፣ 5ኛ ዙር የመካከለኛ አመራር ኮርስ እና የወንጀል ክትትል ባለሙያዎች አስመርቋል። ፎቶ.Amhara Pol
08/05/2021

! በዛሬው ቀን የአማራ ክልል ፖሊስ የልዩ ኀይል አባላት፣ 5ኛ ዙር የመካከለኛ አመራር ኮርስ እና የወንጀል ክትትል ባለሙያዎች አስመርቋል።

ፎቶ.Amhara Pol

07/05/2021
እልፎችን በጀንበር በምትገል ምድር                          በምትበላ ሀገርየሌም ሌላ ዜና የለም ሌላ ሰበር በቁስላችን እንጨት ባትሰዱ ምነበር #መተከል!!!
13/01/2021

እልፎችን በጀንበር በምትገል ምድር
በምትበላ ሀገር
የሌም ሌላ ዜና የለም ሌላ ሰበር
በቁስላችን እንጨት ባትሰዱ ምነበር

#መተከል!!!

" አማሮች ከሰልፍ አልፈውሰይፍ ቢያነሱ አይፈረድባቸውም !""ባለፉት ሁለት ዓመታት ዘራቸው እየተቆጠረ ብቻ በመቶዎች የሚቆጠሩት ታርደዋል፣ በሺዎች የሚቆጠሩት ተፈናቅለዋል፣ የብዙዎች ንብረት ወ...
26/10/2020

" አማሮች ከሰልፍ አልፈው
ሰይፍ ቢያነሱ አይፈረድባቸውም !"
"ባለፉት ሁለት ዓመታት ዘራቸው እየተቆጠረ ብቻ በመቶዎች የሚቆጠሩት ታርደዋል፣ በሺዎች የሚቆጠሩት ተፈናቅለዋል፣ የብዙዎች ንብረት ወድሟል። መንግስትም ዘላቂ መፍትሄ ከመፈለግ ይልቅ ነገሮችን እያድበሰበሰ እያለፈ ለብዙዎች አሰቃቂ ሞት ምክንያት ሆኗል!!"
ኦባንግ ሜቶ

ማነው ወኪላችን ?ከዚህ በፊት ሞተን ምንም አልመሰለን ትላንትናም ሞተን ምንም አልመሰለን የዛሬው በዛና እግር እግር አለን ።ማነህ ምንድነህ ከየት ነህ የማነህ ተብሎ እየተለዬ አማራ ባ'ገሩ መ...
25/10/2020

ማነው ወኪላችን ?
ከዚህ በፊት ሞተን ምንም አልመሰለን
ትላንትናም ሞተን ምንም አልመሰለን
የዛሬው በዛና እግር እግር አለን ።
ማነህ ምንድነህ ከየት ነህ የማነህ ተብሎ እየተለዬ
አማራ ባ'ገሩ መከራውን አዬ ።
ጫካውን መንጥረን ከአውሬ ጋር ተታግለን
ሀብት ንብረት ሰርተን በገዛ አገራችን
መሞት መፈናቀል ስደት መትገላታት
ከሆነማ እጣችን
ንገሩን እንወቀው ማነው ወኪላችን ።
ህዝብ ያልተስማማበት ህግ እያረቀቀ
ወኪል በጉልበቱ ሰው እያደቀቀ
ወይንም ጠንከር አይል እያረገረገ
አማራውን ሁሉ ለሞት መፈናቀል
ለስደት ዳረገ ።
እነ አፄ ቴዎድሮስ በተወለዱበት
እነ አፄ ምኒልክ በተወለዱበት
እነ ንጉስ ሚካዔል በተወለዱበት
እነ በላይ ዘለቀ በተወለዱበት
እነ አስራት ወልደዬስ በተወለዱበት
እነ ይርጋ አበበ በተወለዱበት
እነ አስማረ ዳኜ በተወለዱበት
እነ ጐቤ መልኬ በተወለዱበት
እነ አስቻለው ደሴ በተወሉዱበት
እነ አሳምነው ፅጌ በተወለዱበት
ያ ሁሉ ተረስቶ ሰዎች ቀለዱበት
በአማራው ክብር ላይ ተዘባበቱበት ።
ነቃ በል ወገኔ እምቢ በል ከእንግዲህ
ምንም አይመጣብህ ከመገደል ወዲህ ።
የአምናው የታች አምናው ምንም አልመሰለን
ግፋችን በዛና ዘንድሮስ መረረን ።
እምቢ ትል እንደሆን እምቢ በል አማራ
ማንም ወኪል የለህ ላንተ የሚራራ
ገና የባሰ ነው ያለብህ መከራ
አንድ ሆነህ ተነስ እምቢ በል አማራ ።

አመሰግናለሁ ።

ወንድማችሁ ዱባለ መላክ ነኝ (ጉዱ ገና)
ለሁሉም እንዲደርስ ሼር Shere አድርጉት

💙👌
01/06/2020

💙👌

 #ማለዳየ #ባሕርዳርየ
01/06/2020

#ማለዳየ

#ባሕርዳርየ

 #ባሕርዳር
31/05/2020

#ባሕርዳር

  ፦በአፈ ታሪክ እንደሚነገረው የባሕር-ዳር ስያሜን ያወጡት አፄ ሠርጸ ድንግል ሲሆኑ እሳቸውም ይሕን ታቦት የት እናስቀምጥ ተብለው በተጠየቁ ጊዜ "ከባሕሩ-ዳር" አድርጉ የተባሉ ሰወች ለመንደ...
31/05/2020

፦በአፈ ታሪክ እንደሚነገረው የባሕር-ዳር ስያሜን ያወጡት አፄ ሠርጸ ድንግል ሲሆኑ እሳቸውም ይሕን ታቦት የት እናስቀምጥ ተብለው በተጠየቁ ጊዜ "ከባሕሩ-ዳር" አድርጉ የተባሉ ሰወች ለመንደሩ ባሕር-ዳር ብለው ስያሜ አወጡለት ይባላል።

 ደህና እደሩልኝ ውዶቼ
30/05/2020



ደህና እደሩልኝ ውዶቼ

30/05/2020

ሀሎ ባህር ዳር

ቤዛዊት _ፓላስፀዴ ቀን 💙
30/05/2020

ቤዛዊት _ፓላስ

ፀዴ ቀን 💙

ቤዛዊት ኮረብታየባህር ዳር ከተማን በቅርብ ርቀት ከላይ ወደታች ለመመልከት ተመራጭ ሥፍራ የቤዛዊት ኮረብታ ነው፡፡ የቤዛዊት ኮረብታ በከተማዋ ምስራቃዊ ዳርቻ 5 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ይገኛል፡፡ በ...
30/05/2020

ቤዛዊት ኮረብታ

የባህር ዳር ከተማን በቅርብ ርቀት ከላይ ወደታች ለመመልከት ተመራጭ ሥፍራ የቤዛዊት ኮረብታ ነው፡፡ የቤዛዊት ኮረብታ በከተማዋ ምስራቃዊ ዳርቻ 5 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ይገኛል፡፡ በእግር፣ በመኪና ወይም በብስክሌት በመጓዝ ከኮረብታው መድረስ ይቻላል፡፡ በኮረብታው ላይ አፄ ኃይለ ስላሴ በ1959 ዓ.ም ያሰሩት የቤዛዊት ቤተመንግሥት ይገኛል፡፡

ቤዛዊት ኮረብታ በመሆን እስከተወሰነ ርቀት የአባይን ወንዝ ጠመዝማዛ ጉ‌ዞ፣ በወንዙ ውስጥ የሚንቦጫረቁ ጉማሬዎችንና የተለያዩ አእዋፋትን መመልከት ያስደስታል፡፡

ባህር ዳር በ20ኛው ክፍለ ዘመን መባቻ አካባቢ በደቡባዊ የጣና ጠርዝ የተቆረቆረችው ባህር ዳር ባላት እጹብ ድንቅ ተፈጥሮአዊ አቀማመጥ እና ዙሪያዋን በከበቧት ታሪካዊና ሚስጥራዊ ገዳማት በቱሪ...
30/05/2020

ባህር ዳር

በ20ኛው ክፍለ ዘመን መባቻ አካባቢ በደቡባዊ የጣና ጠርዝ የተቆረቆረችው ባህር ዳር ባላት እጹብ ድንቅ ተፈጥሮአዊ አቀማመጥ እና ዙሪያዋን በከበቧት ታሪካዊና ሚስጥራዊ ገዳማት በቱሪስት መስህብነትና በመዝናኛ ማዕከልነት ተመራጭ የሆነች የሰሜናዊ ምዕራብ ከተማ ናት።

ባህር ዳር በ1830ሜ ከፍታ ላይ የምትገኝና የትሮፒካል የአየር ንብረት የሚበዛባት አፍሪካዊት ከተማ የአማራ ክልል እምብርትና የክልሉ መንግስት መከተሚያ ናት።

ባህር ዳር ውስጥ ውብ በዘንባባ ዛፎች ባጌጡ ጎዳናወቻ የእግር ሽርሽር በማድረግ፣ ማራኪ የሆነውን የጣና ሃይቅን ማራኪ ውበትና የሃሴት እስትንፋሶችን በመኮምኮም፣ ከተማዋን እየከፈለ ረጅም ጉዞውን ወደ ግብጽ በርሃ የሚያደርገውን የአባይ ወንዝና በዙሪያው ያሉ የእንስሳትና የእጽዋት ዝርያወች በመመልከት፣ የጠንካራ ሰራተኛነት ምሳሌ የሚሆኑትን የወይጦ ማህበረሰብን ድንቅ ክህሎቶች በማየት ወይንም ደግሞ ቤዛዊት ኮረብታ ላይ ሆነው የከተማዋንና ተፈጥአዊ አቀማመጥና የዓባይ ወንዝን ጠመዝማዛ ጉዞ በመመልከት የቀኑን ጊዜ ማሳለፍ ይቻላል

Address

BAHIR DAR
Bahir Dar

Telephone

0980233552

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ባሕር ዳር- 𝙗𝙖𝙝𝙞𝙧 𝙙𝙖𝙧 posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Videos

Share

Category



You may also like