Balehageru Tours Ethiopia

Balehageru Tours Ethiopia We focus only in a highly defined area, where our in-depth local
knowledge and expertise is unmatch
(8)

10/02/2024
የአድዋ ዜሮ ዜሮ ኪሎ ሜትር ሙዚየም ሊመረቅ  ነው የአድዋን ድልና ታሪካዊ ዳራ መነሻ አድርጎ እየተገነባ የሚገኘው አድዋ ዜሮ ዜሮ ኪሎ ሜትር ሙዚየም የኢትዮጵያ ጀግኖችንና የአድዋ መልክዓ ምድ...
10/02/2024

የአድዋ ዜሮ ዜሮ ኪሎ ሜትር ሙዚየም ሊመረቅ ነው

የአድዋን ድልና ታሪካዊ ዳራ መነሻ አድርጎ እየተገነባ የሚገኘው አድዋ ዜሮ ዜሮ ኪሎ ሜትር ሙዚየም የኢትዮጵያ ጀግኖችንና የአድዋ መልክዓ ምድርን በሚገልፅ መልኩ ታሪካዊ እሴቱን ጠብቆ ግንባታው ተጠናቆ የፊታችን እሁድ የካቲት 3 ቀን 2016 ዓ.ም ከፍ ባለ ስነስርዓት እንደሚመረቅ ተገለጸ።

ሙዚየሙ በከተማችን ውስጥ እስከዛሬ ከተገነቡ እና በመገንባት ላይ ከሚገኙ ፕሮጀክቶች ግዙፉ ሲሆን 11 ብሎኮችን የያዘ 45000 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ እየተገነባ ያለ በውስጡ የአድዋ ሰንሰለታማ ተራሮችን፣ የአድዋ ፈረሰኞች ማስታወሻ፣ ለሴት ጀግኖች ክብር የተሰየመ ማስታወሻ፣ የአንድነት ማዕከል፣ የአፍሪካ ነፃነት ማስታወሻ እንዲሁም የኢትዮጵያ ጀግኖችን ጉዞ የሚያሳይ ሙዚየም እንዲሁም ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚውሉ ከ300 እስከ 4000 ሰው ድረስ የሚይዙ የተለያዩ አዳራሾች የሚገኙበት ሲሆን ግንባታው ሙሉ ለሙሉ የተጠናቀቀ ሲሆን ከምረቃው መርሐግብር በኃላ የፊታችን ለሚከበረው የአድዋ በዓል ለአገልግሎት ክፍት የሚደረግ ይጠበቃል።
አዲስ አበባን ይጕብኙ

ኢሬቻ/ኢሬሳ !የምስጋናው በዓል   | የክረምቱ መግቢያ ሰሞን ወርሃ ሰኔ ላይ ኦሮሞዎች ወደ ተራሮች ወጥተው ለዋቃ ጉራቻ ፀሎት የማቅረብ ልምድ አላቸው። ዋቃ ጠሉን አውርዶ የመሬት ደረት በልም...
06/10/2023

ኢሬቻ/ኢሬሳ !

የምስጋናው በዓል

| የክረምቱ መግቢያ ሰሞን ወርሃ ሰኔ ላይ ኦሮሞዎች ወደ ተራሮች ወጥተው ለዋቃ ጉራቻ ፀሎት የማቅረብ ልምድ አላቸው። ዋቃ ጠሉን አውርዶ የመሬት ደረት በልምላሜ እንዲሞላ፣ ከብቶቻቸው ሳር እንዲያገኙ፣ አዝዕርቱ እንዲያብብ... ይሄም ''ደራራ'' በመባል ይታወቃል።

ከክረምቱ ማለፍና ብራ መሆን በኃላ ደግሞ ለምስጋና ወደ መልካዎች ይወርዳሉ። ክረምቱን በሰላም አሳልፎ፣ ወንዞች ጎለው የተራራቁ ዘመዳሞች ስለሚገናኙ፣ መሬት በዝናብ ረስርሳ ምርት ስለሰጠች፣ ከብቶች ጠግበው ስለቦረቁ፣ የተዘራው ሁሉ ስለያዘ።

በእጆቻቸው እርጥብ ሳር፣ አበባና የወይራ ዛፍ ዝንጣፊ ይዘው ወንዶችና ሴቶች መሬሆ፣ መሬሆ እያሉ ወደ ውሃው ይወርዳሉ። ዋቃ ፀሎታቸውን ስለሰማ ምስጋና እና አዲሱን አመት የሰላምና የመትረፍረፍ አመት እንዲያደርግ ፀሎት ያቀርባሉ።
የተጣሉ ይቅር ይባባላሉ። ዕዳ ያለበት ይሰረዝለታል። በዓሉ በአንድነትና በህብረት ይከበራል።

ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድኅን ስለ በዓሉ ትውፊት ይሄን ፅፏል፤

''.. . ከ12,000 አመታት በፊት ነው። ያኔ የኩሽ አምላክ፤ የፀሃይ እና የሰማያት አምላክ ተደርጎ የሚታሰበው አስራ ነበር። ሶስት ልጆች አሉት። ታላቁ ወንድ ልጅ ሴት ይባላል፤ ታናሹ ኦራ እና እህታቸው አሲስ። አሲስ በሌላ ስሟም አቴቴ ወይም አድባር ትባላለች።

ልጆቹ የኩሽ ህዝብ በሰፈረበት በኑቢያ እና በጥቁር ምስር (Black Egypt) ኑሮ መስርተው ይኖራሉ። ታላቁ ሴት ታናሽ ወንድሙን ኦራ በሆነ ቅራኔ ወይም ቅናት ተነሳስቶ ይገድለዋል። እህትዬው አሲስ በጊዜው ወግ (አዝና ምናልባትም አልቅሳ . . . ወይም ማቅ ለብሳ) የናይል ወንዝ አቅራቢያ ኦራን ትቀብረዋለች።

ለመታሰብያም የኦዳ ዛፍ መቃብሩ ጎን ትተክላለች። አሲስ ለገዳይም ለሟችም እህት ናትና የሁለቱ ቤተሰቦች ደም እንዳይቃቡ ትሰጋለች። (ሀዘኔ ቅጥ አጣ፤ ከቤቴም አልወጣ እያለች ሊሆን ይችላል)

አባቷን ማለትም የፀሀይን አምላክ አስራን፣ በወንድሞቿ ቤተሰቦች መሃል ሰላም እንዲያሰፍን ትለምነዋለች። አስራ የአሲስ ፀሎትን ይሰማል። ልመናዋን መስማቱን ለማሳየትም፣ ዝናብ አዝንቦ የኦዳውን ዛፍ እንደ ድንኳን ዘርግቶ ያሳድገዋል። ያለመልመዋል። ይህም እርቀ ሰላም ለማውረዱ ምልክት ይሆናታል።

በየአመቱ ለመታሰቢያ መስከረም ሲጠባ የናይል ወንዝ ይሞላል። ከወንዙ አጠገብ ለኦራ እንደ ሀውልት የተተከለው ኦዳ ዛፍም ይለመልማል። በቤተ ዘመዱ መሀል እርቀ ሰላም ለመውረዱ መታሰቢያ ይሆን ዘንድ በአል መከበር ይጀመራል።

ሰላም ያሰፈነውን የፀሀይ አምላክ ለማመስገን የሟቹ ኦራ መንፈስም አብሮ ይገኛል። (ኦራ ኦሞ . . . ኦሮሞ ይለዋል ጋሽ ፀጋዬ)

በአሉ ሲከበርም ኢዮ ካ/Eyo Ka/ እየተባለ ችቦ ተይዞ፣ የፀሀይ እና የሰማይ አምላክ ይወደሳል። ኢዮ . . . ሃ የሚለው ባህላዊ መዝሙር ከዚያ የተወረሰ ነው። ለኩሽ እንግዳ የሆነ የባዳ፣ የባዕድ አምልኮ (ክርስትናም ሆነ እስላም) ከመምጣቱ በፊት ካ (ka) ለኩሽ ህዝብ የአምላክ መጠሪያ አንድ ስም ነው።

ዛሬ ባሉት የኩሽ ህዝቦች አምላክን ዋካ(Wa Ka)፣ ዋቃ(Wa Qa) ብሎ መጥራት መነሻው ከዚያ ነው። (አካ ሱማ፣ አክሱም ይለዋል ሌላ ቦታ ጋሽ ፀጋዬ) ኢዮ ካ . . . ኢዮ ሃ፣ ሲባልም "ካ" ን ማወደስ ነው።

ገዳ (Gada -Ga ada) . . . ወይም ካ አዳ (Kada -Ka Ada) ደሞ የአምላክ ህግጋትን፣ ትእዛዛትን ማከናወን ነው። ከእነዚህም አንዱ እሬቻ ነው። አሲስ ወይም አቴቴ ወይም አድባር በተጋደሉት ወንድሞቿ ቤተሰቦች መሃል ሰላም መስፈኑን በፀሎቷ መልስ ያገኘችበት ነው።

እሬቻ በናይል ወንዝ ዳርቻ የተከለችው የኦዳ ዛፍ ለምልክት ሆኖ የለመለመበት መታሰቢያ በአል ነው። እሬቻ ይህን ሁሉ ላደረገ አምላክ ምስጋና ማቅረቢያ በአል ነው። በኦሮሞ ዘንድ በገዳ ትዕዛዛት እየተመሩ የሁሉን ፈጣሪ አንድ አምላክ ዋቃን ማምለክ ዋቄፈና(Wakefena) ይባላል።

ዋቄፈና ለኦሮሞ ሃይማኖቱ ነው። እሬቻ የእምነቱ አካል ነው። ህዝቡ ለምለም ቄጠማ፣ አረንጓዴ ቅጠል፣ አደይ አበባ ይዞ፣ ዋቃን በወንዝ ወይም በሀይቅ ዳርቻ ወይም በተራራ ላይ የማመስገን፤ የማክበር፣ የማምለክ በአል ነው።

እሬቻ የፀሎት ቀን ነው። እሬቻ ብዙ አይነት ቢሆንም ዋናዎቹ ሁለት ናቸው። እሬቻ መልካ (Irecha Melka) እና እሬቻ ቱሉ (Irecha Tullu ) እሬቻ መልካ፣ በውሃ ዳርቻ ክረምት እንደወጣ ይከበራል። ይበልጡን ምድርን በዝናብ ያጠገበውን ዋቃ በምስጋና የመዘከር በአል ነው።

እሬቻ ቱሉ፣ በተራራ ጫፍ ላይ በበጋው መሀል ይከበራል። ዝናቡ እንደ አምናው በወቅቱ እንዲመጣ ዋቃ ይለመናል። ቢሆንም ቡራኬው፣ ምስጋናው፣ ፀሎቱ በሁለቱም እሬቻ አይቀርም። ለተራራው ወይም ለወንዙ አይሰገድም።

የሚሰገደው እነርሱን ለፈጠረ፣ አምላክ ነው። በኦሮሞ ባህል ልምላሜ እና ውሃ የአምላክ መንፈስ ማደርያ፣ ንፁህ የአምልኮት ስፍራ ነው። ለፀሎት ምቹ እና ሰላማዊ ቦታ ነው።''

መልካም የምስጋና የአንድነትና የወንድማማችነት በዓል ይሁንልን!!

“BAGA AYYAANA IRREECHA NAGAAN GEESSAN`

Baga gessan, Baga geegne

ለመላው የኦሮሞ ተወላጆች እና ለስራ ባልደረቦቼ መልካም በዓል እንዲሆን እመኛለሁ
መረጃውን ከጌጡ ወስጃለሁ

ዮኔስኮ ታድሏል። የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክን በዓለም ቅርስነት መዘገበ።አንዱ ፓርክ ብዙው ዓለም፤ የዓለም ቅርስ ኾኗል።
18/09/2023

ዮኔስኮ ታድሏል። የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክን በዓለም ቅርስነት መዘገበ።
አንዱ ፓርክ ብዙው ዓለም፤
የዓለም ቅርስ ኾኗል።

13/08/2022

የቡሄ የምስራች( BUHE)ምርጥ ስራ የቡሄ ሆያ ሆየ(New music)(Hoya hoye) ሆያ ሆየየቡሄ music # buhe # Hotahoye ...

Welcome to Mother Land Ethiopia we are delighted to provide with the most friendly  and well organized trip to  Lalibela...
14/12/2021

Welcome to Mother Land Ethiopia
we are delighted to provide with the most friendly and well organized trip to Lalibela , Bahirdar and Gondar

BALEHAGERU TOURS ETHIOPIA
Festival and Hitorical tour to most popular destination in Ethiopia
Destinations: Bahir Dar, Gonder& Lalibella
Tour Name: - Balehageru Historical / Festival Tour
Mode of Transportation: Surface/Flight
Duration: 6 Days/5 Nights

Day 1 Addis Ababa to Bahir Dar (Flight)
Early in the morning, you will fly to the beautiful city Bahir dar. After check in your hotel you will take a boat trip on Lake Tana which is the largest lake in Ethiopia to visit the islands monasteries, such as Ura kidanemihiret and Azwa Mariam. You will finish the day with the spectacular sun set view over the lake. Overnight stay at Tana hotel or Hotel of your choice

Day 2 Bahir Dar
This day, you will drive to Blue Nile falls which is about 32 km downstream from the city of Bahir dar. The Blue Nile Falls is a waterfall. It is known as Tis Abay in Amharic, meaning "great smoke". It is situated on the upper course of the river. The falls are one of Ethiopia's best known tourist attractions and you will have a short hike in the area. Overnight stay at Tana hotel or Hotel of your choice

Day 3 Bahir Dar to Gondar
After breakfast, continue north to Gonder. The 180 km asphalted road will take you through rural villages, offering wonderful insight into the Amhara culture. After briefly settling in your hotel, and take lunch, you will explore the sights of Gonder including a visit to the Royal enclosure with six castles and several other buildings. Additionally, visit Fasiledes pool, still used for Timket celebration today, and debre birihan sillasie church with the most famous ceiling in Ethiopia.
Overnight stay at Goha Hotel or hotel of your choice


Day 4: Gondar to Lalibela
Early in the morning embark on a full day of driving to Lalibela. Here you will pass through several small villages, Proceed through this rural area for the stunning approach to the home of Ethiopia’s most prized destination. Overnight stay at Roha Hotel or hotel of your choice

Day 5: Discover Lalibela
The Rock hewn churches of Lalibela is said to be one the Eight of the wonder attraction in the world This day you will visit the 11 rock hewn churches of Lalibela. In the morning time you will visit the 1st and the 2nd group of the rock hewn churches that are symbolized by earthly Jerusalem and heavenly Jerusalem. And after lunch, you will visit the amazing and the only 3rd group of rock hewn church and the symbolized of arc of Noah that is called St. George.
Dinner will be held at well know cultural restaurant and overnight stay at Hotel of your Choice

Day 6: Lalibela – Addis Ababa / Flight
This day in the morning after having breakfast will drive to the Airport for your departure to Addis Ababa, in the afternoon after lunch we will visit the National palace of Ethiopia and Entoto Mountain. Overnight you will have dinner invitation at checheho cultural restaurant with folkloristic dances then you will be transferred to the airport for departure.

NB: This program can be amended based on your time and budget!!
# discover Ethiopia with Balehageru tours for your best experience
Website: balehagerutoursethiopia.com
Email: [email protected]
Mob:+251987868686 / +251920491004
You can reach us on whats app and Telegram

Address

Piyasa Tayitu Hotel 0911434066
Addis Ababa
21297ADDISABABA

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Balehageru Tours Ethiopia posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Balehageru Tours Ethiopia:

Videos

Share

Category