Abenet Higher Clinic

Abenet Higher Clinic Abenet Higher Clinic is a privately owned medical center with 15 plus years of medical service experience.

We are dedicated in achieving excellence in health with low price that centralizes the whole population.

ቃርያን የመመገብ የጤና ጥቅሞችቃርያ አብዛኛውን ጊዜ ምግብን ለማጣፈጥ የምንጠቀምበት ሲሆን እንደሃገራችን ባሉ ቅመማ ቅመም የበዛባቸው ምግቦችን በሚመገቡ ሀገራትም ይዘወተራል።ቃርያ በቫይታሚን ...
01/09/2016

ቃርያን የመመገብ የጤና ጥቅሞች

ቃርያ አብዛኛውን ጊዜ ምግብን ለማጣፈጥ የምንጠቀምበት ሲሆን እንደሃገራችን ባሉ ቅመማ ቅመም የበዛባቸው ምግቦችን በሚመገቡ ሀገራትም ይዘወተራል።
ቃርያ በቫይታሚን ሲ፣ቢ6፣ኤ፣አይረን፣ኮፐር እና ፖታሲየም የበለጸግ ነው። ከዚህም በተጨማሪ ፋይቶኑትሪየንት ማለትም ካሮቲን፣ ሉቲየን ዚያዛንቲን በውስጡ ይዟል።
✓ ቃርያን የመመገብ ጠቀሜታዎች
1. ቫይታሚን ኤ ዋነኛ ከሚባሉ ቃርያ ውስጥ ከሚገኙ ንጥረ ነገሮች ስለሆነ እና ለአይን ጥራት እና ጤናማነት ከፍተኛ ሚናን ስለሚጫወት ቃርያን መመገብ ጠቀሜታን ይሰጣል።
2. ቃርያ በቫይታሚን ሲ እጅግ የበለጸገ በመሆኑ ቆዳችንን ጤናማና የሚያበራ እንዲሆን ያደርጋል።
3. በሽታን የመከላከል አቅምን ማዳበር።
4. የምግብ መፈጨት ሂደትን ያፋጥናል።
5. ጉንፋን፣ሳል፣እንዲሁም የሳንባ ካንሰርን የመከላከል አቅም አለው።
6. ለአጥንት ጤናማነት እና ጥንካሬ እጅግ ጠቃሚም ነው።
7. ለሰውነታችን ጠቃሚ ያልሆኑ ንጥረነገሮችን በማስወገድ እና የፋይበር ምንጭ በመሆን የሆድ ድርቀትን ይከላከላል።
8. ቃርያን የሚመገቡ ሰዎች የቆዳ መሸብሸብ እንዳይኖራቸው እንዲሁም ቶሎ እንዳያረጁ ያደርጋል።

please visit our clinic.....
www.abenethigherclinic.com

22/08/2016

ከብጉር ነፃ የሆነ ቆዳ እንዲኖሮ መመገብ ያለቦዎት ምግቦች

1. በኦሜጋ ፍሬ የበለፀጉ ምግቦች
ተልባ፣ አሳ፣ ዘይት የመሳሰሉት
2. በአንቲ ኦክሲደንት የተሞሉ ምግቦች
ኢንጆሪ፣ ቦሎቄ፣ የመሳሰሉት
3. ሴሊኒየም የበለፀጉ ምግቦች
አሳ፣ ስጋ፣ ዶሮ፣ እንቁላል፣ ወይም እንጉዳይ
4. በፋይታሚን ኢ የበለፀጉ ምግቦች
አቦካዶ፣ ጎመን፣ አሳ፣ ወይራዘይት፣ ብሮክሊ
5. ብዙ የውሀ መጠን በውስጣቸው የያዙ ምግቦች
ሀብሀብ፣ ኢንጆሪ፣ አናናስ፣ ዝኩኒ፣ ቲማንቲም የመሳሰሉት
6. በፋይታሚን ኤ የበለፀጉ ምግቦች
ካሮት፣ ስኳር ዲኒች፣ አሳ፣ ማንጎ
7. ማግኒዢየም ያላቸው የምግብ አይነቶች
አሳ፣ አቦካዶ፣ ባቄላ፣ ሙዝ
ጣፋጭ የሆኑ ምግቦችን ባይመገቡ ይመከራል

19/08/2016

ቲማቲምን የመመገብ የጤና ጥቅሞች

• ቲማቲምን መመገብ ለቆዳ ጥራት ጠቃሚ ነው፡፡
ቲማቲም በውስጡ የያዘው ንጥረ ነገር ለቆዳ ተስማሚ የሆነ
ሲሆን ቲማቲምን ልጦ የልጣጩን ውስጠኛ ክፍል በፊትዎ
ላይ በመለጠፍ ለ10 ደቂቃ በማቆየት መታጠብ ንፁህና
የሚያበራ ፊት እንዲኖርዎ ያደርጋል፡፡
• ቲማቲም የተለያዩ የካንሰር ዓይነቶችን ይከላከላል
ጥናቶች እንደሚያሳዩት በቲማቲም ውስጥ የሚገኘው ሊኮፒን
የተባለ ንጥረ ነገር በፕሮስቴት ካንሰር፣የጨጓራ እና የአንጀት
ካንሰርን የመከላከል አቅም አለው፡፡
• ጠንካራ አጥንት እንዲኖረን ያደርጋል
ቲማቲም በውስጡ ካልሲየም እና ቫይታሚን ኬን የያዘ ሲሆን
ሁለቱም ንጥረ ነገሮች አጥንትአጥንት እንዲጠነክር
ያደርጋሉ።
• ቲማቲም ለልባችን ጠቀሜታም አለው
ቲማቲም በቫይታሚን ቢ እና በፖታሺየም የበለፀገ ሲሆን
ኮሌስትሮልን እና የደም ግፊትን የመቀነስ አቅምም አለው፡፡
ቲማቲምን በዕለት ተዕለት የምግብ ስርአትዎ ውስጥ
ማስገባት ከድንገተኛ የልብ ሕመም እና ኮሌስትሮል እራስዎን
ይከላከላሉ፡፡
• ለፀጉርዎ ጠቀሜታ አለው
በቲማቲም ውስጥ የሚገኘው ቫይታሚን ኤ ፀጉርዎን
ጠንካራና ያማረ እንዲሆን ያደርጋል።
• ቲማቲም ለኩላሊት ጠጠር የመጋለጥ ዕድልዎን ይቀንሳል
• ለዓይንዎ ጥራት
በቲማቲም ውስጥ የሚገኘው ቫይታሚን ኤ ለዓይንዎ ጥራት
እጅግ ጠቃሚ እንደሆነ ጥናቶች ይገልጻሉ፡፡

18/08/2016

የምግብ መመረዝ/የአንጀት ቁስለት

የምግብ መመረዝ ወይንም የአንጀት ቁስለት የምንለው
የሕመም ዓይነት የሚከሰተው በቫይረስ፣በባክቴሪያ፣እና
በፓራሳይት አማካኝነት የተበከለን ምግብ በምንመገብበት
ወቅት ነው፡፡
እነዚህ ተህዋስያን ምግብን በምናበስልበት ወቅት ሊበከሉ
ስለሚችሉ ለምንመገበው ምግብ ንፅህና ጥንቃቄ መውሰድ
ተገቢ ነው፡፡
✔ ለአንጀት ቁስለት ተጋላጭንትን የሚጨምሩ ሁኔታዎች
• በእድሜ የገፉ ሰዎች ሕመም የመከላከል አቅማቸው
እየተዳከመ ስለሚመጣ ተጋላጭ ይሆናሉ፣
• ነፍሰጡር ሴቶች ለአንጀት ቁስለት ተጋላጭነታቸው ከፍተኛ
ነው
• ሕፃናት በሽታን የመከላከል አቅማቸው ጠንካራ ስላልሆነ
በቀላሉ ለአንጀት ቁስለት ይጋለጣሉ
• ተጓዳኝ ሕመም ያለባቸው ሰዎች እንደ ስኳር ሕመም፣ጉበት
ሕመም፣ በኤድስ የተጠቁ ሕሙማን ተጋላጭነታቸው የሰፋ
ነው፡፡
✔ የአንጀት ቁስለት ምልክቶች
የምግብ መመረዝ/የአንጀት ቁስለት ሕመም ምልክቶች
የተበከለ ምግብን ከተመገብን ከሰዓታት በኋላ የሚከሰቱ
ሲሆን
• ምልክቶቹም፡- ማቅለሽለሽ
ማስመለስ
ተቅማጥ
የሆድ ቁርጠት እና ትኩሳት ናቸው፡፡ እነዚህ ምልክቶች ለቀናት
ሊቆዮ ይችላሉ፡፡
✔ ሐኪምዎን ማማከር የሚገባዎ መቼ ነው?
• በተደጋጋሚ የሚያስመልስዎ ከሆነ
• ደም የቀላቀለ ትውከት ወይንም ተቅማጥ ከኖረ
• ከ3 ቀናት በላይ የሚቆይ ተቅማጥ ከኖረ
• ከፍተኛ የሆነ የሆድ ቁርጠት ካለ
• ከፍተኛ ትኩሳት ካለዎት
• ከፍተኛ የውሃ ጥማት፣የአፍ መድረቅ፣የድካም
ስሜት፣ማዞር እና አነስተኛ የውኃ ሽንት ካለዎት ናቸው፡፡
✔ የምግብ መመረዝን ለመከላከል ምን ማድረግ
ያስፈልግናል?
• የእጅን፣ ምግብ ማብሳያን እና መመገቢያ ቁሳቁሶችን
ንፅሕና መጠበቅ
• ጥሬ /ያልበሰሉ/ ምግቦችን አለመመገብ
• ምግብዎን በፅዱ ቦታ ማስቀመጥና በተስማሚ የሙቀት
መጠን ማብሰል
• ምግብዎን ለማቆየት ከፈለጉ በማቀዝቀዣ ውስጥ
በማስቀመጥ እንዳይበከል መከላከል
• ምግብዎ የተበከለ ከመሰለዎ በአፋጣኝ ማስወገድ ተገቢ
ነው
የአንጀት ቁስለት/የምግብ መመረዝ/ ለሕፃናት፣ለነፍሰጡር
ሴቶች፣በእድሜ ለገፉ እና ተጓዳኝ ሕመም ላላቸው ሰዎች
አደገኛ እና ሕይወት እስከማጥፋት የሚያደርስ ሕመም
ስለሆነም ከላይ የተጠቀሱትን ጥንቃቄዎች መተግበር ተገቢ
ነው፡፡
የሕመም ምልክቶችም ከታየ በአፋጣኝ ወደ ሕክምና ቦታ
በመሄድ መፍትሔ ማግኘት ይገባል፡፡
እባክዎን ለወዳጆችዎ ያካፍሉ!!!

17/08/2016

ቆሎን የመመገብ የጤና ጥቅሞች

✓ ለኪንታሮት ህመም እና ለፊንጢጣ ካንሰር የመጋለጥ
እድልን ይቀንሳል
በቆሎ በፋየበር የበለፀገ ስለሆን እንደ ሆድ ድርቀት እና
ተያይዞ የሚመጣውን የኪንታሮት ህመም ተጋላጭነት
በእጅጉ ይቀንሳል።
✓ ለሰውነታችን ጠቃሚ የሆኑ ንጥረ ነገሮችን ይዟል
እንደ ፎስፈረስ ለአጥንት ጥንካሬና እድገት ጠቀሜታ ያለው
እና ማግኒዚየም ለልብ እንዲሁም ለአጥንት ጥንካሬ
የሚጠቅሙ ንጥረነገሮች አሉት።
✓ የኮሌስቴሮል መጠንን ይቀንሳል
በቆሎ መጥፎ የምንለውን የኮሌስቴሮል አይነት እንዲቀንስ
የሚያደርግ ሲሆን ይህም ከልብ ህመም እና ሌሎች
ከኮሌስቴሮል መጠን መጨመር ጋር ተያያዥነት ባላቸው
በሽታዎች እንዳንጠቃ ያደርጋል።
✓ የቫይታሚን ምንጭ ነው
በቆሎ በቫይታሚን ቢ የበለፀገ ስለሆነ በተለየም ታያሚን
ለነርቭ ጤናማነት ወሳኝ ሚናን ይጫወታል።
✓ የበቆሎ አንቲኦክስደንት ባህርይ ስላለው ካንሰርን
የመከላከል አቅም እንዳለው ጥናቶች ያሳያሉ።

17/08/2016

የአስም ህመም

የአስም በሽታ ሳንባችንን የሚጎዳ የህመም አይነት ሲሆን በዓለማችን ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የበሽታው ተጠቂዎች ይገኛሉ፡፡
የአስም ህመም በአብዛኛው ከልጅነት ጀምሮ በመከሰት ደረጃ በደረጃ እያደገ የሚሄድ የመተንፈሻ አካል ህመም ቢሆንም አልፎ አልፎም ቢሆን እድሜ ከገፋ በኋላም የሚጀምር የህመም አይነት ነው፡፡
ለአስም በሽታ መከሰት ምክንያት የሚሆኑ መንስኤዎች በትክክል ያልተወቁ ሲሆን እስካሁንም ድረስ በሽታው ሙሉ በሙሉ ሊፈውስ የሚችል መድሃኒት አልተገኘም፡፡
በአብዘኛው አንድ የቤተሰብ አባል የበሽታው ተጠቂ ከሆነ በዘር የመተላለፍ ባህሪም አለው፡፡
የአስም በሽታ የሚያጠቃው የሳንባችንን የአየር ቧንቧዎች ሲሆን እነዚህን ቧንቧዎች በማጥበብ እና በቂ አየር ወደ ሳንባችን እንዳይገባና እና እንዳየወጣ በማድረግ እስከ ሞት ሊያደርስ ይችላል፡፡
የአስም በሽታ ምልክቶች
1. ሳል ፡- በተለይም በምሽት ግዜ የሚበረታ
2. ትንፋሽ (አየር) ማጠር
3. የደረት መጨምደድ ወይም መውጋት
4. ደረት አካባቢ በምንተነፍስበት ወቅት የሚሰማ ሲር ሲርታ (Wheezing)
የአስም በሽታን ሊቀሰቅሱ ከሚችሉ ነገሮች ውስጥ አንዳንዶቹ ከዚህ በታች ተጠቅሰዋል ነገር ግን ከሰው ሰው ሊለያዩ እንደሚችሉ መገንዘብ ያስፈላጋል፡፡
1. ሲጋራ ማጤስ
ሲጋራ ማጤስ የጤና ጠንቅ መሆኑ ይታወቃል፡፡በተለይም ለአስም በሽታ ተጠቂዎች ማጨስም ሆነ ሲጋራ የሚጤስበት አካባቢ መሆን በሽታው እንዲቀሰቅስ እና እንዲያገረሽ ያደርጋል፡፡
2. የአየር ብክለት
ከተለያዩ ፋብሪካዎች እና ተሽከርካሪዎች ከሚለቀቁ በካይ ጭሶች እና የአካባቢን አየር ከሚበክሉ ሽታዎች ካላቸው ቆሻሻዎች ተጋላጭነትን ማስወገድ አሊያም መቀነስ ያስፈልጋል፡፡
ይህ ጉዳይ በግለሰብ ደረጃ ብቻ ሳይሆን በከተማ እና በሃገር ደረጃ ሊሠራበት የሚገባ ጉዳይ ነው፡፡
3. በረሮዎች
ጥናቶች እንደሚመለክቱት ከሆነ በረሮዎች እና የሚያመነጩት ብናኝ ለአስም በሽታ መቀስቀስ ምክንያት ናቸው፡፡ በረሮዎች በአብዛኛው በቤታችን የሚገኙ እና ለጤና ጠንቅ ስለሚሆኑ ማስወገድ ተገቢ ነው፡፡
4. የቤት እንስሳት
የቤት እንስሳትን በመኖሪያ ከማኖር ይልቅ ከመኖሪያ ቤት ውጪ ቤት መስራት እና ንጽህናቸውን ጠብቆ ማኖር ያስፈልጋል፡፡
እነዚህ እንስሳት ብናኝ ስለሚኖራቸው ለአስም ህመም መቀስቀስ ምክንያት ይሆናሉ፡፡
5. ከዚህ በተጨማሪ እንደ ጉንፋን ፣ የተለያዩ የሳንባ ህመሞች (ኢንፌክሽኖች) ፣ ቅዝቃዜ ፣ የአየር ለውጥ እና የተለያዩ መኣዛ ያላቸው ሽቶዎች የአስም በሽታን ሊቀሰቅሱ እና እንዲያገረሽ ሊያደርጉ ይችላሉ፡፡
ሁሉም የአስም በሽታ ተጠቂዎች የህክምና መድሃኒት መውሰድ አይጠበቅባቸውም፡፡ የአስም በሽታን ከላይ የተዘረዘሩትን የበሽታው ቀስቃሽ የሆኑ ነገሮችን በማስወገድ እና የአካል ብቃት እንቀቅስቃሴ በማድረግ መቆጣጠር ይችላል፡፡
የአስም ህክምና መከታተል የጀመረና መድሃኒት የሚወስድ የበሽታው ተጠቂ ሃኪም በሚያዘው መንገድ መድሃኒቶቹን በአግባቡ እና በትክክል መውሰድ ይኖርበታል፡፡
ወላጆች አስም በሽታ ተጠቂ ከሆኑ ልጆች በሚወልዱበት ግዜ የህክምና ምርመራ እንዲዲርጉ እና በሃኪሞች የሚሰጡ ምክሮችን መከታተል ተገቢ ነው፡፡

16/08/2016

የፀጉር መነቃቀልን ሊያስከትሉ ከሚችሉ ምክንያቶች በጥቂቱ

*በዘር
በዘር የመጣ የፀጉር መመለጥ እጅግ የተለመደ ሲሆን ይህም የቀስ በቀስ ሂደት ያለውና እድሜ በጨመረ ቁጥር የፀጉር መመለጥ እየባስ የሚሄድ ይሆናል።
*የራዲዬሽን ህክምና
ለካንሰር እመም ተብሎ የሚደረገው የራዲዬሽን ህክምና የፀጉር መነቃቀልን ያስከትላል።
*አራስነት
አራስ የሆነች ሴት ፀጉሯን በከፍተኝ ሁኔታ ሊነቃቀል ይችላል። በእርግዝና ወቅት ወፍራምና ጤናምም የሚመስል ፀጉር ሊኖር ቢችልም የኤስትሮጅን ሆርሞን መጠን ሲቀንስ አብዛኞቹ ሴቶች የፀጉር መነቃቀል ይገጥማቸዋል። ይህ ጊዜያዊ ችግር ሲሆን የሆርሞን ሁኔታው ሲስተካክል ፀጉሩ ወደቀድሞ ይዘቱ ይመለሳል።
*የታይሮይድ ህመም
የታይሮይድ ህመም የምንለው የታይሮይድ ሆርሞን በሰውንውታችን በብዛትም ሆነ ባነሰ መጠን ሲገኝ ነው። ሁለቱም ሁኔታዎች የፀጉር ይዘትን የሚጎዱ ይሆናሉ። ነገር ግን የታይሮይድ ሆርሞን መጠኑ በህክምና ወደ ትክክለኛው መጠኑ ሲመለስ ፀጉሩም የሚመለስ ይሆናል።
*መድሃኒቶች
እንዳንድ መድሃኒቶች የፀጉር መነቃቀልን እንደተጓዳኝ ችግር ሊያስከትሉ ይችላሉ።
ይህ ከመድሃኒቱ ጋር ተያይዞ የመጣ እንደሆነ ሃኪምን አማክሮ ማወቅ ይቻላል።
እነዚህ የፀጉር መነቃቀል ምክንያቶች ከብዙዎቹ በጥቂቱ ናቸው።እያንዳንዳችን የተለያዩ ምክንያቶች ስለሚያጋጥሙን በነዚህም ሆነ በሌሎች ምክንያቶች የሚከሰት የፀጉር መነቃቀል የሚያጋጥምዎት ከሆነ ሀኪምዎን ቢያማክሩ ይመረጣል።

17/03/2016

ጨጓራ ሕመምዎን ለማስታገስ የሚጠቅሙ የጤና ምክሮች

visit our website www.abenethigherclinic.com

• ከጥጋብ በላይ አለመመገብ
• ምግብን በዝግታ መመገብ
• ቅባታማ ምግቦችን ማስወገድ
• ቅመማ ቅመም የበዛባቸውን ምግቦች አለመመገብ
• ሲጋራ ያለማጤስ
• ቡና፤አልኮል እና የለስላሳ መጠጦችን አለማዘውተር
• የሰውነት ክብደትዎን ማስተካከል
• የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ
• አዕምሮዎን ዘና በማድረግ ጭንቀትን ማስወገድ

07/03/2016

ቀረፋን የመመገብ የጤና ጥቅሞች

please visit our website

www. abenethigherclinic.com

1. በአንቲ ኦክሲደንት የበለፀገ ነው
ቀረፋ በውስጡ ያዘው አንቲ ኦክሲደንት መጠን ቶሎ የማርጀትን ሁኔታ አንደሚያዘገይ ጥናቶች ያሳያሉ፡፡
2. ለልብን ጤናማነት
ጥናቶች እንደሚሳዩት ከሆነ ቀረፋ ለልብ ሕመም ተጋላጭነትን የሚጨምሩ ሆኑታዎችን ይቀንሳል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የኮሌስትሮል መጠን እንዳይጨምርም የመከላከል አቅም አለው፡፡
3. ስኳር ሕመም
ቀረፋ የስኳር ሕመምን የመከላከል አቅም ስለአለው በደም ውስጥ የሚገኘውን የስኳር መጠን ለመቀነስ ይረዳል፡፡
4. ካንሰርን ይከላከላል
አንቲ ኦክሲደንትን በውስጡ ያዘው ቀረፋ ለካንሰር ተጋላጭነታችንን በከፍተኛ ሁኔታ ይቀንሳል፡፡
5. ኢንፌክሽንን ይከላከላል
የሰውነታችንን በሽታን የመከላከል አቅም የነበረ እንዲሆን ይረዳናል፡፡
6. ለጥርስ ጤናማነት እና ጥሩ የአፍ ጠረን
መጥፎ የአፍ ጠረን እንዳይኖረን እና በአፍ ውስጥ የሚገኙ ሕመሞችን በማድረግ ረገድ ከፍተኛ የሆነ ሚናን ይጫወታል፡፡

13/01/2016

ውሀን የመውሰድ ጠቀሜታዎቸ

www.abenethigherclinic.com

ውሃን በበቂ ሁኔታ መጠጣትና መውሰድ በርካታ ጠቀሜታዎች አሉት፤ ከእነዚህ ጠቀሜታዎቹ ጥቂቶቹ፦

ለሀይልና የአዕምሮን ሥራ ለማቀላጠፍ፦
አዕምሯችን ስራውን በሚገባ እንዲያከናውን የውሃ ድርሻ የላቀ ነው።

ከማሰብና ከማገናዘብ ጋር የተገናኙ ተግባራትን ለማከናወንም ውሃ ወሳኝ መሆኑ ነው የሚነገረው።

የተለያዩ የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎችን በምናደርግበት ወቅት ከፍተኛ መጠን ያለው ውሃ ሰውነታችን እንዲያጣ ስለምናደርግ በቂ ውሃ በየጊዜው መጠጣት ይኖርብናል።

በተጨማሪም ውሃ በአዕምሮም ሆነ በአካል ንቁ እንድንሆንም ያደርጋል።

ትኩስ ሃይል ለማግኘት፦

ሰውነት በቂ ፈሳሽ በውስጡ ሳይኖር ሲቀርና ደረቅ ሲል ድካም እና የመጫጫን ስሜት ይከሰታል። እንደ ወትሮው ነቃ ባለ ስሜትም ስራዎን ላይከውኑ ይችላሉ።

ለዚህ ደግሞ ውሃን መጠጣትና የተስተካከለ የልብ ምት ስርአት እንዲሁም የደም ዝውውር እንዲኖርዎ ማድረግ ይችላሉ።

ከዚህ ባለፈም ሰውነት የሚያስፈልገውን የኦክስጅና ሌሎች ንጥረ ነገሮች በአግባቡ እና በትክክል እንዲዘዋወሩ እና እንዲንቀሳቀሱም ያስችላል።

የኦክስጅን ዑደቱ ሲስተካከልና ሰውነት የፈለገውን የስርአት ምግብ መንሸራሸር በአግባቡ ሲከውንም የደከመውን ሰውነት ነቃ በማድረግ ስራዎን መከወን ያስችልዎታል።

ለጡንቻና መገጣጠሚያ ጤንነት እና ደህንነት፦

ውሃን በአግባቡ መጠጣት የሰውነት መጋጠሚያዎች ላይ በድርቀት ምክንያት የሚከሰትን አላስፈላጊ ጉዳት ማስወገድም ያስችላል።

በሽታን ለመከላከል፦

ሌላው ጠቀሜታው ደግሞ እንደ ጉንፋን ያሉ ቀላል በሽታዎችን መዋጋት መቻሉ ነው።

ይህም ውሃን አብዝቶ በመጠጣት የሰውነትን የሚከሰትን የቫይረስ እና ባክቴሪያ ተጋላጭነትን መቀነስ እና መከላከል ከመቻሉም በላይ፥ ከልብ ጋር የሚከሰቱ ህመሞችን መከላከልም ያስችላል።

ከዚህ ባለፈም ከአንጀት እና ከመተንፈሻ አካላት ጋር ተያያዥ የሆኑ ህመሞችን ለማከም እና ለመከላከልም ይረዳል፤ እናም ይህን ጠቀሜታውን ለማግኘት በሚጠጡት ውሃ ላይ የሎሚ ጭማቂ በመጨመር ይጠቀሙ።

ከዚህ ባለፈም የሰውነት መቆጣት እና ማበጥ እንዲሁም በባክቴሪያና በቫይረስ አማካኝነት የሚከሰቱ ህመሞችንና በሽታዎችን ለመከላከልም ሁነኛ መፍትሄ ነው።

የኩላሊት ጠጠርን ለመከላከል፦

በርካታ ውሃን መጠጣት በሰውነት ውስጥ ያሉ ጠጣር ነገሮችን በተለይም በኩላሊት ውስጥ የሚገኙትን ለማሟሟት እና በፈሳሽ መልክ ለማስወገድም ይረዳል።

የሰውነት ክብደትን ለመቆጣጠር፦

ውሃን አብዝቶ መውሰድ አሳሳቢ የጤና እክል እየሆነ የመጣውን አላስፈላጊ የሰውነት ውፍረት ለመቆጣጠር እና ለማስተካከልም ይረዳል።
ይህም የምግብ መፈጨት እና መሰልቀጥን በማስተካከልና በማዋሀድ ሰውነት በልኩ ነገሮችን እንዲከውን ይረዳዋል።

ለቆዳና ለጸጉር ደህንነት፦

ንጹህ እና በአግባቡ የሚወሰድ ውሃ ሌላው ጠቀሜታው የቆዳን ደህንነት እና ልስላሴን በመጠበቅ ማስዋብ መቻሉ ነው።
ከዚህ ባለፈም ለጤነኛ እና ለጠንካራ የጸጉር እድገትም ይረዳል።

ሰውነት በነቃ እና ዘና ባለ መንፈስ ስራውን እንዲከውን ለማድረግ እና በቀን ውሎዎ ብርታትን ለማግኘትም ውሃን አብዝተው መጠቀሙ አማራጭ መሆኑ ይነገራል።

ከዚህ ባለፈም ምናልባት በምሽት ፕሮግራም በመጠጥ ምክንያት የተጎዳና የተዳከመ ሰውነትን ሃይሉን መልሶ እንዲያገኝ እና ነቃ እንዲልም ውሃን መጠቀሙ መፍትሄ ነው።

የሚወሰደው የውሃ መጠን ቢለያይም ለአዋቂዎች በቀን ከ9 እስከ 16 አነስተኛ ብርጭቆ የውሃ መጠን መጠጣት ይመከራል።

ጠዋት ከእንቅልፍዎ በነቁ ጊዜ ከምግብ በፊት 30 ደቂቃ ቀደም ብለው በባዶ ሆድ ውሃን ቢጠጡ እነዚህን እና ሌሎች የጤና ትሩፋቶቹን ማግኘት ይችላሉ።

ውድ የአብነት ከፍተኛ ክሊኒክ ቤተሰቦች እንኳን ለገና በዓል በሰላም እና በጤና አደረሳችሁ፡፡Please visit our web site www.abenethigherclinic.com
06/01/2016

ውድ የአብነት ከፍተኛ ክሊኒክ ቤተሰቦች እንኳን ለገና በዓል በሰላም እና በጤና አደረሳችሁ፡፡

Please visit our web site www.abenethigherclinic.com

Happy Ethiopian New year...may the new year bring you happiness, love and prosperity.....
11/09/2015

Happy Ethiopian New year...may the new year bring you happiness, love and prosperity.....

31/07/2015

ነስር (Nose bleeds)

please visit our website www.benethigherclinic.com

በአፍንጫ ደም መፍሰስ (ነስር) የምንለው አስደንጋጭ የሆነ፤ነገር ግን በአብዛኛው ለከፋ አደጋ የማይዳርግ የሕመም ዓይነት ነው፡፡
ነስር በሁለት ዓይነት ይከፈላል፡፡
1) ከፊተኛው የአፍንጫችን ክፍል የሚመጣ ነስር (Anterior Nosebleeds)
• ይህ ዓይነቱ የነስር ዓይነት ከ90 በመቶ በላይ ለሚከሰት የነስር ዓይነት ምክንያት ነው፡፡ ከፍተኛው የአፍንጫችን ክፍል የሚመጣን ነስር በቀላሉ መቆጣጠር ወይንም ማቆም ይቻላል፡፡
2) ከኋለኛው የአፍንጫችን ክፍል የሚመጣ ነስር (Posterior Nosebleeds)
• ይህ ዓይነቱ የነስር ዓይንት በአብዛኘው በዕድሜ በገፉ ሰዎች ላይ የሚከሰት ሲሆን ከሌላኛው የተለየ ሕክምና የሚያስፈልገው እና ውስብስብ ነው፡፡
ነስር በአብዛኛው በቅዝቃዜ ወቅት የሚከሰት ሲሆን ከ2 - 10 ዓመትና ከ50 - 80 ዓመት ዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉትንም ያጠቃል፡፡
✔ ነስርን የሚያስከትሉ ምክንያቶች ምንድን ናቸው?
• በአፍንጫ ላይ ከውጭ የሚከሰት አደጋ ወይንም አፍንጫ በመጎርጎር ምክንያት
• በተለያዩ የሕመም ወይንም መድኃኒቶች ምክንያት ደም መርጋት አለመቻል
• የደም ግፊት መጨመር ጋር በተያያዘ የሚመጣ ነስር ነው፡፡
✔ የነስር ምልክቶች ምንድን ናቸው?
• በአብዛኛው ደም የሚፈሰው በአንደኛው የአፍንጫ ቀዳዳ ነው፡፡ ነገር ግን ከፍተኛ የሆነ የደም መፍሰስ ካለ በሁለቱም የአፍንጫ ቀዳዳዎች ደም ሊፈስ ይችላል፡፡ እጅግ ከፍተኛ ደም መፍሰስ ካለ ደግሞ በጉሮሮ አድርጎ በአፍ በኩል ሊመጣ ይችላል፡፡
• ከፍተኛ የሆነ ድም መፍሰስ ሲኖር ራስ ማዞር፣ግራ የመጋባት እና ራስ መሳት ሊያስከትል ይችላል፡፡
✔ ነስርን እንዴት ማቆም ይቻላል?
• በመጀመሪያ ራስዎን ማረጋጋት
• ቀጥ ብለው መቀመጥ
• ከጭንቅላትዎ ጎንበስ ማለት (ጭንቅላትን ወደ ላይ ቀና ማድረግ የሚፈሰውን ደም ወደ ጉሮሮ ከማምጣት ባለፈ ጥቅም የለውም)
• ሁለቱም የአፍንጫ ቀዳዳዎች በአውራ ጣትዎ እና በጠቋሚ ታትም ግጥም አድርጎ ለአስር ደቂቃ ይዞ ማቆየት
• በአፍ የሚመጣን ደም መትፋት
• ነስሩ ካቆመ በኋላ አፍንጫዎን አለመነካካት ናቸው፡፡
✔ ነስር ከተከሰተ በኋላ ወደ ሐኪም መሄድ የሚያስፈልገው መቼ ነው?
• አፍንጫዎን ለ10 ደቂቃ ያህል ይዘው ቆይተው ነስሩ የሚያቆም ካልሆነ
• በአጭር ጊዜ ልዩነት በተደጋጋሚ የሚነስርዎ ከሆነ
• ራስ ማዞር ወይንም ራስዎን የሚስቱ ከመሰለዎት
• የልብ ምትዎ የሚጨምር ከሆነ እና ለመተንፈስ ከተቸገሩ
• ደም የሚያስመልስዎ ከሆነ
• በሰውነትዎ ላይ ሽፍታ ከኖረ
• ትኩሳት ካለዎት ናቸው፡፡
✔ ሐኪምዎን ማማከር የሚያስፈልገው መቼ ነው?
• በተደጋጋሚ ነስር የሚያስቸግርዎ ከሆነ
• ከነስር ሌላ ከሌሎች የሰውነት ክፍሎች መድማት የሚኖር ከሆነ
• በቀላሉ የመበለዝ ምልክቶች በሰውነትዎ ላይ ከተገኙ
• ደምን ለማቅጠን የሚጠቅሙ መድኃኒቶችን የሚወሰዱ ከሆነ
• የደም መርጋትን የሚያስተጓጉሉ ማንኛውንም ዓይንት ሕመም ካለዎት
• የኬሞቴራፒ ሕክምና በቅርቡ ወስደው ከነበረ ነው፡፡
✔ነስርን እንዴት መከላከል ይቻላል?
• በአብዛኛው ነስር የሚከሰተው በቀዘቀዘ እና በደረቅ የአየር ንብረት ጊዜ ነው፡፡ ለነስር ተጋላጭ የሆኑ ከሆነ አፍንጫዎ እንዳይደርቅ ቫዝሊን (Petroleum jelly) በመጠቀም ማለስለስ ይችላል፡፡
• አፍንጫዎን በጣትዎ አለመነካካት
• የነስርዎ መነስዔ ከሌላ የጤና ችግር ጋር ተያያዥነት ካለው ሐኪምዎን ማማከር የሚሰጥዎን የጤና ምክር መተግበር
• ሲጋራ ማጤስ አፍንጫን በማድረቅ ለነስር ስለሚዳርግ ማስወገድ ናቸዉ፡፡
እባክዎን ለወዳጅዎ ያካፍሉ!!

30/06/2015

የአይናችንን ጤና እንጠብቅ

* በመጀመሪያ አይኖ በምን አይነት የጤና ሁኔታ ላይ እደሚገኝ ወደ ህክምና ቦታ በመሄድ ማረጋገጥ፡፡
እንደ ስኳር ህመም ባሉና ከእድሜ መግፋት ጋር ተያይዘው በሚመጡ የጤና እክሎች በአይን ውስጥ የሚፈጠረው ከፍተኛ ግፊት ምክንያት ለብርሃን ማጣጥ መንስኤ የሆኑትን የአይን ህመሞች ቅድሚያ ምልክት ስለማይሰጡ በህክምና ያረጋግጡ፡፡
* አይናችንን ሁልግዜ ማለዳ በንጹህ ውሃ መታጠብ ፡፡
ይህም የግል ንጽህናን ከመጠበቅ ባለፈ እንደ ትራኮማ ካሉ በሽታች ለመከላከል ይጠቅማል፡፡
* የክብደት መጠንዎን ይቆጣጠሩ
እንደ ሰኳር ህመም ያሉ ለዓይናችን ጤና መታወክ ምክንያት ሊሆኑ የሚችሉ በሽታዎች በክብደት መጠን መጨመር ሊከሰቱ ይችላሉና
* ጥናቶች እንደሚያመለክቱት ከሆነ እንደ ተልባ ፣ አሳ ፣ ካሮት እና ጎመን የመሳሰሉ የምግብ አይነቶችን መመገብ ለጤናችን ከፍተኛ ጠቀሜታ አለው፡፡
* አብዛኛዎቻችን ለብዙ ሰአታት በአንድ ቦታ ላይ በአትኩሮት በመመልከት ዓይኖቻችን ማሳረፍ እንዘነጋለን ነገር ግን ቢያንስ በየ 20 ደቂቃ ልዩነት ውስጥ ለ20 ሰከንዶች ያህል አይናችንን ማርገብገብና ማሳረፍ ይገባል፡፡
* ሲጋራ ማጨስን ያስወግዱ
* ዓይንዎ በጸሃይ ጨረር እንዳይጎዳ የጸሃይ መነጽር በማድረግ ይከላከሉ፡፡ (Wear UV protective sunglasses)
* የኮንታክት ሌንስ(wearing contact lenses) ተጠቃሚ ከሆኑ ከ19 ሰዓት በላይ በ አይኖ ላይ መቆየት የለበትም ስለዚህ በሚተኙበት ወቅት ማስወገድ የገባዎታል

Address

Around Abenet And Mexico
Addis Ababa
25011

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Abenet Higher Clinic posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share



You may also like