ጉዞ ኢትዮጵያ - Guzo Ethiopia

ጉዞ ኢትዮጵያ - Guzo Ethiopia ጉዞ ኢትዮጵያ በሀገራችን ያሉ ተፈጥሯዊ ፣ ሀይማኖታዊ ፣ታሪካ
(1)

የሁሉ አስገኚ ሲሆን በባሪያዉ እንጅ ለመጠመቅ ወደ ዮርዳኖስ ወረደ  የተቀበረ የሞት ደብዳቤአችንን ሻረ ዘላለማዊ ልጆቹ እንሆን  ዘንድ ተጠመቆ አሳየን አብ በደመና የማፈቅረው ልጄ እረሱ ነዉ ...
19/01/2024

የሁሉ አስገኚ ሲሆን በባሪያዉ እንጅ ለመጠመቅ ወደ ዮርዳኖስ ወረደ የተቀበረ የሞት ደብዳቤአችንን ሻረ ዘላለማዊ ልጆቹ እንሆን ዘንድ ተጠመቆ አሳየን አብ በደመና የማፈቅረው ልጄ እረሱ ነዉ ብሎ የመሰከረለት መንፈስ ቅዱስ በአምሳለ እርግብ የወረደለት የልእልናችን መሰረት የነፍሳችን ቤዛ መድኅን ዓለም ክርስቶስ ለአርአያነት በማዬ ዮርዳኖስ በእደ ዮሐንስ ተጠመቀ ።
እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ ።

አዳም የተመኘዉን አምላክነት ያገኘበት ሰማያዊው የማይመረመረዉ ዘመን የማይቆጠርለት መለኮት ዘመን የተቆጠረለት እየገፋነዉ የወደደን እየራቅነዉ የቀረበን ለመዳናችን ተስፋ  የልጅነትን ጸጋ የሰጠ...
07/01/2024

አዳም የተመኘዉን አምላክነት ያገኘበት ሰማያዊው የማይመረመረዉ ዘመን የማይቆጠርለት መለኮት ዘመን የተቆጠረለት እየገፋነዉ የወደደን እየራቅነዉ የቀረበን ለመዳናችን ተስፋ የልጅነትን ጸጋ የሰጠን የዘለለም ሕይወት ይሆነን ዘንድ እነሆ መድኃኒት የሆነዉ ኢየሱስ ክርስቶስ በቤተልሄም ከቅድስት ድንግል ማርያም ከላይ ሳይጎድል ከታች ሳይይጨመር ተወለደ ። የተናቁት እረኞች ከመላእክት ጋር ዘመሩ ።
እንኳን አደረሰን አደረሳችሁ መልካም በዓል ይሁንልን ።

11/12/2023

ኑ የበረከቱ ተካፋይ እንሁን ዓመታዊ የቅዱስ ገብርኤል ክበረ በዓለን በጋራ እናክብር ።

15/02/2021

ታላቅ መንፈሳዊ የበረከት ጉዞ



የጉዞው ዋጋ #500 የምግብና አልጋን ጨምሮ
ወደጉዞው ስንሄድ የምንመለከታቸው ቦታዎች በጥቂቱ

#ደብረብርሀን ስላሴ
#ደብረብርሀን አርሴማ
#አርባ ሀራ መድሀኔ አለም
#ቆጵሮስ ተራራ ፅዋው የተቀመጠበት ቅዱሱ ተራራ
#ክናሊ ተራራ እመቤታችን የፀለየችበት
#ዘብር ገብርኤል

ይህ ቦታ ካሉት ቃልኪዳኖች በጥቂቱ

#ቦታውን የረገጠ 7 ትውልድ ይማርለታል
#ተረከዙላይ በስውር ማህተብ ሲኦልን እንደማያይ ይፃፍለታል
#ከላዮ ላይ በስውር ያሉበት መንፈሶች ይወገድለታል

የዚህ በረከት ተካፋይ መሆን ምትፈልጉ ከስር ባሉት ስልኮች በመደወል አናግሩን
+251910455701
+251913162292


መነሻ ቀን የካቲት 12 አርብ
መመለሻ የካቲት 14 እሁድ
አዘጋጅ ማህበረ ኡራኤል (የእመጓ ኡራኤል ገዳም)

ለአርበኞች ቀን እንኳን አደረሳችሁ።
05/05/2020

ለአርበኞች ቀን እንኳን አደረሳችሁ።

27/03/2020

በኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ_19) በሽታ የተያዙ ተጨማሪ ሰዎች መገኘታቸውን ለማሳወቅ የተሰጠ መግለጫ
___________
በኮሮና ቫይረስ የተያዙ አራት (4) ተጨማሪ ሰዎች በመገኘታቸው በአጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር አስራ ስድስት (16) ደርሷል
___________

መጋቢት 3/2012 ዓ.ም የመጀመሪያው በኮሮና ቫይረስ የተያዘ ሰው በሀገራችን ከተገኘ ወዲህ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ አራት (4) ተጨማሪ ሰዎች በመገኘታቸው በአጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር አስራ ስድስት (16) ደርሷል፡፡ የታማሚዎች ዝርዝር ሁኔታ፡-

ታማሚ 1፡ የ72 ዓመት ሞሪሸሳዊ ሲሆኑ መጋቢት 5 ቀን 2012 ዓ.ም ከኮንጎ ብራዛቪል የተመለሱ ናቸው፡፡ መጋቢት 13፣2012 ዓ.ም ወደ ጤና ተቋም የሄዱ ሲሆን ተቋሙም ለኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ሪፖርት በማደረጉ በተደረገላቸው የላብራቶሪ ምርመራ በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል፡፡ ታማሚውም በለይቶ ማከሚያ ውስጥ የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘ ከታማሚው ጋር ግንኙነት የነበራቸው 6 ሰዎች በክትትል ላይ የሚገኙ ሲሆን ከነሱ ጋር ግንኙነት የነበራቸው ሌሎች ሰዎችን የማጣራት ሂደት እየተከናወነ ይገኛል፡፡

ታማሚ 2፡ የ61 ዓመት የአዳማ ከተማ ነዋሪ የሆኑ ኢትዮጵያዊ ናቸው፡፡ ከታማሚው በተገኘው መረጃ መሠረት ግለሰቡ የውጭ የጉዞ ታሪክ ባይኖራቸውም በስራ ባህሪያቸው ምክንያት ከአንድ የውጭ ሀገር ዜጋ ጋር ግንኙነት ነበራቸዉ፡፡ ግለሰቡ መጋቢት 9 ቀን 2012 ዓ.ም የህመም ስሜት ሲሰማቸው ራሳቻውን አግልለው እንደቆዩና መጋቢት 16፣2012 ዓ.ም ወደ ጤና ተቋም የሄዱ ሲሆን ተቋሙም ሪፖርት ባደረገው መሰረት በላብራቶሪ ምርመራ በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል፡፡ በአሁኑ ወቅት ታማሚው በለይቶ ማከሚያ ውስጥ የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘ ከታማሚው ጋር ግንኙነት የነበራቸው 24 ሰዎች በክትትል ላይ የሚገኙ ሲሆን ከነሱ ጋር ግንኙነት የነበራቸው ሌሎች ሰዎችን የማጣራት ሂደት እየተከናወነ ይገኛል፡፡

ታማሚ 3፡ የ28 ዓመት ኢትዮጵያዊት ስትሆን የመጨረሻ ጉዞዋም መጋቢት 12፣ 2012 ዓ.ም እስራኤል ሀገር ደርሳ የተመለሰች ናት፡፡ ግለሰቧም በቀን 16፣ 2012 ዓ.ም በኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በተደረገላት የላብራቶሪ ምርመራ በቫይረሱ መያዙዋ ተረጋግጧል፡፡ በአሁኑ ወቅት ታማሚዋ በለይቶ ማከሚያ ውስጥ የህክምና ክትትል እየተደረገላት ይገኛል፡፡ ከታማሚዋ ጋር ግንኙነት የነበራቸው 7 ሰዎች በክትትል ላይ የሚገኙ ሲሆን ከነሱ ጋር ግንኙነት የነበራቸው ሌሎች ሰዎችን ማጣራት ሂደት እየተከናወነ ይገኛል፡፡

ታማሚ 4፡ የ24 ዓመት ኢትዮጵያዊት ስትሆን የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ የሌላት ቢሆንም የበሽታው ምልክት ከታየባቸው ሰዎች ጋር የነበራት ግንኙነት እየተጣራ መሆኑ እና ግለሰቧም በቀን 17፣ 2012 ዓ.ም በኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በተደረገላት የላብራቶሪ ምርመራ በቫይረሱ መያዙዋ ተረጋግጧል፡ በአሁኑ ወቅት ታማሚዋ በለይቶ ማከሚያ ውስጥ የህክምና ክትትል እየተደረገላት ይገኛል፡፡

በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አማካኝነት እስከ አሁን 718 የላራቶሪ ምርመራ የተደረገ ሲሆን 33 በ24 ሰዓት ( መጋቢት 17 ጥዋት 1፡00 ሰዓት እስከ መጋቢት 18 ጥዋት 1፡00 ሰዓት) ውስጥ የተከናወነ ነው፡፡

ለተጨማሪ መረጃ በነፃ የስልክ መስመር 8335 ወይም በ952 ወይም በመደበኛ የስልክ ቁጥር 0118276796 ወይም በኢሜል አድራሻችን
[email protected] በመጠቀም ማግኘት ይቻላል፡

እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ በሰላም አደረሳችሁ።በዓለ ጥምቀቱ ጎንደር በከፊል።
20/01/2020

እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ በሰላም አደረሳችሁ።
በዓለ ጥምቀቱ ጎንደር በከፊል።

25/12/2019

በጃፓን ኦሎምፒክ ወቅት የጠፋው የአበበ ቢቂላ ቀለበት ከ55 ዓመታት በኋላ ለቤተሰቦቹ ተመለሰ
********************************

እኤአ 1964 በተካሄደው በጃፓን ኦሎምፒክ ወቅት አበባ ቢቂላ የቶኪዮ ማራቶን ውድድርን ባሸነፈበት ውድድር ወቅት የጠፋው ቀለበት ለቤተሰቦቹ ተመለሰ፡፡

የጠፋው የአበበ ቀለበት በወቅቱ በፅዳት ስራ ላይ በነበረች ጃፓናዊት እጅ እንደነበረ እና ከ55 ዓመታት በልጇ አማካኝነት ለአበበ ቤተሰቦች መመለሱ ነው የተገለፀው፡፡

በወቅቱ አበበ ቢቂላ ቀለበቱን በእስታዲዮም መታጠቢያ ክፍል ውስጥ ረስቶት መውጣቱ ስታዲየሙን በማጽዳት ስራ ላይ የነበሩት ባረክ እናት አግኝተውት ለአበበ ቢቂለ እንዲሰጠው ለልጃቸው እንዳስረከቡት ሚስተር ባረክ ተናግሯል፡፡

በወቅቱ የ19 ዓመት ልጅ የነበረው ሚስትር ባረክ ለግማሽ ክፍለ ዘመን የዘለለ አደራ ይዞ በዕድለኝነት ስሜት የአበበን ቤተሰብ ይቅርታ በመጠየቅ ቀለበቱን አስረክቧል፡፡

የአበበ ቤተሰብም ይቅርታውን በመቀበል ቀለበቱን ተቀብለዋል፡፡
ቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
t.me/guzoethiopia

The 10 wonders of the world, as chosen by team Wanderlustታዋቂው የእንግሊዝ የጉዞና ቱሪዝም መጽሔት Wanderlust በትላንትናው ዕለት በዓለም የሚገኙ 10 ...
24/12/2019

The 10 wonders of the world, as chosen by team Wanderlust

ታዋቂው የእንግሊዝ የጉዞና ቱሪዝም መጽሔት Wanderlust በትላንትናው ዕለት በዓለም የሚገኙ 10 አስደናቂ ቦታዎችን ዝርዝር ይዞ ወጥቷል፡፡ ከአስሩ የዓለም አስደናቂ ቦታዎች ውስጥ #በኢትዮጵያ የሚገኙት Danakil Depression በ3ኛ ደረጃ ላሊበላ ደግሞ በ9ኛ ደረጃ በዝርዝሩ ተካተዋል፡፡ ላሊበላ ከ8ቱ የዓለም አስደናቂ ቦታዎች ውስጥ አንዱ መሆኑ የሚታወቅ ነው፡፡

የዓለም አስደናቂ ቦታዎችን ለማየት https://www.wanderlust.co.uk/content/wonders-of-the-world-wanderlust?fbclid=IwAR0a9aPFI3pGTyyDXbefQe8ZfM4j_AmMxheoyjrNcf4uOyW8BLZWFf0JyZU

23/12/2019

ስምንት የአፍሪካ ሀገራት የሳተላይት ምስል ግዢ ጥያቄ ለኢትዮጵያ አቀረቡ!

ኢትዮጵያ "የሳተላይት ምስል" ሽያጩን በራሷ መመሪያ መሠረት ከገዢ ሀገራት ጋር ውል በመፈፀም መሸጥ እንደምትጀምር የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኢንሰቲቲዩት ይፋ አድርጓል። የህዝብ እንደራሴዎች ምክርቤት የሰው ሃብትና ቴክሎጂ ቋሚ ኮሚቴ አባላት በኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኢንሰቲትዩት የሳተላይቷን ቁጥጥርና መረጃ አሰባሰብ ተመልክተዋል።

የቋሚ ኮሚቴው አባላት ለትውልድ የሚተላለፍ አሻራቸውን በማኖራቸው የኢንስቲትዩቱን ሰራተኞች አመስግነዋል። የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚንስትሩ ዶክተር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያ ኢትዮጵያን ከዘርፉ ተጠቃሚ ለማድረግ ባለብዙ ተልዕኮ የሳተላይት መረጃ መቀበያ ተከላ በቅርቡ እንደሚጠናቀቅ ተናግረዋል። የመቀበያ አንቴናው ሀምሳ ሴንቲ ሜትር የምስል ጥራት እና እስከ አምስት የሚደርሱ የሳተላይቶችን መረጃ በአንድ ጊዜ መቀበል የሚያስችል ነው።

የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኢንሰቲትዩት ዳይሬክተር ጀነራል ዶክተር ሰለሞን በላይ ኢትዮጵያ ሳተላይት ባመጠቀች በአራት ቀናት ውስጥ ብቻ ስምንት የአፍሪካ ሀገራት የሳተላይት ምስል ግዢ ጥያቄ ማቅረባቸውን ተናግረዋል። ኢትዮጵያ ታህሳስ 10 ያመጠቀቻት ሳተላይት የታሰበላትን ቦታ ይዛ ስራዋን በአግባቡ እየሰራች መሆኑ ተገልጿል። ሳተላይቷ በቀን አስራ አራት ጊዜ በተዘጋጀላት ምህዋር እየዞረች መረጃ የምትሰበስብ ሲሆን በቀን አራት ጊዜ ደግሞ የሰበሰበችውን መረጃ የመቀበል ስራ ይሰራል፡፡ በቀጣይ የኮሙኒኬሽን ሳተላይት ግንባታ እንደሚጀመርና በዘርፉ የሚደረገው እንቅስቃሴ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተነግሯል፡፡

(MinT)
via tikvahethiopia

እንኳን ደስ አለሽ ኢትዮጵያዬ
20/12/2019

እንኳን ደስ አለሽ ኢትዮጵያዬ

በዓለም ላይ ታዋቂ የጉዞ መረጃ አውጪ ድረገፅ የሆነው ትራቨል ኤንድ ሌይዠር የተባለው ድረገፅ በፈረንጆቹ 2020 ሊጎበኙ ከሚገባቸው 50 የዓለማችን ስፍራዎች ውስጥ አዲስ አበባን አንደኛ አደር...
18/12/2019

በዓለም ላይ ታዋቂ የጉዞ መረጃ አውጪ ድረገፅ የሆነው ትራቨል ኤንድ ሌይዠር የተባለው ድረገፅ በፈረንጆቹ 2020 ሊጎበኙ ከሚገባቸው 50 የዓለማችን ስፍራዎች ውስጥ አዲስ አበባን አንደኛ አደርጎ አስቀምጣል። ልምርጫው ምክንያት ያደረጋቸው ተከታዮቹን ሦስት ነጥቦችን ነው::

1) ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በቤተመንግስት አስገንብተው በቅርቡ ለህዝብ ክፍት ያደረጉት አንድነት ፓርክ የከተማዋ አዲስ ገፅታ መሆኑ

2) ጎብኚዎች የማስፋፊያ ግንባታ የተደረገለት ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ

3) በአዲስ አበባ መካኒሳ አካባቢ የተከፈተው ዞማ ሙዚየም ናቸው::

ከአዲስ አበባ በመቀጠል በፔሩ፣ ዩናይትድ ስቴትስ፣ ኦስትሪያና ሜክሲኮ የሚገኙ የተረለያዩ ስፍራዎች ከሁለት እስከ አምስት ደረጃን ይዘዋል።

ድረገፁ እነዚህን የዓለማችንን ሊጎበኙ የሚገባቸው ስፍራዎች ብሎ የዘረዘራቸውን አካባቢዎች ሲመርጥ፥ የተለያዩ ጸሁፎችን፣ የቱሪዝም ስታትስቲክስን፣ ዋና ዋና ክስተቶችን ፣ አዳዲስ የበረራ መንገድ ሰንጠረዦችን እና የሆቴል አገልግሎትን በማጥናት መሆኑን ጠቁሟል።

ሰበር መረጃ!እንኳን ደስ አለሽ ኢትዮጵያዬ ዩኔስኮ የጥምቀት በአላችንን "የማይዳሰሱ የአለም ቅርሶች" መዝገብ ውስጥ እንዳሰፈረ አስታውቋል!እንኳን ደስ አለን!Via eliasmeseret
12/12/2019

ሰበር መረጃ!
እንኳን ደስ አለሽ ኢትዮጵያዬ

ዩኔስኮ የጥምቀት በአላችንን "የማይዳሰሱ የአለም ቅርሶች" መዝገብ ውስጥ እንዳሰፈረ አስታውቋል!

እንኳን ደስ አለን!

Via eliasmeseret

«ኢትዮጵያ የሰው ልጆች መገኛ ናት። የመጀመሪያው ሆሞ ሴፒያን የፈለሰው ከእርስዎ [ጠ/ሚ ዐቢይ] ግዛት  ነው። በዚህም እኛ ሁላችንም ኢትዮጵያውያኖች ነን።» - የኖቤል ኮሚቴ ሊቀ መንበር ቤሪ...
10/12/2019

«ኢትዮጵያ የሰው ልጆች መገኛ ናት። የመጀመሪያው ሆሞ ሴፒያን የፈለሰው ከእርስዎ [ጠ/ሚ ዐቢይ] ግዛት ነው። በዚህም እኛ ሁላችንም ኢትዮጵያውያኖች ነን።» - የኖቤል ኮሚቴ ሊቀ መንበር ቤሪት ራይስ አንደርሰን

ታህሳስ 19 የሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤልን በዓል በቁልቢ ያክብሩ። መነሻ ቀን ታህሳስ 18 መመለሻ  ቀን ታህሳስ 20+251913765351+251900484994 አዘጋጅ  ጉዞ ኢትዮጵያ ይደዉ...
09/12/2019

ታህሳስ 19 የሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤልን በዓል በቁልቢ ያክብሩ።

መነሻ ቀን ታህሳስ 18
መመለሻ ቀን ታህሳስ 20
+251913765351
+251900484994
አዘጋጅ ጉዞ ኢትዮጵያ
ይደዉሉ ይመዝገቡ።
በቴሌግራም ይከታተላሉን
t.me/guzoethiopia

01/12/2019

ለመላዉ ኦርቶዶክሳዊያን እንኳን አደረሳችሁ።

እነሆ የዓለም ዓይኖች ሁሉ ወደ ኢትዮጵያ አነጣጥረዋል፡፡

ዓለም ሁሉ ዕይታው ኢትዮጵያ ላይ ነው፤ ከፊሎቹ በክፋት፣ ከፊሎቹ ለጥናት፣ ከፊሎቹ እውነታውን ለመረዳት፣ ሌሎቹ ደግሞ በቅናት፡፡ ‹‹አንቺ ለዓለም ብርቅ የሆንሽ፣ ለሰው ልጅ ሁሉ የተሰጠሸ ድንቅ ሚስጥር የት ነው ያለሽው?›› እያሉ ነው፡፡ ኩራት ውበቷ የሆነ፣ ለጠላት ያልተበገረች፣ ፈጣሪ በቃሉ ያጸናት አስርቱ ትዕዛዘትን ያሰፈረባትና ያሳረፈባት ኢትዮጵያ፤ ዓለም በንፍር ውኃ ጠፍታ ዳግም በኖኅ ዘር ስትለመለም ፍጥረታትም ሲበዙ፣ በፈጣሪ ዘንድ የተመረጠው ታላቁ ሙሴ ከእግዚአብሔር ጋር ይነጋገር ነበር፡፡ ሙሴ ሕዝበ እስራኤልን እንዲመራና ወተትና ማር የምታፈልቀውን ምድር ከነዓንን እንዲያወርስ የተመረጠ ነብይ እንደነበር የሃይማኖት ድርሳናት ይመሠክራሉ፡፡

እግዚአብሔር በሲና ተራራ ላይ ወረደ፤ አካባቢውም በደመና ተጋረደ፤ ፍጡር ሁሉ ፈራ ተጨነቀ ራደ፤ ሙሴ ግን ከእርሱ ጋር ይጋገር ነበር፡፡ በሲና ተራራ አናት ላይም የቃል ኪዳን ታቦት ተቀበለ፡፡ የእብራውያኑ ነብዩ ሙሴ የኢትዮጵያዊውን ካህን የዮቶርን ልጅ ሲጳራን ነበር ያገባው፡፡ ሕገ እግዚአብሔርን፣ ሥነ ምግባርና መልካም ትምህርቶችንም በሀበሻ ምድር ተምሯል፡፡

እግዚአብሔር ለሰው ልጆች ከፈጠራት ከኤዶም ገነት የሚፈስሰው ታላቁና የተቀደሰው ወንዝ ግዮን የኢትዮጵያን ምድር ይከብባል፡፡ ኢትዮጵያም በገነት ፈሳሽ ወንዞች የተከበበች፣ በእግዚአብሔር የተመረጠች ቅዱሳን የሚኖሩባት፣ ጻድቃን የሚጠጉባት ጭቁኖች የሚመኩባት፣ ትቢተኞችም የሚያፍሩባትና አደብ የሚገዙባት ቅድስት ሀገር ናት፡፡ ኢትዮጵያዊነት በዘመን እርዝማኔ፣ በቦታ መራራቅ የማይለወጥና የማይናወጥ ነው፡፡ ኢትዮጵያዊነት እንደጋሻጃግሬ የሚያስከትሉት እንደመልካም ድል የሚመኩበት ኩራትና ተድላ ነው፡፡

የእግዚአብሔር ነብይ ኤሪሚያስን ከጉድጓድ አውጥቶ ከሞት ያዳነው ኢትዮጵያዊ ጃንደረባ አቤሜሌክ ነው፡፡ ይህም ኢትዮጵያዊ ለሰው እንደሚኖር ማሳያ ነው፡፡ ኢትዮጵያዊነት ፍቅር፣ ርኅራሄ፣ ድል፣ ዕድል፣ ታማኝነትና ሕይወት ነው፡፡

‹‹ከኢትዮጵያ ወንዞች ማዶ የሚማልዱኝ የተበታተኑት ልጆቼ ቁርባኔን ያመጣሉ›› እንዳለ መጽሐፍ ቅዱስ ኢትዮጵያውን የፈጣሪን መልካም ነገር የሚቀበሉ ናቸው፡፡ ኢትዮጵያ ለጥቁር ሁሉ ማሸነፍን ያስተማረች፤ እጇቿን ወደፈጣሪዋ ዘርግታ ለዓለም ምሕረትንና ሠላምን የምትለምን ድንቅ ሀገር ናት፡፡ ኢትዮጵያ ሕገ ልቦናን፣ ሕገ ኦሪትንና ሐዲስ ኪዳንን ያስተማረች ሀገርም ናት፡፡ ዓለም ከጨለማ ባልተላቀቀባት ጊዜ ብርሃን የነበረባት ሀገር ናትም ይላሉ ሊቃውንት፡፡

የሰው ልጅ ሳይሰለጥን፣ ጥበብ በዓለም ሁሉ ሳይስፋፋ፣ ስልጣኔ በወንዞች አካባቢ ተወስኖ በነበረበት ዘመን ቀድማ የሰለጠነች፤ አስቀድማ የተጠበበች፤ ደንጋይን እንደ ጭቃ ቅርጹን ገርተው ድንቅ ኪነ ሕንጻዎችን የሚሠሩባት የብልሆች ብልህ ሀገር ነበረች፡፡ ኢትዮጵያ ቅድመ ልደት ክርስቶስ ከ1000 ሺህ ዓመት በፊት በሀገር ደረጃ የኦሪት ሕግን ተቀብላ ነበር፡፡ ፈጣሪ ያዘጋጃት፣ ሃይማኖት የተሰበከባት የፈጣሪ ሕግ ያረፈባት፣ ቅድስቲቱ ከተማ አክሱምም የመንግሥቱ መቀመጫ ነበረች፡፡

በ2550ዓ.ዓ ገዳማ የነገሠው ኢትዮጵስ አክሱማይ ሲራክ የተባለ ልጅ እንደነበረውና በዚያ ዘመን አካባቢ እንደተቆረቆረች ይገርላታል፤ አክሱም፡፡ በኢትዮጵስ ልጅ አክሱማይ ሲራክ ስም የተሰዬመች እንደሆነ ሲነገር በሌላ በኩል ደግሞ ‹አክሱም› የሚለው ቃል ‹‹ከአገውኛ የተወረሰ ነው›› ይባላል፤ ትርጉሙም ‹ውኃ ሹም› ማለት መሆኑን ያስረዳሉ፡፡ ከአክሱም ጋር የጠበቀ ቁርኝት ያለው አሁን በከተማዋ አካባቢ የሚገኘው ‹ማይሹም› የሚባለው አካባቢ ይህን ታሪክ ያጠናክረዋል፡፡

አክሱም ለኢትዮጵያውያን የብዙ ነገር መነሻ ናት፡፡ የዓለም ዓይኖች ሁሉ ወደ ኢትዮጵያ እንዲያዩ ካደረጋቸው ሚስጥር፣ ስለቀዳሚውና ስለሙሴ ጽላት በዚህ ጽሑፍ ትንሽ ለማቅረብ ወደድን፡፡ ከአባ ጴንጤሊዮን ተራራ ግርጌ ከንግሥተ ሳባ ቤተ መንግሥት አጠገብ፣ በንግሥተ ሰባ መዋኛ ገንዳ የተከበበችውና አያሌ ሚስጥራትን በውስጧ ያነገበችው አክሱም ከተማ ሚስጥርን በመያዝ የሚስተካከላት የለም፡፡ በአክሱም ከነገሡት አያሌ ነገሥታት መካከል ስሟ ከብሮና ገንኖ የሚጠራው ንግሥተ ሳባ (ማክዳ) ወይንም ንግስተ አዜብ ናት፡፡ ንግሥተ ሳባ እርሷ ነግሣበት በነበረበት ዘመን በኢየሩሳሌምም አንድ ታላቅ ንጉሥ ነግሦ ነበር፡፡ ንግሥተ ሳባ ስለ ኢየሩሳሌሙ ንጉሥ ለመጀመሪያ ጊዜ የሰማችው ታምሪን በሚባለው ነጋዴዋ አማካኝት ነበር፡፡ ‹‹የሳባም ንግሥት በእግዚአብሔር ስም የመጣላትን የሰሎሞንን ዝና በሰማች ጊዜ በእንቆቅልሽ ትፈትነው ዘንድ መጣች›› እንዲሉ መጽሐፍ ቅዱስና ክብረ ነገሥት፡፡

ታምሪን ነጋዴ ነበር፤ 520 ግመሎችና 73 መርከቦች ነበሩት፡፡ የኢየሩሳሌሙ ንጉሥ ንጉሥ ሰሎሞን ለጽላተ ሙሴ ማስቀመጫ ይሆን ዘንድ ሦስተኛ ቤተ መቅደሱን ሊሠራ ባሰበ ጊዜ ለመሥሪያ ዕቃ የሚያመጡለት ሀብታም ነጋዴዎችን ያፈላልግ ነበር፡፡ ከኢትዮጵያዊው ሀብታም ነጋዴ ከታምሪን ጋርም በዚህ ምክንያት ተገናኘ፡፡ ንጉሡም ቀዩን ወርቅ፣ ጥቁሩን የማይነቅዝ እንጨትና ሰምጴር የተባለውን ከዓረብ ሀገር ታምሪን እንዲያመጣለት አዘዘው፡፡ ታምሪንም ንጉሡ የፈለገውን ሁሉ አመጣለት፡፡ ንጉሥ ሰሎሞንም ለታምሪን የሚሻውን ሁሉ ከገንዘቡ አብልጦ ሰጠው፡፡ ብልሁ ነጋዴ ከሰሎሞን ጋር በቆዬባቸው ጊዜያት የሰሎሞንን ጥበብ ያስታውል ነበር፡፡ ወደሀገሩም በተመለሰ ጊዜ ከንጉሥ ሰሎሞን ያዬውን ሁሉ ለንግሥተ ሳባ ነገራት፡፡ ንግሥቷም ከነጋዴው በሰማችው ነገር ትደነቅና ወደ ሰሎሞንም ለመሄድ ሻተች፡፡

በመጨረሻም ከጥበቡ ለማዬትና ለመታዘብ ወደ ቅድስቲቱ ምድር ለመሄድ ቆርጣ ተነሳች፡፡ ለምንገዷ የሚያስፈለጉ፣ ለንጉሡ የሚቀርበውን ገጸ በረከት እና ለመኳንንቱና ለመሳፍንቱ የሚሰጠውን ስጦታ ሁሉ አዘጋጅታ ወደ ኢየሩሳሌም ተጓዘች፡፡ በኢየሩሳሌምም ብዙ ጥበብ ከሰሎሞን ተማረች፡፡ እርሱም ከንግሥተ ሳባ ብዙ ነገር ተመለከተ፡፡

በስጋዊ ፍቅርም ወደቁ፤ ንግሥቷም ከንጉሡ ፀነሰች፡፡ ነፍሰ ጡር ሆናም ንግሥቷ ወደ ሀገሯ ተመለሰች፤ ወለደችም፡፡ ስሙም ምኒልክ ተባለ፤ አድጎም ወደ ኢየሩሳሌም አባቱን ለመተዋወቅ ሄደ፡፡
ምኒልክ በአባቱ ዘንድ ተወደደ፤ ‹‹ይህን ልጄን በእየሩሳሌም አነግሠዋሁ›› ሲልም ንጉሥ ሰሎሞን ተሰማ፡፡ ምኒልክ ግን ከእየሩሳሌም ይልቅ በኢትዮጵያ መንገሥ እንደሚፈልግ አጥብቆ ተናገረ፤ በእስራኤላውያን በኩልም ወደ ሀገሩ እንዲመለስ ቅሬታ ይቀርብ ነበር፡፡ ጠቢቡ ሰሎሞንም መኳንንቱንና መሳፍንቱን አስጠርቶ ‹‹እነሆ አሁን የምነግራችሁን ስሙኝ፡፡ በቀኜም በግራዬም የምትቀመጡ መኳንንትና መሳፍንንት ሆይ! ልጄን ከልጆቻችሁ ጋር በኢትዮጵያ እንድናነግሠው ፍቀዱ፤ ልጆቻችሁም እንዲሁ አለቃ ሆነው በቀኝና በግራ ሆነው ይቀመጡ፤ እናንተ አማካሪዎቼ መኳንንትና መሳፍንት የበኩር ልጆቻችሁን እንሰጠው ዘንድ ፍቀዱ፤ በተወለደበት ንጉሥ ይሆናልና›› አላቸው፡፡ እነርሱም ፈቃዳቸው ሆነ፡፡

ለቅበዓ መንግሥቱን የሚጣፍጥ ሽቶ አዘጋጁ፤ ነጋሪት፣ እምቢልታ፣ እንዚራ፣መሰንቆና ከበሮ ተመታ፤ ቅድስቲቱ ከተማ በልዕልታና በደስታ ድምጽ ተመላች፡፡ ወደ ቤተመቅደሱም ውስጥ አስገቡት፡፡ በካህኑ በሳዶቅና የንጉሥ ሰለሞን የኃይል አዛዥና ካህን በሆነው በኢዮሳፍ ቅብዓ መንግሥት ተሰጠው፡፡ ከቤተ መቅደስም ወጣ፡፡ ስሙን ዳዊት ብለው ሰየሙት፡፡

ቀደማዊ ምኒልክ ከአባቱ ከሰሎሞን ጋር በኢየሩሳሌም ሦስት ዓመታትን ሲኖር በሊቀ ካህናቱ በሳዶቅ መምህርነት ሕገ ኦሪትን፣ ሕገ መንግሥትንና የእብራይስጥ ቋንቋን ተምሯል፡፡ ከንጉሡ ጋር ወደ ኢትዮጵያ እንዲሄዱ የታዘዙ የእስራኤል የበኩር ልጆችም ከሀገራቸውና ከወገናቸው ይልቁንም ከታቦተ ጽዮን ተለይቶ መሄድ እጅግ አሳዝኗቸው ነበር፡፡ የካህናቱም ልጆች ለብቻቸው ተሰባስበው ‹‹ጽዮንን እንዴት ልንተዋት እንችላለን? ለእርሷም ተሰጥተናልና ምን እናድርግ?›› ብለው ተማከሩ፡፡

የካህኑ የሳዶቅ ልጅ አዛሪያስ ‹‹ታቦተ ጽዮንን ከመንበሯ ማንም ሳያውቅብን እንውሰዳት!›› የሚል ሐሳብ አቀረበ፤ ሁሉም ተስማሙ፡፡ የቤተ መቅደሱ ቁልፍ በአዛሪያስ እጅ የነበረ በመሆኑ ማድረግ እንደሚቻልም አመኑ፡፡ የታቦተ ጽዮን ወደ ኢትዮጵያ መምጣት የእግዚአብሔር ፈቃድ እንደሆነም ይነገራል፡፡ ለአብነትም ‹‹የእግዚአብሔር መልአክ ለአዛሪያስ ደግሞ ታዬው በላዩም ላይ እንደ እሳት ምሰሶ፤ ወጣ በብርሃኑም ቤቱ ተመላ፣ አዛሪያስንም አስነስቶ ‹ቁም፣ ጽና፣ ወንድምህን ኤልማኖስን፣ አብሳን፣ መክሪምንም አንቃ፤ እነዚህን የጽላት እንጨቶች ውሰዱ፤ እኔም የቤተ መቅደሱን በሮች እከፍትልሃለሁ.፤የእግዚአብሔርንም ታቦተ ሕግ ውሰዳት፡፡ እኔም ለዘላለም ከእርሷ ጋር እንድኖርና በአያያዟም መሪ እንድሆንልህ ከእግዚአብሔር ታዝዣለሁ› አለው፡፡›› ይላሉ አበው፡፡ የተባሉትንም አደረጉ፡፡ ታቦተ ጽዮንን ከመንበሩ አንስተው ወደ አዛሪያስ ቤት አስገቧት፡፡

ቀደማዊ ምኒልክ አባቱን ተሰናብቶ ወደ ሀገሩ ሊመለስ በዝግጅት ላይ በነበረ ገዜ የነበረውን ትርምስ እንዲህ ብለው ይገልጹታል፤ ‹‹ሰረገላዎቹ ሁሉ ተጫኑ፣ አለቆዎች ሁሉ ተነሱ፣ ነጋሪት ተመታ፣ ሀገሪቱም ጮኸች፣ ጎልማሶች ደነፉ፣ግርማም ጋረዳት፣ ጸጋም ከበባት፣ የእስራኤል ጀግኖችና የመኳንንቱ ልጆች ስለተነሱ ሽማግሌዎች ዋይ ዋይ አሉ፡፡ ሕጻናት ጮሁ፤ ባልቴቶችና ደናግላንም አለቀሱ፤ በእነርሱ ምክንያት ግርማዋ ስለተወሰደባት እንጂ ሀገሪቷ የምታለቅሰው ስለእነርሱ ብቻ አይደለም፤ ታቦተ ጽዮን እንደተወሰደች በግልጽ ባያውቁም በልባቸው አልሳቱም ነበርና እግዚአብሔር የግብጽን የበኩር ልጆች በገደለ ጊዜ እንደነበረው ዓይነት መሪር ለቅሶን አለቀሱ፡፡››
ንጉሥ ሰሎሞንም በሁኔታው ደነገጠ፡፡ የሚሄዱትን ሰዎች ግርማ ባዬ ጊዜም እንባው በክብር ልብሱ ላይ እስኪንጠባጠብ ድረስ አምርሮ እንዳለቀሰ አፈ ታሪኮች ያስረዳሉ፡፡ ሰሎሞንም ምኒልክ በመሄዱ የሀገሩ ግርማ ስለተገፈፈ የበኩር ልጆችንም ይዞ ስለተንቀሳቀሰ ‹‹ክብሬ አልፋለች፤ የመመኪያዬ ዘውድም ወድቃለች፤ ሆዴም ተቃጥላለች፤ ወዮልኝ›› አለ፡፡ ከ12 ነገደ እስራኤል የተውጣጣ በጠቅላላው 12 ሺህ (አንዳንድ ድርሳናት 40 ሺህ ይላሉ) ሕዝብ ምኒልክን ተከትሎ ወደ ኢትዮጵያ መጣ፡፡

በእግዚአብሔር መልአክ መሪነትም ወደሌላኛዋ ቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ ንጉሡን ተከትለው የመጡት ካህናት ምኒልክን ‹‹ሚስጥር ትችል እንደሆነ እንገርህ›› አሉት፡፡ እርሱም ‹‹እችላለሁ እስከ ዕለተ ሞቴም አልናገርም›› አላቸው፡፡ እነርሱም ‹‹ፀሐይ ከሰማይ ወረደች፤ በሲናም ለእስራኤል ተሰጠች፡፡ ከሙሴ እስከ እሴይ ዘር ድረስ ለዓዳም ዘር ሁሉ መድኃኒት ሆነች፡፡ እነሆ በእግዚአብሔር ፈቃድ በአንተ ዘንድ ናት፤ እግዚአብሔርም አንተንና ሀገርህን ለቅድስቲቷ ለሰማይቷ ጽዮን አገልጋይ ትሆኑ ዘንድ መረጠ፡፡ የአምላክህን ትዕዛዝ ከጠበክ ለአንተም ከአንተ በኋላ ለሚመጣው ለዘርህም መሪ ትሆናለች፤ አንተ ብትሻ እርሷን ለመመለስ አትችልም፤ አባትህም ቢሻ አይችልም፤ እርሷ ወደፈቀደችበት ትሄዳለች እንጂ›› አሉት፡፡

ምኒልክ ታቦተ ጽዮንን ባዬ ጊዜም ደንግጦ ለፈጣሪው ምሥጋናን አቀረበ፡፡ ታቦተ ጽዮን መምጣቷ ሲሰማ በኢትዮጵያ ደስታ ሆነ፤ በኢየሩሳሌም ደግሞ ሐዘን ሆነ፡፡ ካህኑ ሳዶቅ ወደንጉሥ ሰሎሞን በተመለሰ ጊዜ ንጉሡ ሲተክዝ አገኘው፡፡ ንጉሡም ያስተከዘውን ለካህኑ ሳዶቅ ነገረው፡፡ ‹‹ንገሥተ ሳበ በመጣች ወቅት በሌሊት እንዲህ ዓይቼ ነበር፤ በእየሩሳሌም ዋልታ እንደቆምኩ በይሁዳ ሀገር ከሰማይ ፀሐይ ወረደች፤ እጅግም አበራች፤ ቆይታም ጠፋች፡፡ በሀገረ ኢትዮጵያ አበራች ፤ሁለተኛም ያቺ ፀሐይ ወደ አይሁድ አልተመለሰችም፡፡›› ካህኑ ሳዶቅ ይህንን እንደሰማ ደንግጦ ወደ ቤተ መቅደሱ ገሰገሰ፡፡ ወደ ቤተመቅደስም ገባ ታቦተ ጽዮን አልነበረችም፡፡ በድንጋጤ እንደበድን ሆነ፡፡ ንጉሡም በሰማም ጊዜ ተቆጣ፣ በእግዚአብሔር ፈቃድ እንደሆነም ስላወቀ አልቅሶ ዝም አለ፡፡

የእስራኤል ክብር ወደ ኢትዮጵያም መጣ፡፡ ታቦተ ጽዮንም በፈጣሪ ፈቃድ በግዮን ከምትከበበው ከቅድስቲቷ ምድር ለመቀመጥ ኢትዮጵያን መረጠች፡፡ ኢትዮጵያውያንም የዚህ ድንቅ ሚስጥር መቀመጫ እንዲሆኑ ተመረጡ፡፡ ምኒልክ እናቱን ሲያገኝ ‹እልልል› ብላ ተቀብላ አነገሠችው፡፡

ከእየሩሳሌም ከሰሎሞን ቤተ መቅደስ ወጥታ በኢትዮጵያ በምኩራብ ለብዙ ዓመታት ተቀምጣለች፡፡ ከታቦተ ጽዮን ጋር የመጡት እስራኤላውያንም በዚሁ ቀሩ፡፡ ክርስቶስ ያለው ቃል ሲደርስ በአዲስ ሕይወት አዲስ ኪዳን ተተካ፡፡ በ34 ዓ.ም በሐዋሪያው ፊሊጶስ አማካኝነት የአዲስ ኪዳን ክርስትናን ተቀበለች፡፡ በአቡነ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን አማከኝነትም ከሕገ ኦሪት ወደ ሐዲስ ኪዳን ተሸጋገረች ፡፡

አባ ሰላማ በኢትዮጵያ የተሾሙ የመጀመሪያው ጳጳስ ናቸው፡፡ የቀደመ ስማቸው ፍርሚናጦስ ነበር፡፡ አቡነ ሰላማ ቅዱሳት መጻሕፍ ከሰባ ወደ ግዕዝ እንዲተረገሙና የተስተካከለ የአጻጻፍ ስልት እንዲመጣም ታላቅ ድርሻ ነበራቸው፡፡ ኢትዮጵያን ለ15 ዓመታት ያስተዳደሩት መንትያዮቹ አብርሃ ወአጽብኃ ለመጀመሪያ ጊዜ ባለ 12 ክፍል ቤተ መቅደስ በአክሱም ሠሩ፡፡ ቤተ መቅደሱ 72 ምሰሶዎች የነበሩበት አስደናቂም ነበር፡፡ ለ14 ዓመታት ተሰርቶ ሲጠናቀቅ በአቡነ ሰላማ ተባርኮ ታቦተ ጽዮን ካረፈችበት መቅደሰ ኦሪት ወጥታ አዲስ ወደተሠራው ቤተ መቅደስ ገባች፡፡ በዓሉን ለማክበርም ከመላው ኢትዮጵያ የተውጣጣ ሕዝብ ተሰብስቦ ነበር ይባላል፡፡ በእልልታና በዝማሬም ቅዳሴ ቤቱን አከበሩ፡፡

የዓለምም ዓይን ይህን ሚስጥር ለማዬትና ለማወቅ ወደኢትዮጵያ ይመጣሉ፤ ነገር ግን ማዬት አይቻላቸውም፡፡ ኢትዮጵያም በፈጣሪ ጸናች፤ አትናወጥምም፡፡ ከታቦተ ጽዮን በኋላ በእርሷ አምሳል እየተሠራ በተለያዩ አብያ ክርስቲያናት ጽላት ይቀመጣል፡፡ አብርሃ ወአጽብኃ ያሠሩት ቤተ መቅደስ ከ600 ዓመታት በኋላ በዮዲት ጉዲት ዘመን ጠፋ፡፡ ንጉሡ አንበሳውድም ባለሰባት ቤተ መቅደስ አድርጎ ድጋሜ አሠራው፡፡ ጽዮንን ግን አስቀድመው አሸሽተዋት ስለነበረች በዮዲት ጊዜ በጠላት አልተነካችም፡፡ የንጉሡ አንበሳውድም ቤተ መቅደስ ድጋሜ በግራኝ አህመድ ዘመን ጠፋ፡፡ ንዋዬ ቅድሳቱና ታቦተ ጽዮን ግን አስቀድመው ከቦታው ተነስተው ነበርና አልተጎዱም፡፡

እስከ አጼ ፋሲለደስ ዘመነ መንግሥት ድረስም የአክሱም ቤተ መቅደስ እንደፈረሰች ቆዬች፡፡ አጼ ፋሲል የጎንደርን አብያተ መንግሥታት በሚስል ድንቅ ጥበብ ባለሦስት ቤተ መቅደስ በአክሱም አሠሩ፡፡ እርሳቸው ያሠሩት አስደናቂ ቤተ መቅደስም ዛሬ ድረስ ተውቦና አምሮ ይገኛል፡፡ በኋላም አጼ ኃይለሥላሴ በዘመናዊ አሠራር ሌላ ተጨማሪ ቤተ መቅደስ በድንቅ ሁኔታ አሠሩ፡፡ የቀደማዊ ኃይለሥላሴ ባለቤት እቴጌ መነንም ባለ አንድ ፎቅ ቤተ መቅደስ አሠሩ፡፡

ይህ ሁሉ ታሪክና ክብር ያላት ርዕሰ አድባራት ወገደማት አክሱም ጽዮን ማርያም ኅዳር 21 ቀን በየዓመቱ በታላቅ ክብር ትከብራለች፡፡ ስለምን ቢሉ ‹‹በዚህ ቀን ታቦተ ጽዮን ደራጎን የተባለውን ጣዖት የሰበረችበትን ቀን ለማሰብ፤ ቀደማዊ ምኒልክ ታቦተ ጽዮንን ይዞ አክሱም የገባበትና ንግሥተ ሳባም በደስታ ግብዣ ያደረገችበትን ለማሰብ፣ አብርሃ ወ ጽብኃ የመጀመሪያውን ባለ 12 ቤተ መቅደስ አሰርተው ታቦተ ጽዮንን ያስገቡበት ቀንም ስለሆነ ያንን ለማሰብ፣ በዮዲት የጥፋት ዘመን ጊዜ ታቦተ ጽዮንን ይዘው ወደ ዝዋይ ደሴት ተሰደው የነበሩት አባቶች የተመለሱት በኅዳር 21 ቀን ስለሆነ ያን ለማሰብና ሌሎች አያሌ ሚስጥራትን ለማድረግ ኅዳር 21 አክሱም ጽዮን ማርያም በእልልታና በዝማሬ ትከብራለች›› ይባላል፡፡

እነሆም ዛሬም አክሱም ጽዮን እየከበረች ትገኛለች፡፡ ሚስጥሩን ለማዬት የሚጓጉ የዓለም ሕዝቦች ሁሉ ወደ አክሱም ተጉዘዋል፤ ታሪኩንም ያያሉ፡፡ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ሚስጥር ነው፡፡ ለመላው የክርስትና ሃይማኖት ተከታዮች እንኳን አደረሳችሁ፡፡

‹ታቦተ ጽዮን በኢትዮጵያ› በሚል የተዘጋጀውን ዘጋቢ ፊልም፣ መጽሐፍ ቅዱስ፣ ከብረ ነገሥትና ታቦተ ጽዮንን ፍለጋ መጻሕፍትን በማጣቀሻነት ተጠቅመናል፡፡

በታርቆ ክንዴ ከአማራ ማስ ሚዲያ
ፎቶ፡- ከድረገጽ

ህዳር 21ታቦተ ፅዮንእንኳን አደረሳችሁ!በቅዱሳት መጻሕፍት ጽዮን የሚለው ቃል ተደጋግሞ በነቢያቱ ተነግሯል፡፡ ሆኖም የጽዮን ትርጉም እንደተነገረበት ዐውደ ትንቢት እንደተሰበከበት መዋዕለ ትምህ...
15/11/2019

ህዳር 21
ታቦተ ፅዮን
እንኳን አደረሳችሁ!
በቅዱሳት መጻሕፍት ጽዮን የሚለው ቃል ተደጋግሞ በነቢያቱ ተነግሯል፡፡ ሆኖም የጽዮን ትርጉም እንደተነገረበት ዐውደ ትንቢት እንደተሰበከበት መዋዕለ ትምህርት ምስጢሩ ይለያያል፡፡
በዚህ ጽሑፍ በጥቂቱ የምንመለከተው ታቦተ ጽዮን ወደ ኢትዮጵያ እንዴት እንደመጣች፣ ኅዳር 21 ቀን ስለምናከብረው ዓመታዊ በዓል፣ በታቦተ ጽዮን እና በዘመነ ሐዲስ በተገለጠችው በእመቤታችን በቅድስትድንግል ማርያም ያለውን ምስጢራዊ ትርጉም ነው፡፡ታቦት አንቺ ነሽ» ብሏል፡፡

ታቦተ ጽዮን በፈቃደ እግዚአብሔር በነቢዩ ሙሴ አማካኝነት ለሰው ልጆች ተሰጥታ እስራኤላውያን ሲባረኩባት፣ መሥዋዕታቸውን ሲያቀርቡባት ከእግዚአብሔር ሲታረቁባት ኖረዋል፡፡ከአራት ሺሕ ሦስት መቶ ሃያ ሰባት ዓመተ ዓለም (4327 ዓ.ዓ.) ጀምሮ ለአርባ ዓመታት ያህል እስራኤላውያንን በክህነት ያገለግል የነበረው ካህኑ ዔሊ ዕድሜው ሲገፋ ሁለት ልጆቹን ጠርቶ ምሉዕና ዱግ /ዋናና ምክትል/ አድርጎ ሾማቸው፡፡

በደብተራ ኦሪት ታቦተ ጽዮንን እንዲያገለግሉ የተሾሙት ሁለቱ ወጣት ካህናት /አፍኒን እና ፊንሐስ/ ፈቃደ እግዚአብሔርን ተላልፈው ሦስት ታላላቅ በደሎችን ፈጸሙ፡፡ የመጀመሪያው በደል፤ በሙሴ ሥርዓት በቀዳማይ ሰዓተ ሌሊት በርታ በቀዳማይ ሰዓተ መዓልት የምትጠፋ መብራት እንድትቀመጥ የተሠራ ሥርዓት ነበር፡፡ ሆኖም አገልግሎት ከሌለ ሲበራ ማደሩ ለምን ? ብለው መቅረዙን አነሡ፤ መብራቱንም አጠፉ፡፡ ሁለተኛ፣ ለራሳቸው ሥጋዊ ጥቅም ቅድሚያ ሰጥተው ለመሥዋዕት እንዲሆን ከመጣው እንስሳ ታርዶ ስቡ ሳይጤስ፣ደሙ ሳይፈስ ሥጋውን እየመረጡ ተመገቡ፡፡ሦስተኛ ጸሎት እናደርሳለን ሥርዓተ አምልኮ፣ እንፈጽማለን ብለው ወደ መገናኛው ድንኳን ይመጡ ከነበሩት እስራኤላውያን ቆነጃጅት ጋራ በዝሙት ወደቁ፡፡ አባታቸው ካህኑ ዔሊም የልጆቹን በደል እያየ እንዳላየ እየሰማ እንዳልሰማ ቸል በማለቱ እግዚአብሔርአዘነ፡፡ በዚህም ምክንያት ፍልስጥኤማውያንን አስነሥቶ በጦርነት ቀጣቸው፡፡

ዕብራውያን በጦርነት ውሎ ያለልማዳቸው በአሕዛብ ተሸነፉ፡፡ ሕዝበ እስራኤልም ግራ ቢገባቸው «ድል የተነሣነው ታቦተ ጽዮንን ይዘን ባለመዝመታችን ነው» ብለው አፍኒን እና ፊንሐስ ጽላቱን እንዲሸከሙ አድርገው ወደ ፍልስጥኤማውያን የጦር ምሽግ ገሠገሡ፡፡ ሆኖም ያሰቡት ሳይሳካ ታቦተ ጽዮን ተማረከች፣ አፍኒንና ፊንሐስ ሞቱ፤ ዕብራውያንም በጦርነቱ ድል ተደረጉ፡፡ፍልስጥኤማውያንም ታቦተ ጽዮንን ማርከው ዳጎን ከተባለው ጣዖታቸው ላይ አስቀመጧት፡፡ በማግስቱ ሲመለሱ ዳጎን ተገልብጦ ታቦተ ጽዮን በላይ ተቀምጣ አገኟት፡፡ በማግስቱም ተመሳሳይ ድርጊት ተፈጽሞ ዳጎን ወድቆና ተሰባብሮ አገኙት፡፡ 1ሳሙ 5÷4 ይኽን በተመለከተ ኢትዮጵያዊው ሊቅ አባ ጽጌ ድንግል ሰቆቃወ ድንግል በተባለው ድርሰቱ፤

«ታቦተ አምላከ እስራኤል ጽዮን ዘነገደት ምድረ ኢሎፍሊ፤

ወቀጥቀጠቶ ለዳጎን ነፍሳተ ብዙኃን ማህጎሊ፤

አመ ነገደት ቁስቋመ በኀይለ ወልዳ ከሃሊ፤

ወድቁ አማልክተ ግብፅ መናብርተ ሰይጣን ሐባሊ፡፡

ወተኀጉሉ ኲሎሙ ዘቦሙ አስጋሊ. . .፤

ወደ ኢሎፍሊ ምድር ተማርካ የሔደች የእስራኤል አምላክ የቃል ኪዳኑ ታቦተ ጽዮን የብዙዎችን ነፍሳት ያጠፋ ዳጎንን ሰባበረችው፡፡ ድንግል ማርያምም ሁሉን ማድረግ ከሚችለው ከልጇ ጋር ግብፅ ወደሚባል ሀገር በሔደች ጊዜ የሐሰተኛ ሰይጣን ዙፋኖች የሆኑ የግብፅ ጣዖታት ፈረሱ ጠንቋይ አስጠንቋይ ያላቸው ሁሉ ዐፈሩ» በማለት በንጽጽር አስቀምጦታል፡፡ ኢሳ 19÷1 ኃይል እና ድል ማድረጉን በዳጎን የጀመረችው ታቦተ ጽዮን የፍልስጥኤማውያንን መንደር በአባርና በቸነፈር በእባጭም መታች፡፡ ሕዝበ ፍልስጥኤምም ታቦተ ጽዮን ወደ እስራኤል ምድር እንድትመለስ አደረጉ፡፡

በእንደዚህ ዓይነት ታላቅ ክብር በሀገረ እስራኤል ትኖር የነበረችው ታቦተ ጽዮን ወደ ሀገራችን ወደ ኢትዮጵያ መምጣቷ ታላቅ የሆነ መንፈሳዊ ሐሴት እንዲሰማን ያደርጋል፡፡

የታቦተ ጽዮን ወደ ኢትዮጵያ መምጣት
ከአርባ ሁለት ጊዜ በላይ ስሟ ተደጋግሞ የተጠቀሰው ሀገር ቅድስት ኢትዮጵያ በእግዚአብሔርየተወደደች ለመሆኗ ነቢያቱ መስክረዋል፡፡ ከነቢያት አንዱ አሞፅም፤ «የእስራኤል ልጆች ሆይ ለእኔ እንደ ኢትዮጵያ ልጆች አይደላችሁምን ?» ብሎ እግዚአብሔር መናገሩን ጽፏል /9÷7/፡፡ ከሁሉም ከፍ ባለመልኩ ነቢዩ ቅዱስ ዳዊት፤ «ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች» ብሎ ሕዝበ ኢትዮጵያ እደ ሕሊናውን እና እደ ልቡናውን ዘወትር በአምልኮተ እግዚአብሔር፣ በጾምና በጸሎት፣ በምጽዋትና በትሩፋት፣ ዘርግቶ በሃይማኖት ጸንቶ፣ በምግባር ቀንቶ የሚኖር በመሆኑ፤ ሕዝቡ ሕዝበ እግዚአብሔር ምድሪቱ ሀገረ እግዚአብሔር ተብለዋል፤ /መዝ.68÷31/፡፡
ለታቦተ ጽዮን ወደ ኢትዮጵያ መምጣት ዋናው ምክንያት በእስራኤል እና በኢትዮጵያ መካከል የነበረው የሠመረ ግንኙነት ነው፡፡ ይኽም በመሆኑ የንግሥት ሳባ እና የንጉሥ ሰሎሞን ግንኙነት ሰፊውን ታሪክ ይዞ ይገኛል፡፡የንግሥተ ሳባ ዕቃ ግምጃ ቤት የነበረው ታምሪን ወደ ኢየሩሳሌም ሔዶ ንጉሥ ሰሎሞን ያሠራውን ቤተ መቅደስ ዓይቶ፣ የሰሎሞንን ጥበባዊ ዝና ሰምቶ በፍጹም መደነቅ ወደ ሀገሩ ተመለሰ፡፡ ያየውንና የሰማውን ለንግሥቲቱ አጫወታት፡፡ እሷም የሰማችውን ለማየት ወደ ኢየሩሳሌም ሔዳ የሰሎሞንን መንፈሳዊና ሥጋዊ ጥበብ ተመልክታ እግዚብሔርን አመስግና ተመለሰች፡
ከንጉሥ ሰሎሞን ምኒልክን ፀንሳ ከኢየሩሳሌም ተነሥታ ባሕረ ኤርትራን ተሻግራ፣ ሐማሴን አውራጃ ስትደርስ አሥመራ ከተማ በሚገኘው ማይበላ ከተባለው ቦታ ወንድ ልጅ ወለደች፡፡ የሕፃኑንም ስም የንጉሥ ልጅ ስትል «እብነ መለክ» አለችው፡፡ ይኽ ስም በዘመን ሒደት ምኒልክ ተብሎ ተለወጠ፡፡
ምኒልክ ተወልዶ በአእምሮ እያደገ ሲሔድ አባቴ ማን ነው ? አድራሻውስ ወዴት ነው ? እያለ ጥያቄ ቢያበዛባት በሃያ ሁለት ዓመቱ ወደ ኢየሩሳሌም ላከችው፡፡ ምኒልክም አባቱ ንጉሥ ሰሎሞንን አግኝቶ ሕገ ኦሪትንና የዕብራይስጥ ቋንቋ ሲያጠና ከቆየ በኋላ፤ ዐሥራ ሁለት ሺሕ እስራኤላውያንን አስከትሎ ከምድረ እስራኤል ወደ ኢትዮጵያ ጉዞውን አቀና፡፡
ከቀዳማዊ ምኒልክ ጋር ለጉዞ የተነሡ ዕብራውያን ከቤተሰቦቻቸው መለየታቸው ሳያሳዝናቸው ከታቦተ ጽዮን መለየታቸው እጅግ ከበዳቸው፡፡ ወዲያው በፈቃደ እግዚአብሔር ታቦተ ጽዮንን ከመንበሯ አንሥተው በሊቀ መላእክት በቅዱስ ሚካኤል መሪነት ወደ ኢትዮጵያ ገቡ፡፡
ቀዳማዊ ምኒልክ እና እስራኤላውያን ታቦተ ጽዮንን ይዘው አክሱም የደረሱት ኅዳር 21 ቀን ነበር፡፡ ንግሥተ ሳባም የታቦተ ጽዮን ወደ ኢትዮጵያ መምጣት በጣም ስላስደሰታት በክብር ተቀበለቻቸው፡፡ «ወአንበርዋ ውስተ ሕፅነ ደብረ ሀገረ ማክዳ» እንዲል በአክሱም ከተማ መካከል ደብረ ማክዳ /ዛሬ ቤተ ጊዮርጊስ ከሚባለው/ ላይ ደብተራ ኦሪት ሠርተው አስቀመጧት፡፡
አሁን ያለው ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን በዘመናዊ ዐቅድ የታነፀው የአክሱም ጽዮን ገዳም ቅዳሴ ቤቱ ጥር 30 ቀን 1957 ዓ.ም ግርማዊ ንጉሠ ነገሥት ቀዳማዊ ዐፄ ኃይለ ሥላሴ፣ ግርማዊት ንግሥት ኤልሳቤጥ /የታላቋ ብሪታንያ ንግሥት/ እና ልዑል ፊልፕ ከክብር ባለሟሎቻቸው ጋር በተገኙበት ተከብሯል፡፡

ኅዳር ጽዮን በአክሱም

አክሱም ማርያም ጽዮን በኢትዮጵያ ውስጥ ለሚገኙት አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ መሠረታቸው ስትሆን ከተማዋም የኢትዮጵያ ሥልጣኔ መነሻ ናት፡፡ አክሱም በሕገ ልቡና የጸናች፣ ሕገ ኦሪትን የፈጸመች፣ በሕገ ወንጌል ያመነች ናት፡፡ ለዚህም ነው «ሕግ ይወጽእ እምጽዮን፤ ከጽዮን ሕግ ይወጣል» የሚለው ጥቅስ የሚነገረው፡፡

በዓለ ልደትን በላሊበላ፣ ጥምቀትን በጎንደር፣ ኅዳር ጽዮንን በአክሱም ጽዮን ሲያከብሩት ልዩ የሆነ ሥርዓት ስለሚቀርብባቸው ምእመናን መንፈሳዊ ደስታ ይሰማቸዋል፡፡

ኅዳር 21 ቀን የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ በዓል ነው ብለን በተለየ መልኩ የምናከብርበት ምክንያት፡-

1. በብሉይ ኪዳን ታቦተ ጽዮን የፈጸመችውን ልዩ ልዩ ገቢረ ተአምራትን ለማሰብ

2. ቀዳማዊ ምኒልክ ከዐሥራ ሁለቱ ነገደ እስራኤል የበኲር ልጆች ጋር ሊቀ ካህናቱን አዛርያስንና ታቦተ ጽዮንን ይዞ አክሱም የደረሰበት ዕለት በመሆኑ

3. በሦስት መቶ ሠላሳ ዓመተ ምሕረት በአብርሃ ወአጽብሃ ዘመነ መንግሥት ክርስትና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሃይማኖት ይሁን ተብሎ ዐዋጅ የታወጀበት

4. ዘካርያስ በተቅዋመ ወርቅ ምሳሌ ራእይ ያየበት

5. ነቢዩ ሕዝቅኤል በተቆለፈች ቤተ መቅደስ

6. ዕዝራ በቅድስት ሀገር ምሳሌ ራእይ ያየበት

7. አብርሃና አጽብሃ በወርቅና በዕንቁ ያሠሩት ባለ አሥራ ሁለት ክፍል ቤተመቅደስ ለመጀመሪያ ጊዜ ቅዳሴ ቤቱ የተከበረበት

8. በዘጠነኛው መቶ ክፍለ ዘመን ዮዲት ጉዲት አብያተ ክርስቲያናትን ስታቃጥል ታቦተ ጸዮንን ይዘው ወደ ዝዋይ ሐይቅ ከተሰደዱ በኋላ ዘመነ ሰላም ሲጀመር አክሱም በነበሩ ካህናት አስታዋሽነት ከዝዋይ ወደ አክሱም የገባችበት ዕለት

በመሆኑ በርእሰ አድባራት ወገዳማት አክሱም ጽዮን ከፍ ባለ መንፈሳዊ በዓል እናከብራለን፡፡ ይኽ ሲባል ግን በዓሉ የሚከበረው በአክሱም ጽዮን ማርያም ብቻ ነው ማለት ሳይሆን፤ ታቦተ እግዝእትነ ማርያም ባለችበት ቦታ ሁሉ መከበሩን ልብ ማለት ያስፈልጋል፡፡ ከዚሁ ጋርም የመመኪያችን ዘውድ፣ የመዳናችን ምክንያት፣ የንጽሕናችን መሠረት ስለሆነችው እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ያልተነበየ ነቢይ፣ ያልሰበከ ሐዋርያ፣ ያልተቀኘ ባለቅኔ ከቶ የለም፡፡ኢየሱስ ክርስቶስ ከሰማየ ሰማያት ወረደ፣ በቤዛነቱ ዓለምን አዳነ፣ ዳግመኛም በክበበ ትስብእት፣ በግርማ መለኮት ለፍርድ ይመለሳል ብንል ከቅድስት ድንግል ማርያም በነሣው ሥጋ በመሆኑ ያለ ወላዲተ አምላክ ምስጢረ ሥጋዌን፣ ነገረ ድኅነትን፣ ነገረ ምጽአትን ማሰብ ከቶ የማይቻል ነው፡፡

«ዕግትዋ ለጽዮን፤ ጽዮንን ክበቧት» እንዳለ ነቢዩ፤ ዐሥርቱ ቃላት የተጻፈባትን የእስራኤል አምባና መጠጊያ የሆነችውን ታቦተ ጽዮንን ሌዋውያን ከበዋት ውዳሴ ያቀርቡላት እንደነበረው፤ ዛሬም እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ካህናትና ምእመናን ከሩቅ እና ከቅርብ ተሰብስበው በማኅሌት፣ በዝማሬ፣ በቅዳሴና በውዳሴ ያከብሯታል፡፡

በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያም እና በቃል ኪዳኑ ታቦት መካከል ጥልቅ የሆነ ምስጢራዊ ትምህርት አለ፡፡ /ዘፀ. 25÷9-20/፡፡ ይህቺ የቃል ኪዳን ታቦት በደብተራ ኦሪት በቅድስተ ቅዱሳን ውስጥ የኖረች፣ የዮርዳኖስን ባሕር የከፈለች /ኢያ. 3÷14-17/፤ ቅጽረ ኢያሪኮን ያፈረሰች /ኢያ 6÷1-21/፤ ዳጎን የተባለ የፍልስጥኤማውያንን ጣዖት የቆራረጠች /1ሳሙ 5÷1-5/፤ በድፍረት ሊነካ የሞከረውን ኦዛን የቀሰፈች /1ሳሙ 6÷6/፤ በአቢዳራ ቤት ሦስት ወር ተቀምጣ ቤቱን በበረከት የመላች /2ሳሙ 6÷12/፣ ዳዊት የዘመረላት /2ሳሙ 6÷14/፤ ጠቢቡ ሰሎሞን በቤተ መቅደስ በክብር ያኖራት/1ነገ 8÷1/፤ የእግዚአብሔር የክብር መገለጫ ናት፡፡

በታቦተ ጽዮን እና በዘመነ ሐዲስ በተገለጠችው በቅድስት ድንግል ማርያም መካከል ያለውን ረቂቅ እና ድንቅ ምስጢራዊ ንጽጽር አስመልክቶ ሦርያዊው ሊቅ ቅዱስ ኤፍሬም፤ «ታቦት በወርቅ ልቡጥ እምኩለሔ ዘግቡር እምዕፅ ዘኢይነቅዝ፤ ከማይነቅዝ እንጨት የተቀረጸ በው ስጥ በአፍአ በወርቅ የተለበጠ

እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ንጽሐ ጠባይዕ ሳያድፍባትና የቅድስና ባሕርይ ሳይጎድፍባት በማየት፣ በመስማት፣ በመዳሰሰ፣ በማሽተት አንዳችም እድፍ ጉድፍ ሳያገኛት በንጽሕናና በቅድስና ጸንታ በኃጢአት ሳትለወጥ ኖራለች፡፡ ጠቢቡ ሰሎሞንም፤ «አልብኪ ነውር ወኢምንትኒ ላዕሌኪ፤ ምክንያታዊ ነውር ኃጢአት የሌለብሽ የኃጢአት ሸታ ያልደረሰብሽ ንጽሕት በድንግልና ሥርጉት በቅድስና ክብርት በልዕልና አንቺ ነሽ» /መኃ 4÷7/ ሲል ተናግሯል፡፡

ታቦተ ጽዮን በከበረ ወርቅ እንደተሸለመች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምም በንጽሐ ሥጋ፣ በንጽሐ ነፍስ እና በንጽሐ ልቡና የተሸለመች ያጌጠች መሆኗን ያጠይቃል፡፡

ታቦተ ጽዮን የቃለ እግዚአብሔር ማደሪያ እንደሆነችው ቅድስት ድንግል ማርያምም ለአካላዊ ቃል ለእግዚአብሔር ወልድ ማደሪያ ሆናለች፡፡ ይኽንንም ቅዱስ ኤፍሬም ሲያስረዳ፤ «ኮንኪ ታቦቶ ለፈጣሬ ሰማያት ወምድር ፆርኪዮ በከርስኪ ተሰዓተ አውርኃ አንቲ ማእምንት ለዘኢያገምርዎ ሰማያት ወምድር፤ ድንግል ማርያም ሆይ ሰማይና ምድርን ለፈጠረ አምላክ ለእርሱ ማደሪያ ሆንሽ ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን በማኅፀንሸ ቻልሽው ተሸከምሽው ሰማይና ምድር የማይወስኑትን ለመወሰን የታመንሽ አንቺ ነሽ» ብሎ ተቀኝቶላታል፡፡ ስለሆነም ከብሉይ ኪዳን እስከ ሐዲስ ኪዳን እግዚአብሔር ራሱን የገለጠበትን የቸርነት በዓል እግዚአብሔርበፈቀደልን ቦታ ሆነን ስናከብር ከእኛ የሚጠበቀውን በጎ ነገር እያሰብን በተግባርም እየገለጥን ከበዓሉ ረድኤትና በረከት ተሳታፊ እንሆን ዘንድ የእግዚአብሔር ቸርነት የእናቱ የቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት አይለየን፡፡መልካም በዓል ይሁንላችሁ! ምንጭ የኔታ ቲዩብ

13/11/2019

በአክሱም ፂዮን ጉዞአችን ከምናያቸዉ ገዳማት እና አድባራት ጥቂቶቹ ፡፡
ሀ. ጥንታዊ ገዳማት እን አድባረትከተመሰረቱ 400 - 1600 ዓመት የሆናቸዉ ገዳማት እና እድባራት
1. ድብረ ብርሃን ስላሴ
2. ሀይቅ እስጢፋኖስ አብነ ኢየሱስ ሙዓ ገዳም
3. አብነ የማዕታ ገዳም
4. ደብረ ዳሞ አብነ አረጋዊ ገዳም
5. አብነ ጴንጠሊዎን ገዳም
6. አባ ሊቃኖስ ገዳም
7. ዋልድባ ስቋር ኪደነምህረት
8. ጎንደር ደብረ ብርሃን ስላሴ
9. ጎንደር ቁስቋም ማርያም
10. ጎንደር ባዕታ ለማርያም
11. ጎንደር መድኃኒዓለም
12. አባጃሌ ተክለ ሃይማኖት
13. አዘዞ ተክለ ሃይማኖት
14. ደብረ ሲና ማርያም
15. የጣራ ገዳማት
16. ወሻ እንድርያስ
17. ዛራ ቕዱስ ሚካኤል
18. አቡነ ዘራአብሮክ (ሰከላ ) የአባይ ወንዝ መነሻ ቦታ
19. አብማ ማርያም
20. ዋሻ ሚካኤል
ለ ዉቅር አብያተ ክርስቲያነት 1400 ዓመት ባላይ እድሜ ያለቸዉ
1. ቁርቁር ማርጣም
2. ቁርቁር ስላሴ
3. ጳጳሲት ማርያም
4. ስላሴ ግድም
5. እና ሌሎችም
ሐ. የጣና ገዳማት
1. ዑራ ኪዳነ ምህረት
2. ዘጌ ጊወርጊስ
3. አብነ ብተረ ማርያም
4. አዝዋ ማርያም
5. ክብራን ገብርኤል
6. እንጦንስ ኢየሱስ
7. ደብረ ማርያም
መ. ታሪካዊ ቦታች
1. የሚኒልክ መስኮት
2. የንጉስ ሚካኤል ቤተ መንግስት ደሴ
3. ዉጫሌ
4. አፄ ዮኃንስ ቤተ መንግስት መቀሌ
5. የሰማእታት ሀዉልት መቀሌ
6. አድዋ
7. የሳባ ቤተ ቤተ መንግስት
8. ማይ ሹም ዉሃ
9. የፋሲል ግንብ ጎንደር
10. አፃ ኃለስላሴ ቤተ መንግስት ባህር ዳር
11. የአባ እና ጣና መለያ ቦታ
12. ጢስ አባይ ፏፏቴ

ሰ. ሌሎች አብያተ ክርስቲያናት
ደዉሉ ይመዝገቡ
0913765351
0900484994
ቴሌ ግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ t.me/guzoethiopia
ለሌሎችም ሼር ያድረጉ
እኛን ስለመረጡ እናመሰግናለን፡፡

ዩኔስኮ ለስሜን ተራራዎች ብሔራዊ ፓርክ ልማት የሚውል 74 ሺህ የአሜሪካ ዶላር መመደቡን የፓርኩ ጽሕፈት ቤት አስታወቀ። ዓለም አቀፉ የሳይንስ፣ የትምህርት እና የባሕል ድርጅት (ዩኔስኮ) ለባ...
12/11/2019

ዩኔስኮ ለስሜን ተራራዎች ብሔራዊ ፓርክ ልማት የሚውል 74 ሺህ የአሜሪካ ዶላር መመደቡን የፓርኩ ጽሕፈት ቤት አስታወቀ። ዓለም አቀፉ የሳይንስ፣ የትምህርት እና የባሕል ድርጅት (ዩኔስኮ) ለባለሙያዎች ስልጠና እና ለቁሳቁስ ማሟያ የሚሆን 74 ሺህ የአሜሪካን ዶላር መመደቡን የስሜን ተራራዎች ብሔራዊ ፓርክ ጽሕፈት ቤት አስታውቋል፡፡

ባለፈው ዓመት ብሔራዊ ፓርኩ የእሳት ቃጠሎ ከደረሰበት የፓርኩ አካል መካከል 65 በመቶው ሳር ስለነበር በፍጥነት ማገገሙም ታውቋል፡፡ በተለይም ሳር በል ለሆኑ የፓርኩ እንስሳት ምቹ የሳር መኖ መውጣቱን ነው የስሜን ተራራዎች ብሔራዊ ፓርክ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ አበባው አዛናው የተናገሩት፡፡

የደረሰው የእሳት ቃጠሎ የከፋ የሚባል አሉታዊ ተጽዕኖ አላሳደረም፡፡ ድርጊቱ ባልታወቀ መንገድ የተፈጸመ እና ሳይንሳዊ መንገዱን ያልተከተለ መሆኑ እንጂ ቃጠሎ በሳይንሳዊ መልኩ እንደሚመከርም ተናግረዋል፡፡

ተፈጥሮ የነበረው ችግር ዳግም እንዳይፈጠር የሕዝቡን የመልካም አስተዳድር ችግሮች አስቀድሞ ለመፍታት፣ ማኅበረሰቡን በልማት እና በአካባቢጥበቃ ለማሳተፍ፣ የአካባቢውን የፀጥታ አካላት ከፓርኩ ስካውቶች ጋር በማገናኘት በየቀጠናው ጥብቅ የቁጥጥር ሥራ ለማከናወን በትኩረት እንደሚሠራም አመላክተዋል፡፡ ችግሩ በተደጋጋሚ የሚከሰትባቸውን ቦታና ጊዜ በመለዬትም 24 ሰዓት ጠበቅ ያለ ቁጥጥር እንዲደረግ ይሠራል ብለዋል አቶ አበባው፡፡

ዓለም አቀፉ የሳይንስ፣ የትምህርት እና የባሕል ድርጅት (ዩኔስኮ) ብሔራዊ ፓርኩን ውጤታማ በሆነ መልኩ ለማልማት እና ለመንከባከብ የሚያግዝ የገንዘብ ድጋፍ ማድረጉንም አስታውቀዋል፡፡ ዩኔስኮ ለባለሙያዎች ስልጠና እና ለቁሳቁስ ማሟያ የሚሆን 74 ሺህ የአሜሪካን ዶላር መድቧል ነው ያሉት፡፡

ባለሙያዎች የእሳት አደጋ በሚከሰትበት ጊዜ ውጤታማ የመቆጣጠር ሥራ ማከናወን የሚያስችል ስልጠና በኬንያ መውሰዳቸውንም አስታውቀዋል፡፡ የሰለጠኑት ባለሙያዎችም እስከ ሕዳር 20/2012 ዓ.ም ድረስ በሀገሪቱ ከሚገኙ ብሔራዊ ፓርኮች ለተውጣጡ ባለሙያዎች የአሰልጣኞች ስልጠና በደባርቅ ከተማ እንደሚሰጡ ተመላቷል፡፡ በፓርኩ አዋሳኝ አካባቢ የሚገኙ ወጣቶችም ስልጠናውን ይወስዳሉ ተብሏል፡፡

በተያያዘ ዜና በብሔራዊ ፓርኩ 38 ሺህ የሚጠጉ የተለያዩ ሀገር በቀል ችግኞች በክረምቱ ተተክለዋል፤ 25 ሺህ ሄክታር የፓርኩ መሬትም በችግኞች ተሸፍኗል፡፡

በችግኝ ተከላ ዘመቻውም የክልሉን ርዕሰ መስተዳድር ጨምሮ የክልል እና የፌደራል የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ ከክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች የተውጣጡ የማኅበረሰብ ክፍሎች፣ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች፣ የአካባቢው ማኅበረሰብ እና ሌሎችም አካላት ተሳትፈውበታል፡፡ ችግኞቹ እንክብካቤ እየተደረገላቸው መሆኑንም አቶ አበባው ነግረውናል፡፡

የአካባቢውን ወጣቶች በማሰማራትም የማረም እና የመኮትኮት ተግባራት እየተከናወነ ነው፡፡ እንደአብመድ የተተከለው ችግኝ የጽድቀት መጠን እንዲጨምር ከዘርፉ ባለሙያ ጋር ለመሥራት መታሰቡንም ነው ኃላፊው የተናገሩት፡፡

ምንጭ:- ኢፕድ

የሜርኩሪ ሽግግርዛሬ ማለትም ሰኞ ህዳር 1 ፡ 2012 ዓ.ም ከስዓት ቦኃላ ከቀኑ⏱  9:35-12:01 ማምሻ  ድረስ  #በመላው ኢትዮጵያ። ጥንቃቄ፦ ያለምንም መከላከያ ወደ ፀሀይ መመልከት እይ...
11/11/2019

የሜርኩሪ ሽግግር

ዛሬ ማለትም ሰኞ ህዳር 1 ፡ 2012 ዓ.ም
ከስዓት ቦኃላ ከቀኑ⏱ 9:35-12:01 ማምሻ ድረስ #በመላው ኢትዮጵያ።

ጥንቃቄ፦ ያለምንም መከላከያ ወደ ፀሀይ መመልከት እይታን ያሳጣል❗️

የሜርኩሪ ሽግግር ሂደት

፩) ከፊል ሽግግር የሚጀምረው ልክ ከቀኑ 9:35 ስሆን ሜሪኩሪ በፀሀይ ጤርዝ አከባቢ ትታያለች።

፪) ሙሉ ሽግግር የሚጀምረው ልክ ከቀኑ 9:36 ስሆን ሜሪኩሪ ከፀሀይ ጤርዝ አከባቢ ፈቀቅ ብላ የፀሃይ ክበብ(Circle) ዉስጥ ትገባለች። በዝህ ጊዜ ሜሪኩሪ እንደ ጥኩር ነጥብ በፀሀይ ድስክ ውስጥ ትታያለች።

፫) ከአድስ አበባ ስትታይ ሜሪኩሪ የፀሃይ ማዕከል (Center) ላይ የምትደርሰው ልክ 11:58 ስሆን ነዉ። ለጥቆማ ያህል በዝህ ሰዐት ለዕይታ ግልጽ እንድሆን ወደ ምዕራብ-ደቡባዊ ምዕራብ ወይም ከፍታ ቦታዎች ቢወጡ ይመከራል ምክንያቱም ፀሀይ ወደ አድማስ እየተጠጋች ስለሆነ።

፬) 12:00 ከፀሀይ መጥለቅ ጋር የሜሪኩሪ ሽግግር በአዲስ አበባ ሰማይ ላይ ይታያል። ፀሀይ ወደ አድማስ እየተጠጋች ስለሆነ ለዕይታ ግልጽ እንድሆን ወደ ምዕራብ-ደቡባዊ ምዕራብ ወይም ከፍታ ቦታዎች በወጡ ይመከራል።

🌑Eclipses and Mercury Transit in Addis Ababa

🌎Global Event: Mercury Transit
🇪🇹 Local Type: Mercury Transit, in Addis Ababa
⏱Begins: Mon, 11 Nov 2019, 15:35
⏱Midpoint: Mon, 11 Nov 2019, 17:58
⏱Ends: Mon, 11 Nov 2019, 18:01
⏳Duration: 2 hours, 26 minutes


&Inspiration

በጉዞ ኢትዮጵያ ይጓዙ!!!በጉዞአችን ጥንታዊ እና ታሪካዊ የሆኑ ገዳማትን ፣ አድባራትን ፣ ዉቅር አብያተክርስቲያናትን እና የጣና ገዳማትን ይሳለማሉ በረከትንም ያገኛሉ። በተጨማሪም የሀገራችን ...
07/11/2019

በጉዞ ኢትዮጵያ ይጓዙ!!!
በጉዞአችን ጥንታዊ እና ታሪካዊ የሆኑ ገዳማትን ፣ አድባራትን ፣ ዉቅር አብያተክርስቲያናትን እና የጣና ገዳማትን ይሳለማሉ በረከትንም ያገኛሉ።
በተጨማሪም የሀገራችን አኩሪ የሆኑ ታሪካዊ ቦታዎች ፣ቤተ መንግስቶች እና ጥንታዊ ሀዉልቶችን ይጎበኛሉ ።
ይደዉሉ ይመዝገቡ
+251913765351
+251900484994
t.me/guzoethiopia ቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
https://www.facebook.com/ጉዞ-ኢትዮጵያ-Guzo-Ethiopia-105371294166167/ ፌስቡክ ፔጃችንን ላይክ ያድርጉ
በፈለጉት አማራጭ ያገኙናል ለጉዞ ፍላጎት ጉዞ ኢትዮጵያ ይመልስልዎታል።
እኛን ስለመረጡ እናመሰግናለን።

እሳቱ እየተዛመተ ነው!  | የ450 የአፍሪቃ ዝሆኖች መኖሪያ፤ ማደሪያ ብሔራዊ ፓርክ ነውየጉዞ ኢትዮጵያ የቴሌቪዥን ፕሮግራም ዋና አዘጋጅ (ብርቱ ሰዉ፤ ሌት ተቀን ለአገርና ለሕዝብ የሚታትረው...
06/11/2019

እሳቱ እየተዛመተ ነው!

| የ450 የአፍሪቃ ዝሆኖች መኖሪያ፤ ማደሪያ ብሔራዊ ፓርክ ነው

የጉዞ ኢትዮጵያ የቴሌቪዥን ፕሮግራም ዋና አዘጋጅ (ብርቱ ሰዉ፤ ሌት ተቀን ለአገርና ለሕዝብ የሚታትረው) Seyoume Hagere ጋር ደወልኩ።

" አዎን! ...የቃፍታ ሽራሮ ብሔራዊ ፓርክ እሳት እየበላው ነው" አለኝ።

የቃፍታ ሽራሮ ብሔራዊ ፓርክ ኃላፊ ቶ ዘነበ አረፋይኔ ጋር ደወልኩላቸው።

"አደባይ የምትባል ቦታ- እሳቱን ለማጥፋት ኅበረተሰቡና አመራሮች ተሰባስበን መንገድ ጀምረናል"

የተከዜ ዳርቻ፤ አረንጓዴ ደጀን፤ የብዝሃ ሕይወት ዘብ የሆነነው - ቃፍታ ሽራሮ ብሔራዊ ፓርክ እሳት እየጎበኘው።

እናንት ያገሬ ልጆች ...
ይህንን መልዕክት ሼር በማድረግ ለአገርና ለሕዝብ አድርሱ!
Viva ጌጡ ተመስገን

ህዳር 21 የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን አመታዊ ክብረ በዓልን በአክሱም ፅዮን ያክብሩ! የበረከቱ ተካፋይ ይሁኑ። በጉዞው ጥንታዊ ገዳማት፣ አድባራት  ፣ዉቅር  አብያተክርስቲያናት እና...
28/10/2019

ህዳር 21 የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን አመታዊ ክብረ በዓልን በአክሱም ፅዮን ያክብሩ! የበረከቱ ተካፋይ ይሁኑ።
በጉዞው ጥንታዊ ገዳማት፣ አድባራት ፣ዉቅር አብያተክርስቲያናት እና የጣና ገዳማትን ይሳለማሉ እንዲሁም ታሪካዊ እና ተፈጥሮአዊ ቦታዎችን ይጎበኛሉ።
ይደዉሉ ይመዝገቡ
+251913765351
+251900484994
የቴሌ ግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
t.me/guzoethiopia
የፌስቡክ ፔጃችንን ይቀላቀሉ
ስለ ጉዞ በቀላሉ መረጃ ያግኙ።
ሌሎችም ሼር ያድርጉ

የለዛ አዋርድ ተሸላሚው ጃንቦ ጆቴ _________________________(ትናንት ለኦቢኤን ቴሌቪዥን ጣብያ በአፋን ኦሮሚፋ ከሰጠው ቃለ ምልልስ ያነሳቸው ነጥቦች) + አማርኛ ቋንቋ አድጎ እ...
22/10/2019

የለዛ አዋርድ ተሸላሚው ጃንቦ ጆቴ
_________________________
(ትናንት ለኦቢኤን ቴሌቪዥን ጣብያ በአፋን ኦሮሚፋ ከሰጠው ቃለ ምልልስ ያነሳቸው ነጥቦች)

+ አማርኛ ቋንቋ አድጎ እዚህ የደረሰው በአርት (art) ነው:: አማርኛ ቋንቋን እንዲወደድ ያደረጉት ከሌላ ህብረተሰብ የወጡ አርቲስቶች ጭምር ናቸው:: ለምሳሌ ብንጠቅስ ከኦሮሞ ጥላሁን ገሰሰ ከትግራይ ፀሀዬ ዮሐንስ ከጉራጌ ማሕሙድ አህመድ ከአማራ ኤፍሬም ታምሩ እና ሌሎችም ናቸው::

+ "አማርኛ ተጭኖብን ነው" የሚባለው አስተሳሰብ ፈፅሞ ስህተት ነው:: ማንም ማንም ላይ አልጫነም:: ይሄ የተሳሳተ አረዳድ ነው:: እኛም ቋንቋችን እንዲያድግ ከፈለግንና አማረኛ ያደገበትንና የተወደደበትን መንገድ መከተልና ቋንቋችንን ማሳደግ ነው ያለብን::

+ "ቋንቋችንን ካልተናገራችሁ" ብለን በመሳሪያ ብናስገድድ ቋንቋችንን ከማሳደግ ይልቅ እንዲጠላና እንዳያድግ ነው ሚያደርገው::

+ በቁጥር 40-50 ሚሊዮን ብንሆን የትም አንደርስም:: ምንም አናመጣም:: እኛ 50% ነን ብንል ሌሎችም እኮ ተሰባስበው 50% ይሆናሉ! ከሌሎች ብሄር ብሄረሰቦች ጋር ተፋቅረን ተሳስበን ስንኖር ነው ለውጥ የምናመጣው::

+ ብዙ ነን ብለን ከዛም ከዚህም መጋጨት ለኦሮሞ ምንም የሚፈይደው ነገር የለም:: ጠላት ከማብዛት ውጭ!

+ መለወጥ ያለብን በዙ ነገሮች አሉ:: በእኛ ላይ ጥሩ አመለካከቶች የሉም:: ለኦሮሞ የሚታገሉ ድርጅቶች ብዙ ስህተት ሰርተዋል:: የኦሮሞን ህዝብ ልክ እንደ ቡልጉ (አውሬ) እንዲታይ ትልቅ ሚና ተጫውተዋል:: ይህ ነገር በቶሎ ማስተካከል አለባቸው:: ያለበለዚያ ጠላት እያበዛን ነው ምንሄደው::

+ መፎከር የሚገባው ያኔ ወያኔ አራት ኪሎ በነበረ ሰአት ነበር:: አሁን የእኛ ሰው ነው ሀገር እየመራ ያለው:: እኛ አራት ኪሎ ገብተን መፎከሩ በእኛ ላይ አያምርም!

+ ይልቅ የሚያምርብን እንደአባቶቻችን አቃፊ ብንሆን ነው:: ማሸነፍ የምንችለው በፍቅር ብቻ ነው!

በ Telegram ቻናልም ቤተሰብ ይሁኑ
https://t.me/guzoethiopia
via Yohans Mekonen

ቅዳሜን በሶደሬ ያሳልፍ በስራ የደከመ አእምሮዎን እና ሰዉነትዎን ዝና ያድርጉ። በተፈጥሮ ፍል ዉሃ ታጥበዉ በዋና ዘና ብለዉ ይመለሱ። ይደዉሉ ይመዝገቡ+ 251913765351+25190048499...
19/10/2019

ቅዳሜን በሶደሬ ያሳልፍ በስራ የደከመ አእምሮዎን እና ሰዉነትዎን ዝና ያድርጉ። በተፈጥሮ ፍል ዉሃ ታጥበዉ በዋና ዘና ብለዉ ይመለሱ።
ይደዉሉ ይመዝገቡ
+ 251913765351
+251900484994
ይቀላቀላሉ።

የምድረ ከብድ አቡነ ገብረ መንፈስቅዱስ ዉሎአችን በከፊል
17/10/2019

የምድረ ከብድ አቡነ ገብረ መንፈስቅዱስ ዉሎአችን በከፊል

 # # #  # # # *ዛሬ ደቡብ አሜሪካዊት ሀገር ወደሆነችዉ ቦሊቪያ ተጉዘን የሰማይና የምድር ድንበር ተብሎ የሚጠራዉን አስገራሚ ቦታ በወፍ በረር እንቃኛለን፡፡እንደእዉነቱ ከሆነ ሰማይና ም...
15/10/2019

# # # # # # *
ዛሬ ደቡብ አሜሪካዊት ሀገር ወደሆነችዉ ቦሊቪያ ተጉዘን የሰማይና የምድር ድንበር ተብሎ የሚጠራዉን አስገራሚ ቦታ በወፍ በረር እንቃኛለን፡፡
እንደእዉነቱ ከሆነ ሰማይና ምድር የሚገናኙበት ድንበር የላቸዉም፡፡ ነገር ግን እግር ጥሏችሁ ቦሊቪያ ወደምትባለዉ ደቡብ አሜሪካዊት ሀገር ቢሄዱ " የሰማይና የምድር
ድንበር " ወይም the border of heaven and earth በመባል የሚጠራ ከተማ ያገኛሉ፡፡
ይህ 129 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለዉ አስደናቂ ከተማ እኛ ሀገር ዉስጥ እንዳለዉ " ዳሎል "ተብሎ እንደሚጠራዉ ስፍራ ሙሉ ለሙሉ በጨዉ የተሸፈነ የጨዉ ምድር ነዉ፡፡ ነገር ግን በቦሊቪያ የሚገኘዉ የጨዉ ምድር በሌሎች የአለማችን ክፍሎች ከሚገኙት ተመሳሳይ አፈጣጠር ካላቸዉ ቦታወች የሚለየዉ አንድ ነገር አለ፡፡ እሱም ይህ ቦታ litiyem በሚባለዉ ንጥረ ነገር የበለፀገ መሆኑ ነዉ፡፡
እዚህ ጋር ነዉ እንግዲህ የዚህ ቦታ አስገራሚነት የሚጀምረዉ ማለትም ይህ ቦታ ሀገሪቷ ላይ የበጋ ወቅት በሆኑት 8 ወራቶች ላይ ለተመለከተዉ ለእይታ የማይስብ ተራ የጨዉ ምድር ቢመስልም የዝናብ ወቅት በሚሆኑት አራት ወራት ላይ ወደ አስገራሚ የምድር ላይ
ገነትነት ይለወጣል፡፡
በአጭሩ ይህ litiyum በተሰኘዉ ማእድን የበለፀገዉ የጨዉ ምድር ትንሽ ዝናብ ሲነካዉ ወደ መስታወትነት ይለወጣል፡፡ በዚህም የተነሳ ይህ ምድር እንደ መስታወት
ስለሚያንፀባርቅ ወደ ሰማይ ቀና ሲሉ ሊመለከቷቸዉ የሚችሏቸዉን ነገሮች በሙሉ ምድሩ ላይ ሊመለከቱ ይችላሉ፡፡
በዚህም ከፈጣሪ በተቸረዉ አስገራሚ የተፈጥሮ ዉበት ምክንያትነት በየአመቱ ብዙ ሺህ ቱሪስቶች ፎቶ ለመነሳት ወደዚህ ቦታ ይጎርፋሉ፡፡ ምክንያቱም ይላሉ ይህን ቦታ ለመጎብኘት እድሉን ያገኙ ቱሪስቶች " እዚህ ቦታ ላይ
ስትራመድ በሰማይ ላይ የምትራመድ ሁሉ ሊመስልህ ይችላልና ነዉ፡፡"

via omg_fact

፨፨፨፨፨  ፨፨          …       በአንድ ዙፋን :         ከእነርሱ ቀድሞ ያልታየ፤ ከራሳቸው ውጪም እስከዛሬ ማንም ያልደገመው ፤ ወደፊትም ሊሆን የማይችል አስደናቂ ጥምረት ነበ...
15/10/2019

፨፨፨፨፨ ፨፨ … በአንድ ዙፋን
:
ከእነርሱ ቀድሞ ያልታየ፤ ከራሳቸው ውጪም እስከዛሬ ማንም ያልደገመው ፤ ወደፊትም ሊሆን የማይችል አስደናቂ ጥምረት ነበራቸው። ለ30 ዓመታት በአንድ ዙፋን ላይ ተቀምጠው ኢትዮጵያን በፍቅርና ሰላም መርተዋል የዘመኑ የሥልጣኔ ቁንጮ እንድትሆንም አስችለዋል። በሃይማኖትም በኩል ጠንካሮች ነበሩና ክርስትና በሀገሪቱ ሙሉ እንዲስፋፋ አድርገው አሁን ላለንበት መሠረት ጥለዋል እራሳቸውም በጽድቅ ተመላልሰው ለቅድስና በቅተዋል።
አባታቸው #ታዜር /አይዛና/ ይባላል ንጉሠ ኢትዮጵያ ነበረ እቴጌይቱ እናታቸውም ንግስት ሶፍያ/አሕየዋ/ትባላለች።የተወለዱት በጌታችን የልደት ቀን በ312 ዓ,ም ነው። መንትያ ወንድማማቾች ሲሆኑ ቀድሞ #ኢዛና እና #ሳይዛና በኋላም ተብለው ተጠርተዋል።

እነዚህ ወንድማማቾች የሕፃንነት ጊዜያቸውን በአክሱም ቤተ መንግስት ሲያሳልፉ የኦሪትን ሕግ ከሊቀ ካህኑ አንበረም ትምህርተ ክርስትናን ደግሞ ከፍሬምናጦስ(አቡነ ሰላማ) እየተማሩ አድገዋል። ገና በ12 ዓመታቸው አባታቸው ሲሞት ሥልጣነ መንግስቱ ለጥቂት ጊዜ በእናታቸው ሲጠበቅ ቆይቱ ኋላ እነሱ ከፍ ሲሉ ተሰጣቸውና ነገሥተ ኢትዮጵያ ተብለው ሁለቱም በአንድ ዙፋን ተቀምጠው ተሾሙ።ሀገር የማስተዳደር ኃላፊነቱንም እየተባበሩ መወጣት ጀመሩ አማካሪም አስተማሪም ሆኖ ያሳደጋቸውን ፍሬምናጦስንም ወደ ግብፅ እስክንድርያ ልከው ጵጵስናን ተቀብሎ እንዲመጣ አደረጉ።አቡነ ሰላማ ተብሎ ወደ ሀገር ቤት ሲመለስም በእጁ የክርስትና ጥምቀትን ተጠመቁና አብርሃ ወ አጽብሃ ተባሉ ከዚያ ወዲያ ሀገር ከመምራቱ ጎን ለጎን በመላዋ ኢትዮጵያ በጃንደረባው ተሰብካ የነበረችውን ክርስትና አስፋፉ በአክሱም ጽዮን ማርያም ጀምረው በቁጥር እጅግ የበዙ አብያተ ክርስቲያናትን አሳነጹ።በዚህ መልኩ ለ30 ዘመን አብረው ከገዙ በኋላ ሀገር ስትሰፋ በሸዋ መንበር ዘረጉና አብርሃ በአክሱም አጽብሃ በሸዋ የረር ሆነው መምራት ጀመሩ የዛኔም እድሜያቸው 42 ነበር።ለአስር ዓመታትም ተነጣጥለው ከገዙ በኋላ አብርሃ በ52 ዓመቱ በጥቅምት 4 ቀን እረፍቱ ሆነ ወንድሙ አጽብሃም ሚስት አግብቶ አስፍሀ የሚባል ልጅ ወልዶ በ 65 ዓመቱ መንትያ ወንድሙ ባረፈባት በጥቅምት 4 ቀን አረፈ። መካነ መቃብራቸውም አሁን በስማቸው በሚጠራውና በውቅሮ ከተማ በኽልተ አውላሎ አውራጃ በገርአልታ ተራሮች ከአለት ተፈልፍሎ በተሰራው ቤተ መቅደስ ውስጥ ሆነ።ስለ ክብራቸውም እግዚአብሔር አምላክ በማይታበል ቃሉ "ስማችሁን የጠራ መታሰቢያችሁንም ያደረገውን እምርላቹሃለሁ" ሲል ቃል ኪዳን ገባላቸው። ቤተ ክርስቲያንም ቅድስናን ሰጠቻቸውና በስማቸው ታቦት ቀርፃ መዘከር ጀመረች።

★እነሆ ዛሬ የመታሰቢያቸው እለት ናትና ፈጣሪያችን ከቅዱሳኑ አባቶቾቻችን ረድኤት በረከትን ይከፈለን ሀገራችን አትዮጵያንም በአንድነቷ ይጠብቅልን።
Via dewol

Address

Adwa Street
Addis Ababa

Telephone

+251913765351

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ጉዞ ኢትዮጵያ - Guzo Ethiopia posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to ጉዞ ኢትዮጵያ - Guzo Ethiopia:

Videos

Share

Category