Konsopia

Konsopia ኢ ት ዮ ጵ ያ

ክፍል 1 ለነፍሳቸው ዕረፍት ፍትህን ለሚሹ ሁሉ!
09/09/2023

ክፍል 1
ለነፍሳቸው ዕረፍት ፍትህን ለሚሹ ሁሉ!

ህግ ማስከበር በብልፅግና ቤት - ክፍል 1 | konsopia ••• ከሰሜን ዕዝ እስከ ሸገር ፓርክ•••Zhabesha | anchor media | ems | ESAT tv |

ናሽናል ጂኦግራፊክ መጽሔት "ወርሃ ጥርንማ ወደ ኢትዮጵያ ነው፤" ብሏል፡፡***(ተጓዡ ጋዜጠኛ ሄኖክ ስዩም ~ለድሬ ቲዩብ)ጥር ዝም ብሎ ወር አይደለም፡፡ ስሜን ኢትዮጵያ ምርቱን ሰብስቦ ልጁን ...
10/01/2023

ናሽናል ጂኦግራፊክ መጽሔት
"ወርሃ ጥርንማ ወደ ኢትዮጵያ ነው፤" ብሏል፡፡
***
(ተጓዡ ጋዜጠኛ ሄኖክ ስዩም ~ለድሬ ቲዩብ)

ጥር ዝም ብሎ ወር አይደለም፡፡ ስሜን ኢትዮጵያ ምርቱን ሰብስቦ ልጁን ይድራል፡፡ ኮንሶ ዘመን ይቀይራል፡፡ ደግሞ ባስኬት አዲስ ዓመቱ ነው፤ ሾልኣ-ካሻ የተባለውን የፍስሐ በዓል ያከብራል፡፡ የማሌ ብሔረሰብ "ዶኦማ" የሚለውን ዘመን መለወጫ በዓሉን በሚያከብርበት በዚህ ወቅት ኢትዮጵያን ስለመጎብኘት የሚያትተው የናሺናል ጂኦግራፊክ መጽሔት ለዓለም ስለ ኢትዮጵያ አድርሷል፡፡

እ.ኤ.አ ዴሴምበር 7 ቀን 2022 ለህትመት የበቃው የናሺናል ጂኦግራፊክ መረጃ በወርሃ ጥር ሊጎበኙ ከሚገባቸው ሀገራት አንዷን ኢትዮጵያ አድርጓል፡፡ ዓለምን በጥር የት መሄድ እንዳለባችሁ ልንገራችሁ ያለው ይህ ዕትም አሜሪካ፣ ኢንግላንድ፣ ደቡብ ምስራቅ ቻይና፣ ስፔን እና ኢትዮጵያን በጥር ጎብኚ ብሏል፡፡

ናሽናል ጂኦግራፊ የደናኪል ዲፕሬሽን በፕላኔታችን ላይ ካሉት ደረቅ፣ ሞቃታማ እና ዝቅተኛ ቦታዎች አንዱ መሆኑን ጠቅሶ፣ በጨው ሀይቆች፣ በቢጫ አሲዳማ ምንጮች፣ በላቫ ሐይቆች እና ከአፍሪካ ንቁ በሆነው እሳተ ገሞራ በማማለል ኢትዮጵያን ጎብኙ ብሏል፡፡

ኢትዮጵያ በዚህ ወር ዝናቡ እየቀነሰ የሚሄድባት፣ ከደቡብ እስከ ራቅ ወዳለው የኦሞ ሸለቆ ድረስ በጭቃ የተሰሩ መንገዶች እንደልብ ለመጓዝ ምቹ በመሆናቸው የበርካታ የጎሳ ጎሳዎች መኖሪያ የሆኑትን ቀጠናዎች ጎብኙ ሲል ለዓለም ነግሮልናል፡፡

ናሺናል ጂኦግራፊ በኢትዮጵያ በወርሃ ጥር ከሚከበሩት የሃይማኖት በዓላት መካከል ገና እና ጥምቀትን ትኩረት አድርጎ በመላ ኢትዮጵያ የሚገኙ ኦርቶዶክሳውያን ወደ ተቀደሰ ጥምቀተ ባሕሮች በመሄድ ስለምናሳልፈው ሥርዓት ጠቁሟል፡፡ በተለይም የ17ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ታላቅ ቤተ መንግሥት ባለባት በጎንደር እና ዓለም በቅርስነት በመዘገባቸው የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት የሚደረጉ ጉዞዎችን ጠቁሟል፡፡
ናሽናል ጂኦግራፊ በዚህ ጥቆማው አያይዞ ምክር ሲል የሰሜን ኢኮ ቱር Simien Eco Tours’ እና ያሬድ አስጎብኚን Yared Tour & Travel ጠቁሟል፡፡

Address

Adwa Street
Addis Ababa
31023

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Konsopia posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category