Ethiopian Hotel Professionals Association -EHPA

Ethiopian Hotel Professionals Association -EHPA This Association is unique in its kind and aims to empower it's members & contribute to the sector.
(3)

Ethiopian Hotel Professionals’ Association
EHPA Is The First And Very Unique Professional Network In Ethiopia Which Is Designed To Encourage All Hospitality Professionals To Discuss Common Issues, To Share Experiences, Communicate Opportunities, Contribute To The Sector And More,

08/11/2023
የማሰልጠኛ ኢንስቲትዩቱ ከዓለም ባንክ ጋር በመተባበር በEASTRIP ፕሮጀክት እየተከናወኑ የሚገኙ ሥራዎች ላይ ከኢንዱስትሪ ቴክኒካል አማካሪ ቦርድ ጋር ውይይት ተካሄደ፡፡የቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢ...
05/11/2023

የማሰልጠኛ ኢንስቲትዩቱ ከዓለም ባንክ ጋር በመተባበር በEASTRIP ፕሮጀክት እየተከናወኑ የሚገኙ ሥራዎች ላይ ከኢንዱስትሪ ቴክኒካል አማካሪ ቦርድ ጋር ውይይት ተካሄደ፡፡

የቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ከዓለም ባንክ ጋር በመተባበር በምስራቅ አፍሪካ የክህሎት ትራንስፎርሜሽንና ቀጣናዊ ትስስር ፕሮጀክት (EASTRIP) በ2015 በጀት ዓመት የተከናወኑ ሥራዎች ሂደትን ለመገምገምና የ2016 ዓ.ም ዕቅድ ላይ ከኢንዱስትሪ ቴክኒካል አማካሪ ቦርድ አባላት ጋር ውይይት አካሂዷል፡፡

ፕሮጀክቱ የሀገራችንን የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና መርሃ ግብሮችን ተደራሽ ለማድረግ፣ ጥራትን ለማሻሻልና ስፔሻላይዜሽንን ለማጎልበት እንደሚረዳ ዋና ዳይሬክተሩ ጨምረው ገልጸዋል፡፡

የማሰልጠኛ ኢንስቲትዩቱ የሥራ አመራርና አስተዳደር ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ገዛኸኝ አባተ በበኩላቸው ፕሮጀክቱ ስራ ላይ እንዲውል የተለያዩ ጥናታዊ ጽሁፎችን በማዘጋጀትና ሙያዊ ድጋፍ በማድረግ አስተዋጽኦ ላደረጉ የቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ባለሙያዎች፣ አሰልጣኞች፣ የኢንዱስትሪ አማካሪ ቦርድ አባላትና በዚህ ስራ ላይ ለተሰተፉ ሁሉ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

የሀገራችንን ቱሪዝም ለማሳደግ የቱሪስት መዳረሻዎችን ብቻ ማልማት በቂ ባለመሆኑ በኢንዱስትሪው ውስጥ ያለውን ብቃት ያለው የሰው ሀይል እጥረት ችግር ለመፍታት ሊሰራ ይገባል ያሉት የቴክኒካል አማካሪ ቦርዱ ሰብሳቢ አቶ መልካሙ መኮንን ፕሮጀክቱ ይህን ለመለወጥ ትልቅ መሰረት ስለሚሆን ለዕቅዱ ስኬት እንሰራለን ብለዋል፡፡

በውይይት መድረኩ ላይ የ2015 በጀት ዓመት አፈጻጸምና የ2016 ዕቅድ በማሰልጠኛ ኢንስቲትዩቱ የፕሮጀክቱ አስተባባሪ አቶ አብሃም ለገሰ የቀረበ ሲሆን በፕሮጀክቱ ማዕቀፍ የተሰሩ ሶስት የጥናት ውጤቶች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል ፡፡

ለስልጠና ፈላጊዎች በሙሉ
26/10/2023

ለስልጠና ፈላጊዎች በሙሉ

ሌጲስ ኢኮ ቱሪዝም መንደር በዓለም ድንቅ የቱሪዝም መንደርነት የእውቅና ሽልማት ማግኘቱን የቱሪዝም ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ከነጌሌ አርሲ ከተማ በስተምሥራቅ 18 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኘው የ...
19/10/2023

ሌጲስ ኢኮ ቱሪዝም መንደር በዓለም ድንቅ የቱሪዝም መንደርነት የእውቅና ሽልማት ማግኘቱን የቱሪዝም ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ከነጌሌ አርሲ ከተማ በስተምሥራቅ 18 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኘው የሌጲስ ኢኮ ቱሪዝም መንደር በዓለም ድንቅ የቱሪዝም መንደርነት በተባበሩት መንግስታት የዓለም ቱሪዝም ድርጅት እውቅና ሽልማት ተሰጥቶታል፡፡

በአስደናቂ እይታዎች፣ ፏፏቴ፣ አዕዋፋት እና የዱር እንስሳት በውስጡ የያዘው የሌጲስ ኢኮ ቱሪዝም መንደር ከቀርከሃ በሚሰሩ የእደ-ጥበብ ውጤቶች በስፋት ይታወቃል፡፡

በአካባቢው ያለው ጥብቅ ደን፣ በርካታ ዕፅዋትና እንስሳቶች፣ ድንቅ ፏፏቴ በመካከለኛው ስምጥ ሸለቆ ውስጥ የሚገኝ መሆኑ እንዲሁም በተፈጥሮ ጥበቃ ስራ እና በዕደ ጥበብ ስራዎች ጠንካራ የማህበረሰብ ክፍሎች ያሉት መሆኑ ተመራጭ እንዳደረገውም ተነግሯል፡፡

ኢትዮጵያ ከዚህ ቀደም በዓለም ድንቅ መንደርነት የጮቄ ተራራ እና የወንጪ የኢኮ ቱሪዝም መንደርን ማስመዝገቧ ይታወሳል፡

Ethiopia Land of Origins

10/10/2023

ተከፈተ !

የቱሪዝም እና ሆስፒታሊቲ ዓውደርዕይ ዛሬ በይፋ ተከፍቷል። በሳይንስ ሙዚየም የተዘጋጀው ይህ ዓውደርዕይ ላይ ሁላችሁም ተጋብዛችኋል።

ይምጡና ይጎብኙ ሀገርዎን ይወቁ !

የኢትዮጵያ ሆቴል ባለሙያዎች ማህበር።

ⓄⓃⓁⓎ ❶ Day to go ...All ready for the Exhibition & Conference to begin. Where we proudly presented the EHPA.We look forw...
09/10/2023

ⓄⓃⓁⓎ ❶ Day to go ...

All ready for the Exhibition & Conference to begin. Where we proudly presented the EHPA.

We look forward to welcoming you at our stand (booth) over the next Several days at the National Tourism and Hospitality Exhibition. 2023 at Science Museum Addis Ababa.

Picture:- Members of Professional Association those who Active Participant of the Sector.

⭐️⭐️💎💎💎⭐️⭐️⭐️⭐️💎💎⭐️⭐️⭐️⭐️💎

አንድ ቀን ብቻ ቀረው...

ነገ በይፋ ለሚከፈተው ሀገር አቀፍ የቱሪዝምና ሆስፒታሊቲ አውደርዕይ ዝግጅታችንን ጨርሰን በመጠበቅ ላይ እንገኛለን።

በአዲስአበባ ሳይንስ ሙዚየም ለሚቀጥሉት በርካታ ቀናት በሚዘጋጀው በዚህ ኹነት ላይ ተሳታፊ ሆነው እንዲጎበኙ እየጠየቅን የተለመደው ኢትዮጵያዊው መልካም የእንግዳ አቀባበል ከታላቅ አክብሮት ጋር ይጠብቃችኃል።

ምስል:- በዘርፉ ንቁ ተሳትፎ እያደረጉ የሚገኙ የሙያ ማህበራት ተወካዮች!!

📣 Exciting News! 📣We are excited to announce that the Ethiopian Hotel Professional Association will be exhibiting our to...
09/10/2023

📣 Exciting News! 📣

We are excited to announce that the Ethiopian Hotel Professional Association will be exhibiting our top-notch services at the upcoming Hospitality and Tourism Exhibition. 🏨✈️

🗓 Save the Date: October 10/2023
📍 Visit Our Booth: Science Museum

Explore our innovative offerings and join us in shaping the future of hospitality and tourism. We look forward to welcoming you at the exhibition! 🌍👥

Stay tuned for more updates as we prepare to showcase our dedication to excellence in the industry. 🎉

ምን ?ሀገር አቀፍ የቱሪዝም ሆስፒታሊቲ ፎረምና  ኤግዚቢሽን።መቼ ?ከፊታችን ማክሰኞ መስከረም 29 እስከ ጥቅምት -28/2016 ዓ.ም። የት ?በአዲስአበባ ሳይንስ ሙዚየም በድምቀት ለእይታ ክፍ...
08/10/2023

ምን ?

ሀገር አቀፍ የቱሪዝም ሆስፒታሊቲ ፎረምና ኤግዚቢሽን።

መቼ ?

ከፊታችን ማክሰኞ መስከረም 29 እስከ ጥቅምት -28/2016 ዓ.ም።

የት ?

በአዲስአበባ ሳይንስ ሙዚየም በድምቀት ለእይታ ክፍት ይሆናል።

እነማን ይሳተፋሉ ?

በሀገራችን የሚገኙ የተለያዩ የዘርፉ ባለድርሻ አካላትና ሌሎች ተቋማት ምርትና አገልግሎታቸውን ያሳያሉ፣ አዳዲስ የቴክኖሎጂ ፈጠራዎች ለእይታ ይቀርባሉ።

ይህን አውደርዕይ መጎብኘት ምን ይጠቅማል?

በዘርፉ ውስጥ የሚገኙ ትልልቅ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ የግል ሴክተር ተቋማት እንዲሁም ተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦችን በቀላሉ የማግኘት ዕድል ይፈጠራል።

የኢትዮጵያ ሆቴል ባለሙያዎች ማህበርም በአውደርዕዩ ላይ ዘርፉን በመወከል ተሳታፊ በመሆን ስለሚሰጠው አገልግሎትና ተግባራት የሚያስተዋውቅ ይሆናል።

ከነባር አባላት ባሻገር በሙያ ማህበሩ አባል ለመሆን ለሚፈልጉ አዳዲስ አባላት ምዝገባ የምናካሂድ መሆኑን እናበስራለን።

ሀገር አቀፍ የቱሪዝምና ሆስፒታሊቲ አውደርዕይ በሳይንስ ሙዚየም።

Telegram :- https://t.me/hoteliergroup
https://t.me/EHPA1

እንኳን ለኢሬቻ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!Baga Ayyaana Irreechaatiin Isin Gahe!
07/10/2023

እንኳን ለኢሬቻ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

Baga Ayyaana Irreechaatiin Isin Gahe!

መውሊድ!!!የኢትዮጵያ ሆቴል ባለሙያዎች ማህበር ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለመውሊድ በዓል በሰላም አደረሳችሁ እያለ በዓሉ የሰላምና የጤና እንዲሆን መልካም ምኞቱን ይገልፃል፡...
26/09/2023

መውሊድ!!!

የኢትዮጵያ ሆቴል ባለሙያዎች ማህበር ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለመውሊድ በዓል በሰላም አደረሳችሁ እያለ በዓሉ የሰላምና የጤና እንዲሆን መልካም ምኞቱን ይገልፃል፡፡

እንኳን አደረሳችሁ መልካም በዓል!!

የኢትዩጵያ ሆቴል ባለሙያዎች ማህበርየኢትዮጵያ የሆቴል ባለሙያዎች ማህበር ሰኔ 25 ቀን 1991ዓ.ም ህጋዊ እውቅና በማግኘት የተቋቋመ ማኅበር ሲሆን ላለፉት 24 ዓመታት አግባብነት ካላቸው መን...
23/09/2023

የኢትዩጵያ ሆቴል ባለሙያዎች ማህበር

የኢትዮጵያ የሆቴል ባለሙያዎች ማህበር ሰኔ 25 ቀን 1991ዓ.ም ህጋዊ እውቅና በማግኘት የተቋቋመ ማኅበር ሲሆን ላለፉት 24 ዓመታት አግባብነት ካላቸው መንግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ጋር ግንኙነት በማድረግ የማህበሩ አላማዎች ለማሳካት የተለያዩ ስራዎችን ሲሰራ ቆይቷል፡፡

የማህበሩ አላማ

• የሆቴል ሙያን ማስከበር
• ለቱሪዝም ኢንደስትሪው ድጋፍ መስጠት
• የአባላትን ግንኙነት መፍጠር
• ከአገር ውስጥ እና ከውጭ አገር አቻ ማህበራት ጋር ግንኙነት መፍጠር
• ሙያውን ለማሳደግ ለአባላቱ ትምህርታዊ መድረኮችን ማመቻቸት
• አባላት ራሳቸውን እንዲችሉ ማበረታታት

ማህበሩ ያከናወናቸው ዋና ዋና ተግባራት

1. ከፊዴራል የቱሪዝም ሚኒስቴር እና ከስራና ክህሎት ሚኒስቴር ጋር በቅርበትና በጋራ በመስራት የሚከተሉት አንኳር ስራዎች አከናውኗል፡-
• በቱሪዝም ሚኒስቴርና በክልሎች ቱሪዝም ቢሮ በሚያዘጋጁት የስልጠና ፍላጎት መሠረት በኮሮና ምክንያት እስካቆመበት ጊዜ ድረስ ለበርካታ የሆቴል ባለሙያዎች ሙያዊ ሥልጠና ሲሰጥ ቆቷል፡፡
• በሆቴል ዘርፍ በሚሰጡ የሙያ ስርዓተ-ትምህርት ከ level 1-4 ድረስ በስራና ክህሎት ሚኒስቴር በቀረቡ ሰነዶች ላይ የሰነዶች ክለሳና ማሻሻያ ላይ ማህበሩ ባለሙያዎች መድቦ ሥራዎቹ ከግብ እንዲደርሱ ድርሻውን ተወጥቷል፡፡
• ቱሪዝም ለሀገር የሚሰጠው የኢኮኖሚና ማህበራዊ አስተዋጽ TSA (Tourist satellite Account) በቱሪዝም ሚኒስቴር በአዲስ መልክ በውጪ ባለሙዎች ጭምር ጥናቶች እየተደረጉ ይገኛሉ ፡፡ በዚሁ መሠረት የኢትዮጵያ የሆቴል ባለሙያዎች እንደ አንድ የጥናቱ አካል በመሆን ሙያዊ ድርሻውን እየተወጣ ይገኛል ፡፡
2. ማህበሩን በማስተዋወቅና የአባላት ቁጥጥርን ለማሳደግ በተለያዩ የሆቴልና የቱሪዝም ዘርፍ በየጊዜው በተዘጋጁ ኮንፈረሶች ፣ ኤግዝቢሽኖች ፣ ሴሚናሮች ላይ የነቃ ተሳትፎ በማድረግ የማህበሩን አላማ በማስተዋወቅ ከፍተኛ ስራዎችን በመስራት የማህበሩን አባላት ከፍ አድርገናል፡፡
3. ከሆቴልና ቱሪዝም ማሠልጠኛ ኢንስቲትዮት እና ከክልል የቱሪዝም ቢሮዎች ጋር በመተባባር ፤ በየክልሉ ላሉ ሆቴሎች በጥናት ላይ የተደገፈ ስልጠና ለመስጠት የመግባቢያ ሰነድ በተፈራረመው መሠረት ሥራው እየተከናወነ ይገኛል፡፡
4. ከፌደራል የደረጃ ምደባ ፣ ከፌደራል የጤና ጥበቃ እና ከክልል የቱሪዝም ቢሮዎች ጋር በመሆን በሆቴልና ሆቴል ነክ የሥራ መስኮች የደንብ ልብስ አስፈላጊነትና የአካባቢ ንፅህና አጠባበቅ በተመለከተ ሀገራዊ ሰነድ ተዘጋጅቶ በሚመለከታቸው የመንግስት አካላት ፀድቆ ተግባራዊ እንዲሆኑ ተደርጓል፡፡
5. በአሁኑ ጊዜ እንደ ፋሽን ሆኖ አንዳንድ ከቼን ሆቴሎች ውጭ የሆኑ ሁሉ በሀገር ውስጥ ባለሙያ ሊሠሩ የሚገቡ ስራዎችን ያለምንም ውድድር የውጭ ሀገር ዜጎችን ቀጥረው በማሠራት ላይ ይገኛሉ ፡፡ በዚሁ መሠረት ማህበሩ የጉዳዩ አሳሳቢነት ከፌደራል የቱሪዝም ቢሮና ከአ/አበባ የባህልና ቱሪዝም ቢሮ ጋር በመወያየት የፓሊስ ማፅደቅ ስራዎችን ጀምረናል፡፡
6. የኮርና ወረርሽኝ በተከሰተ ጊዜ በርካታ ባለኮከብ ሆቴሎች (ከጥቂቶች በስተቀር) ሠራተኞችን ከስራ ማባረር ጀምረው ነበር ፤ ይሁን እንጂ ማህበሩ በወቅቱ ከነበሩ የባህል እና ቱሪዝም ሚኒስቴር መስሪያቤት ፤ የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር፤ ከኢትዮጵያ ሰራተኛ ማህበራት ኮንፌዴሬሽን ጋር በጋራ አብረን በመስራት እንዲሁም የተለያዩ ታዋቂ ሚዲያዎችን በመጋበዝ ባደረገው ከፍተኛ ጥረት መንግስት ጣልቃ ገብቶ ሠራተኞች ከስራ ከመፈናቀል ተርፈዋል፡፡
7. የገነት ሆቴል የምግብ ዝግጅት በሚታደስበት ጊዜ ማህበሩ ባለሙያ በመመደብ ሥራው በጥራትና በዘመናዊነት እንዲጠናቀቅ ደርሻውን ተወጥቷል፡፡
8. በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል በነበረው ግጭት ማህበሩ ለመከላከያ ሠራዊት የምግብ ግብአት ገዝቶ በማቅረብ ድርሻውን ተወጥቷል፡፡

ለማህበሩ እድገት ማን ምን ያድርግ

የኢሆባሙ የተመሰረተው የሆቴል ባለሙያዎች በተደራጀ መልክ ህጋዊ ሂደት ተከትለው ለመብታቸው ፣ ለሙያቸው ፣ ለጥቅማቸው ፣ ለህልውናቸው ፣ ለተሻለ ሙያዊ አገልግሎት ጥራት እና ወዘተ ለማግኘት እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ይህ ማህበር ከተመሰረተ 24 ዓመታትን ያስቆጠረ ሲሆን አንግቦ የተነሳውን አላማ ከግብ ለማድረስ ሁሉም የሆቴል ባለሙያዎች የበኩላቸውን መወጣት ይገባቸዋል፡፡ ማህበር (Association) ትልቅ አቅም ያለው አደረጃጀት እንደሆነ ይታወቃል። ስለዚህ የምንፈልገውን ጥያቄያችን ለማሳካት ተሰሚነት ያለውን ጠንካራ እና አንጋፋ ማህበር ማጠናከር ምርጫ የማሰጠው ጉዳይ ነው ።
የኢትዮጵያ የሆቴል ባለሙያዎች ማህበር ትልቅ ሃገራዊ ተቋም እንዲሆንና ለሁሉም የሃገሪቱ የሆቴል ባለሙያዎች ድምፅና ልሳን እንዲሆን የሚፈልግ የሆቴል ባለሙያ ሁሉ ከዳር ቁሞ ከመቆዘምና ሙያዉን ከማማረር ይልቅ የማህበሩ ህጋዊ አባል ሁኖ ማህበሩን ጠንካራ ተቋም በማድረግ ለመብቱ ዘብ መቆምና መጠየቅ ይገባዋል።
አንድን ማህበር ጠንካራና ግዙፍ ከሚያደርጉት የመጀመርያዎቹ ነገሮች አንዱ በስሩ ያሉ አላማዉን በፅኑ የሚደግፉ የማህበሩ አባላት ዋነኞቹ ናቸዉ። በአብዛኛዉ ታዳጊ ሃገራት የሲቪል ማህበራት ጠንካራ ተቋማት እንዲሆኑ አይፈለግም፡፡ እነዚህ ተቋማት ጠንክረዉ ከወጡ መንግስትን የመሞገትና የሰራተኛዉን አላማ ለማስፈፀም በእጅጉ ቅርብ ስለሆኑ ነዉ።
በኢትዮጵያ የሆቴል ባለሙያዎች አሁናዊ ሁኔታ እጅግ ብዙ በሚባሉ የተበጣጠሱ የሙያ ማህበራት መኖራቸዉ የሆቴል ባለሙያዎችን የመከራ ጊዜ አስረዘመዉ እንጂ ለሆቴል ባለሙያዎች ያመጣዉ ተጨባጭ ለዉጥ የለም።
በሃገሪቱ ትልቁን የሰዉ ሃይል የሚሸፍነዉ የሆስፒታሊቲ ኢንደስትሪ እስካሁን አቅምያለው በባለሙያዎቹ የተደገፈ ለመብቱ የሚሟገትለት አንድ ትልቅ ሃገራዊ ተቋም ባለመኖሩ ከጊዜ ወደ ጊዜ በብዙ ነገሮች ተጎጂ እየሆነ ሙያዉም የሚገባዉን ያክል ሳያድግና ተገቢዉን ክብር ሳያገኝ ቀርቷል ።
ስለሆነም የኢትዮጵያ የሆቴል ባለሙያዎች ማህበርን በደንብ ማደራጀት ፣ትልቅ፣ አንጋፋ የሆቴል ባለሙያዎች ብቸኛ የመሰብሰቢያ ተቋም ማድረግ ለነገ የማይባል ለሁሉም የሆቴል ባለሙያዎች ምርጫ የሌለዉ ተግባር ነዉ። ቁጭ ብለን ማንም መብታችን እንዲያከብርልን አንጠብቅ መብታችን የሚከበረዉ በራሳችን ጥረት ብቻ እና ብቻ ነዉ !!

የቴሌግራም ቻናላችንን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
https://t.me/hoteliergroup

የፌስ ቡክ ፔጃችን
https://www.facebook.com/profile.php?id=100057403332375&mibextid=ZbWKwL

በመስቀል ደመራ እና በኢሬቻ በዓል አከባበር ዙሪያ ውይይት ተካሄደ *** መስከረም 08/2016 ዓ.ም  (ባ.ኪ.ቱ ቢሮ) የአዲስ አበባ ባህል፣ ኪነ-ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ ሰራተኞች እና ከአራቱም...
19/09/2023

በመስቀል ደመራ እና በኢሬቻ በዓል አከባበር ዙሪያ ውይይት ተካሄደ

***

መስከረም 08/2016 ዓ.ም (ባ.ኪ.ቱ ቢሮ)

የአዲስ አበባ ባህል፣ ኪነ-ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ ሰራተኞች እና ከአራቱም ቴአትር ቤት ሰራተኞች ጋር በመሆን «የአብሮነት፣ የወንድማማችነትና የፍቅር መገለጫ የሆኑ በአላቶች በጋራ እናክብር» በሚል መሪ ቃል ውይይት ተካሄደ።

የአዲስ አበባ ባህል፣ ኪነ-ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ ከሌላው ተቋማት በተለየ ሁኔታ በአዋጅ ከተሰጠው ተግባራት መካከል በዩኔስኮ ከተመዘገቡት የማይዳሰሱ ቅርሶች መካከል በዚህ በያዝነው ወር የሚከበረው የመስቀል ደመራና የኢሬቻ በዓል ይገኝበታል።

በአገራችን በአደባባይ የሚከበሩና በርካታ ህዝቦች ወጥተው የሚያከብሩት በዓላቶች ያሉ ሲሆን በዓላቶቹ የራሳቸው የሆነ ወግ፣ ባህልና ትውፊቶች አሏቸው።

የመስቀል ደመራና የኢሬቻ በዓል ሲከበር በርካታ ሚሊዮን ህዝቦች ወጥተው በአብሮነት፣ በፍቅርና በአንድነት የሚያከብሩት በዓል ከመሆኑ ባሻገር ከመላው አለም ዲፕሎማቶችና ቱሪስቶች በመገኘት በዓሉን በደመቀ ሁኔታ የሚከበሩ በዓል ናቸው ያሉት የአዲስ አበባ ባህል፣ ኪነ-ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ የቱሪዝም ዘርፍ ኃላፊ አቶ ኃፍታይ ገ/እግዚአብሔር ናቸው።
ቅናሽ በማድረግ ቱሪስቱን ምንስብበት መንገድ ቢዘጋጅ ጥሩ ነው በማለት ከተሳታፊዎች ሀሳብ ተነስቷል።

እንኳን ደስ አለን።
18/09/2023

እንኳን ደስ አለን።

ሳምንቱ በሆስፒታሊቲ ዘርፍ!!!🙏🙏🙏በአለምአቀፍ ደረጃ በየዓመቱ እ.ኤ.አ የሴፕቴምበር ወር በገባ በሁለተኛው ሳምንት የ "Housekeeper Day" ታስቦ ይውላል።እንደሚታወቀው በሆቴልና መሠል...
13/09/2023

ሳምንቱ በሆስፒታሊቲ ዘርፍ!!!

🙏🙏🙏

በአለምአቀፍ ደረጃ በየዓመቱ እ.ኤ.አ የሴፕቴምበር ወር በገባ በሁለተኛው ሳምንት የ "Housekeeper Day" ታስቦ ይውላል።

እንደሚታወቀው በሆቴልና መሠል አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ውስጥ በHousekeeping ስራ ክፍል የሚሰሩ ሰራተኞች ሆቴሉን ፅዱና ምቹ በማድረግ ረገድ ያላቸው ሚና የጎላ ነው።

ሳምንቱ እነዚህ ትጉ ሰራተኞች የሚመሰገኑበትና እንዲበረቱ የሚደረግበት ነው። ተቋሞቻችን ፅዱና ለእንግዶችም ሆነ ለሰራተኞች ምቹ እንዲሆን ስለምታደርጉ ከልብ እናመሰግናለን።

🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼

Hospitaliy Industry on this week!!

Globally Every 2nd week of September Hospitality Sector stakeholders Celebrate "Housekeepers Day".

As we all knew that,Housekeeping Department team members who have spend more times for Cleaning and maintaining safe working environment to Hotels, Resorts & others Service provider firms.

Let's honor these important team members They deserve so much gratitude for Their effort that make your property shine.

Thank You to these dedicated Department and Employees!



Source:-
Witness Hospitality

🌻🌻🌻🌻🇪🇹🇪🇹🇪🇹🌼🌼🌼🌼የኢትዮጵያ ሆቴል ባለሙያዎች ማህበር እንኳን ለአዲሱ ዓመት በሰላም አደረሳችሁ እያለ መልካም ምኞቱን ይገልፃል።መልካም አዲስ ዓመት!!🌻🌻🌻🌻መልካም በዓል!! 🌼🌼🌼🌼
10/09/2023

🌻🌻🌻🌻🇪🇹🇪🇹🇪🇹🌼🌼🌼🌼

የኢትዮጵያ ሆቴል ባለሙያዎች ማህበር እንኳን ለአዲሱ ዓመት በሰላም አደረሳችሁ እያለ መልካም ምኞቱን ይገልፃል።

መልካም አዲስ ዓመት!!🌻🌻🌻🌻
መልካም በዓል!! 🌼🌼🌼🌼

HOTEL EMPLOYEES DAY!!!🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹 🇪🇹   🍷🍹   🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹Employees are the lifeblood of every hotel and cornerstone of an enjo...
05/09/2023

HOTEL EMPLOYEES DAY!!!

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹 🇪🇹 🍷🍹 🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Employees are the lifeblood of every hotel and cornerstone of an enjoyable hotel stay. We appreciate Multi Thousands of hotel professionals who work in Ethiopian Hotels for their incredible service and dedication today and throughout the year,

we are proud to recognize hotel employees and their important work.The Ethiopian Hospitality industry doesn’t work without dedicated hotel employees, and today is an opportunity to recognize all of their hard work & the hotel industry depends on these energetic and hardworking team members who work day in and day out to ensure smooth operations and make the guest experience unforgettable.

We Applaud these hardworking professionals and hope you also find time to thank a hotel employees on this matter.

Ethiopian hotel employees are the backbone of our Industry, and we salute their empathy, professionalism, dedication, and hospitality.

Thank you for serving up the Hospitality!! 🙏🙏🙏

በመላው ኢትዮጵያ ለሚገኙ የሆቴል ሰራተኞች ትህትና የተሞላበት፣ቀልጣፋና አስደሳች አገልግሎት ከኢትዮጵያዊ መልካም መስተንግዶ ጋር ስለሰጣችሁን ወደፊትም ስለምትሰጡን ከልብ እናመሰግናለን። 🙏🙏🙏

Witness Hospitality

03/09/2023

አዲስ አበባ የዓለም ቱሪዝም ከተሞች ፌደሬሽንን ተቀላቀለች
----
የአዲስ አበባ ከተማ የዓለም ቱሪዝም ከተሞች ፌደሬሽን አባል ሆናለች፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ጃንጥራር አባይ የአባልነት ሰርተፍኬቱን በቻይና ቤጂንግ ከፌደሬሽኑ አመራሮች ተቀብለዋል፡፡

የዓለም ቱሪዝም ከተሞች ፌደሬሽን በ85 ሀገራት የሚገኙ 242 በላይ ከተሞችን በአባልነት ያቀፈ ተቋም መሆኑን በቻይና የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመላክታል፡፡

ፌደሬሽኑ አባል ከተሞች በቱሪዝም ዘርፍ ያላቸውን ልምድ በመጋራት በትብብር እንዲሰሩ ሁኔታዎችን እንደሚፈጥር ተገልጿል፡፡
ምንጭ:- የአዲስ አበባ ኮሙኒኬሽን ቢሮ

የኢትዮጵያ ሆቴል ባለሙያዎች ማህበር በዛሬው ቀን የምስረታ ጉባዔውን በይፋ ባስተዋወቀው የአዲስ አበባ ሆቴልና ቱሪዝም ባለሙያዎች ማህበር መመስረት የተሰማውን ላቅ ያለ ደስታ ይገልፃል።🇪🇹🇪🇹በ...
29/08/2023

የኢትዮጵያ ሆቴል ባለሙያዎች ማህበር በዛሬው ቀን የምስረታ ጉባዔውን በይፋ ባስተዋወቀው የአዲስ አበባ ሆቴልና ቱሪዝም ባለሙያዎች ማህበር መመስረት የተሰማውን ላቅ ያለ ደስታ ይገልፃል።

🇪🇹🇪🇹
በዘርፉ ውስጥ ያሉትን መልካም ነገሮች ለማስቀጠል ፣ተግዳሮቶችን ለመቀነስ፣ብቁና ተወዳዳሪ የሰው ሀይል፣ዘመናዊና ወቅቱን የዋጀ ቀልጣፋ አገልግሎት እንዲኖር በሚደረገው ጥረት ውስጥ የሙያ ማህበራት ሚና የላቀ መሆኑን እናምናለን።

🇪🇹🇪🇹

በዚህም ማህበራችን ከአዲስአበባ የሆቴልና ቱሪዝም ባለሙያዎች እና ከሌሎች አቻ ማህበራት ጋር በመሆን በዘርፉ ውስጥ የላቀ ስራ እንደምንስራ በመግለፅ በድጋሚ ማህበሩን ለመሰረቱ መስራች አባላትና የሙያ አጋሮቻችን እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት እንወዳለን።

መልካም የስራ ጊዜ ይሁንላችሁ።🇪🇹🇪🇹

28/08/2023

በቱሪዝምና ሆስፒታሊቲ ዘርፍ ኢትዮጵያዊ ቀለም ያለው አገልግሎት እንዲኖር የሚያስችል ውይይት ተደረገ።
ቱ. ማ. ኢ.
ነሐሴ 17/2015 ዓ ም
የቱሪዝም መሪዎች ወግ በሚል ርዕስ ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ከዘርፉ ባለድርሻ አካላት ጋር ዛሬ በአንባሳደር ሆቴል ውይይት አድርጓል።
የዚህ ውይይት ሀሳብ በቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት የምርምርና ማማከር ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ይታሰብ ስዩም እንደገለጹት የቱሪዝምና ሆስፒታሊቲ ዘርፍ ኢትዮጵያዊ ባህልና መልክ ያለው ለማድረግ የቱሪዝም ማለቅያ ስትራቴጂ ለማዘጋጀት ከባለድርሻና ከጉዳዩ ባለቤቶች ጋር መወያየት በማስፈለጉ ነው ብለዋል፡፡ ሀገራችን ታሪካዊ ፣ ተፈጥሯዊና የሰው ሰራሽ የቱሪዝም ሃብት ያላት ቢሆንም በሚፈለገው ደረጃ አላደገም፤ ለዚህም የተለያዩ ውስንነቶች እንዳሉ ጥናቶች ያመለክታሉ ብለዋል አቶ ይታሰብ አያይዘውም የቱሪስቶችን እርካታና ፍሰቱን ለመጨመር እንዴት እንደሚቻል እና የአገልግሎት አሰጣጣችን ወጥነት እንዲኖረው ከሁሉም ባድርሻ አካላት የሚጠበቀውን ውይይት ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን ጠቁመዋል።
ከታላቁ አስጎብኚ ድርጅት የመጡት አቶ ናሆም አድማሱ እንደተናገሩ ቱሪዝም የጋራ ሥራ የሚፈልግ በመሆኑ ተቀናጅተን በመስራት ጥራት ላይ ቅድሚያ ቢሰጥ የተሻለ ነው ብለዋል።
ከአዲስ አበባ ከተማ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ አቶ ሳምሶን አየናቸው እንዳሉት በመጀመሪያ የኢትዮጵያዊ ቀለም ስንል ምን ምን እንደሆኑ በመሰብሰብ ወደ አንድ ሀሳብ መምጣት አለብን በማለት ሀሳባቸውን ገልጸዋል።
ሌሎች ተሰብሳቢዎችም በተደጋጋሚ በጉዳዩ ዙሪያ ስለአስፈላጊነቱ እና መሰራት ስላለባቸው ቅድመ ሁኔታዎች ሃሳብ የሰጡ ሲሆን፤ ወጥ የሆነ ሃሳብ አምጥተን መግባባት ላይ አስከምንደርስ ድረስ በየወሩ መገናኘት እና ሃሳብ መለዋወጥ አስፈላጊነው ብለዋል፡፡ ስለሆነም በሚቅለው ወር በተመሳሳይ አጀንዳ እንደ ሃገር የሚያስፈልጉን እና ልናዳብራቸው የሚገቡትን ነቅሰን በማውጣት የባለድርሻ አካላት የውይይት መድረክ ለማዘጋጀት አስፈላጊነቱ ታምኖበታል። (ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንሰቲትዩት )

🇪🇹🇪🇹🇪🇹   እንኳን ደስ አለን!!🇪🇹🇪🇹🇪🇹በቡዳፔስት የአለም  የአትሌቲክስ ሻምፒዮና በሴቶች 10ሺህ ሜትር ኢትዮጵያዊያን ከ1ኛ እስከ 3ኛ በመውጣት የወርቅ፣ የብርና የነሃስ ሜዳሊያዎችን ጠ...
19/08/2023

🇪🇹🇪🇹🇪🇹 እንኳን ደስ አለን!!🇪🇹🇪🇹🇪🇹

በቡዳፔስት የአለም የአትሌቲክስ ሻምፒዮና በሴቶች 10ሺህ ሜትር ኢትዮጵያዊያን ከ1ኛ እስከ 3ኛ በመውጣት የወርቅ፣ የብርና የነሃስ ሜዳሊያዎችን ጠራርገው ወስደዋል።

አረንጓዴው ጎርፍ በቡዳፔስት ተመልሷል።💚💛❤️

Ethiopians sweep women’s 10,000m world championships !!

The Ethiopian Atheletics Squad AKA 'Green Flood' back to the Right Place!!

Congrats for All Ethiopian 🇪🇹🇪🇹🇪🇹

ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ከሆቴል ባለቤቶች ጋር በመተባበር በሀገር ዓቀፍ ደረጃ የሆቴል አገልግሎት ጥራትን ማሻሻል ዓላማ ያደረገ የአጭር ጊዜ የስራ ላይ ስልጠናዎች በአዳማ ከተማ ለሚገኙ ...
15/08/2023

ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ከሆቴል ባለቤቶች ጋር በመተባበር በሀገር ዓቀፍ ደረጃ የሆቴል አገልግሎት ጥራትን ማሻሻል ዓላማ ያደረገ የአጭር ጊዜ የስራ ላይ ስልጠናዎች በአዳማ ከተማ ለሚገኙ ከአራት መቶ በላይ ለሚሆኑ የሆቴል ባለሙያዎች መስጠት ጀምሯል፡፡

የስልጠናው ዋና ዓላማ የባለሙያዎችን አቅም በማሳደግ የሆቴሎች አገልግሎት ደረጃውን የጠበቀ ለማድረግ እንደሆነና በመጀመሪያ ዙር በስድስት ሆቴሎች በምግብ ዝግጅት፣ በምግብና መጠጥ መስተንግዶ፣በቤት አያያዝ እና ደምበኞች አገልግሎት ላይ ያተኮረ በተግባር የተደገፈ ስልጠና መሆኑን ተገልጿል፡፡

የአጫጭር ጊዜ ስልጠናው አዳማን ጨምሮ የሆቴል ባለቤቶችና ስራ አስኪያጆችንም በማካተት በቀጣይነት በሌሎች የክልል ከተሞች ላይ ለመስጠት እየተሰራ ይገኛል።

ስልጠና እየተሰጠበት ከሚገኙ ሆቴሎች መካከል የካኖፒ ሆቴል ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ቶሌራ ዓለሙ

"በኢንስቲትዩቱ እየተሰጠ ያለው ስልጠና ሰራተኞች ባላቸው እውቀት ላይ የሙያ ሥነ-ምግባርን እንዲያዳብሩና የአመለካከት ለውጥ ለማምጣት እንደሚያግዝ የሆስፕታሊቲ እንዱስትሪው ካለው ተለዋዋጭ ባህሪ አንጻር ሰራተኞች ሁሉን አቀፍ ሙያተኛ እንዲሆኑ ይፈለጋል ጥራት ያለው የሆቴል አገልግሎት መስጠት የሀገርን በጎ ገጽታ ለመገምባት ከፍተኛ አስተዋጽኦ አለው" በማለት ሀሳባቸውን ገልፀው የማሰልጠኛ ኢንስቲትዩቱ የተጀመረውን ስልጠና ጥናትና ፍላጎት ላይ በመመስረት በቀጣይነት ሊያዘጋጅ እንደሚገባም ጠቁመዋል፡፡

የመረጃ ምንጭ:- Tourism Training Institute

 #መረጃየኢትዮጵያ ሆቴል ባለሙያዎች ማህበር በመላው ኢትዮጵያ ከሚገኙ የማህበሩ ነባርና አዳዲስ  አባላት ጋር በቀጣይ  ሊከውናቸው ስላሰባቸው ጉዳዮች ለመወያየትና አዳዲስ አደረጃጀቶችን ለመፍጠ...
04/08/2023

#መረጃ

የኢትዮጵያ ሆቴል ባለሙያዎች ማህበር በመላው ኢትዮጵያ ከሚገኙ የማህበሩ ነባርና አዳዲስ አባላት ጋር በቀጣይ ሊከውናቸው ስላሰባቸው ጉዳዮች ለመወያየትና አዳዲስ አደረጃጀቶችን ለመፍጠር ዝግጅት በማድረግ ላይ ይገኛል።

በቅርቡ የተመረጡት የማህበሩ የቦርድ አባላት በተለይ በክልል ዋና ዋና ከተሞች ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ለመክፈትና አባላት በቅርበት እንዲገለገሉበት ለማድረግ ከሚመለከታቸው የዘርፉ አካላት ጋር በመወያየት ላይ ይገኛሉ።

በተጨማሪም በ2016 የመጀመሪያ ወር መገባደጃ በመላው ሀገሪቱ ከሚገኙ የማህበሩ አባላት ጋር ጠቅላላ ጉባዔ በአዲስአበባ ለማድረግ ቅድመ ዝግጅት በማድረግ ላይ ይገኛል።



EHPA aimed to link with Existing and New Members of Association on the update of upcoming task and maintain structure that members should aware the planned work.

The New Elected Board Members Were discussed with Concerned regarding the Opening Branch office locating entire Regional Cities that Consists easy access of Members.

Meanwhile, Board members planned to held General Meeting with Members on the upcoming Month perhaps End of September,2023 at the Vibrant City of Addis Ababa.

Board Members!!

31/03/2023

የኢትዩጵያ ሆቴል ባለሙያዎች ማህበር አባል ለመሆን ፍላጎት ያላችሁ እና በተደጋጋሚ በውስጥ መልዕክት"እንዴት አባል መሆን ይቻላል"? እያላችሁ ለምትጠይቁ የሆቴል ባለሙያዎች ነገ ማለትም መጋቢት 23/2015ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 በገነት ሆቴል የመሰብሰቢያ አዳራሽ በመገኘት የአባልነት ምዝገባ ማከናወን እና ከማህበሩ ጋር ወደፊት ስራዎችን ለመስራት በጋራ የሚወሰኑ ውሳኔዎች ላይ እንድትሳተፉ እናሳስባለን፡፡

ለኢትዩጵያ የሆቴል ባለሙያዎች ማህበር አባላት የተላለፈ የጠቅላላ ጉባዔ ጥሪየኢትዩጵያ ሆቴል ባለሙያዎች ማህበር የአባላት ጠቅላላ ጉባዔ ቅዳሜ መጋቢት 23/2015 ዓ.ም ለጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ ...
27/03/2023

ለኢትዩጵያ የሆቴል ባለሙያዎች ማህበር አባላት የተላለፈ የጠቅላላ ጉባዔ ጥሪ

የኢትዩጵያ ሆቴል ባለሙያዎች ማህበር የአባላት ጠቅላላ ጉባዔ ቅዳሜ መጋቢት 23/2015 ዓ.ም ለጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ በአዲስ አበባ ገነት ሆቴል መሰብሰቢያ አዳራሽ ስለሚካሄድ የማህበሩ ነባር እና አዳዲስ አባላት በተጠቀሰው ሰዓት፣ ቀን እና ቦታ በጉባኤው ላይ እንድትገኙ የማህበሩ ቦርድ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡

የጉባዔ አጀንዳዎች

1. የጉባዔውን አጀንዳ ማፅደቅ
2. የማህበሩን የስራ፣ ፋይናንስ ሪፓርት ማድመጥ
3. የኦዲት ሪፓርት ማድመጥ
4. በቀረበው ሪፓርት ላይ መወያየት
5. አዲስ የቦርድ አባላት ምርጫ ማከናወን
6. የጉባዔውን ቃለ ጉባኤ ማፅደቅ

የኢትዩጵያ ሆቴል ባለሙያዎች ማህበር ቦርድ

መልካም የመስቀል በዓል
26/09/2022

መልካም የመስቀል በዓል

የ2015 ዓ.ም የአለም የቱሪዝም ቀን በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል
26/09/2022

የ2015 ዓ.ም የአለም የቱሪዝም ቀን በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል

በሆቴል ዘርፍ ለባለሙያው እድል እየተሰጠ አይደለም
05/07/2022

በሆቴል ዘርፍ ለባለሙያው እድል እየተሰጠ አይደለም

በሆቴልና ቱሪዝም ዘርፍ ለአገር ውስጥ ባለሙያዎች ዕድል መነፈጉ አገሪቷን ለውጭ ምንዛሪ ብክነት መዳረጉ ተጠቆመ
***************
(ኢ ፕ ድ)
በሆቴልና ቱሪዝም ዘርፍ ለሰለጠኑ የአገር ውስጥ ባለሙያዎች ዕድል አለመሰጠቱ አገሪቷ ከዘርፉ የምታገኘውን የውጭ ምንዛሬ የውጭ አገራት ባለሙያዎችን በመቅጠር እንድታባክን እያደረጋት መሆኑን የቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተርና የሆቴል አስተዳደር ተመራማሪና አማካሪ አቶ ይታሰብ ስዩም ተናገሩ።

አቶ ይታሰብ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ በኢትዮጵያ ከአሥር ዓመታት በላይ በዘርፉ ልምድ ያላቸውና እስከ ባለአምስት ኮከብ ሆቴሎችን የመምራት አቅም ያላቸው የአገር ውስጥ ባለሙያዎች ቢኖሩም አብዛኞቹ ትላልቅ ሆቴሎች ከውጭ አገራት ባለሙያዎችን እያስመጡ ይቀጥራሉ።

ይህ አካሄድ ዜጎችን የሥራ ዕድል እንዳያገኙ ከማድረጉም በላይ አገሪቷ በዘርፉ የምታገኘውን የውጭ ምንዛሪ የውጭ አገራት ባለሙያዎችን በመቅጠር መልሳ እንድታጣው ያደርጋታል ብለዋል።

በኢትዮጵያ የሆቴልና ቱሪዝም ዘርፍ ለአገሪቱ ኢኮኖሚያዊ እድገት የበኩሉን ሚና እንዲጫወት ለማስቻል በሙያው ለሰለጠኑ የአገር ውስጥ ባለሙያዎች ዕድል ሊሰጣቸው እንደሚገባም አስተያየታቸው ሰጥተዋል።

ኢትዮጵያ ለቱሪዝም ዘርፉ ልዩ ትኩረት በመስጠትና ዜጎችም ዘርፉ በሚፈጥረው የሥራ ዕድል ተጠቃሚ ለማድረግ በሆቴልና ቱሪዝም ዘርፍ አሁን ላይ እስከ 15 በሚደርሱ የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች በመጀመሪያ ዲግሪ ባለሙያዎችን እያሰለጠነች ትገኛለች ያሉት ተመራማሪው፤ አብዛኞች ትላልቅ ሆቴሎች ለአገር
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=76455
ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ‼️
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ተጨማሪ የመረጃ አማራጮቻችን ‼️
ዩቲዩብ 👇
https://youtube.com/channel/UCoH2CVwWn9suWP7q0u2L7MA
ቴሌግራም 👇
https://t.me/ethpress
ትዊተር 👇
https://twitter.com/PressEthio
ድረ ገጽ 👇
https://www.press.et/

በኢትዮጽያ ሆቴል ባለሙያዎች ማህበር እና በቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት የተቀዛቀዘውን የሆቴል ኢንደስትሪ ባለሙያዎች ለማነቃቃት የተዘጋጀ  ሥልጠና በገነት ሆቴል ተሰጠ። በስልጠናው ለተሳተፍች...
04/06/2022

በኢትዮጽያ ሆቴል ባለሙያዎች ማህበር እና በቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት የተቀዛቀዘውን የሆቴል ኢንደስትሪ ባለሙያዎች ለማነቃቃት የተዘጋጀ ሥልጠና በገነት ሆቴል ተሰጠ። በስልጠናው ለተሳተፍችሁ እናመሰግናለን።

04/06/2022

የባለሙያው ድምፅ የሆነው የኢትዮጵያ ሆቴል ባለሙያዎች ማህበር። ከአቶ ልዑል ሰገድ የተላለፈ መልዕክት

03/06/2022
01/06/2022

ለውድ የሆቴል ባለሙያዎች
ስልጠናዉ ሁለት ቀናት ብቻ ቀረዉ፤
አርብ ከጠዋቱ 2፡30 ላይ በገነት ሆቴል

26/05/2022
26/05/2022

የኢትዮጵያ ሆቴል ባለሙያዎችን በሚመለከት የተዘጋጀ ዘገባ

ለኢትዮጵያ ሆቴል ባለሙያዎች ማህበር አባላት እና ሌሎች ባለሙያዎች በሙሉአንጋፋዉ ማህበራችን የኢትዮጵያ ሆቴል ባለሙያዎች ማህበር ከቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ጋር በመተባባር ያዘጋጀዉ ስልጠ...
26/05/2022

ለኢትዮጵያ ሆቴል ባለሙያዎች ማህበር አባላት እና ሌሎች ባለሙያዎች በሙሉ

አንጋፋዉ ማህበራችን የኢትዮጵያ ሆቴል ባለሙያዎች ማህበር ከቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ጋር በመተባባር ያዘጋጀዉ ስልጠና በመጭዉ ግንቦት 26/2014 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 የሚጀመር ሲሆን፤ ይህን በመገንዘብ በሰዓቱ በገነት ሆቴል አዳራሽ እንድትገኙ በድጋሜ ጥሪያችን እናስተላልፋለን፡፡ አድራሻ፡ ከሜክሲኮ ወደ ቄራ በሚወስደዉ መንገድ ላይ

የኢትዮጵያ ሆቴል ባለሙያዎች ማህበር

20/05/2022

ለኢትዮጵያ የሆቴል ባለሙያዎች በሙሉ

ባለፉት ጥቂት ጊዚያት የሀገራችን የሆቴል ዘርፍ በኮሮናና በጸጥታ ችግሮች በአስከፊ ሀኔታ እንደተጎዳ ይታወቃል፡፡በእነዚህ ጊዚያትም የዘርፉ ባለሙያዎች ከፍተኛ የማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ስነልቦናዊ ችግሮች ተጋልጠዉ ቆይተዋል፡፡ በመሆኑም የባለሙያዉን ስሜት እንዲሁም ዘርፉን ለማነቃቃት ያለመ ስልጠና የኢትዮጵያ የሆቴል ባለሙያዎች ማህበር ከአንጋፋዉ የሆቴልና ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት(CTTI) ጋር በመተባባር ግንቦት 26/2014 ዓ.ም በገነት ሆቴል አዘጋጅተናል፡፡ በመሆኑም መላ የማህበራችን አባላት እና ሌሎች የሆቴል ባለሙያዎች ተሳታፊ እንድትሆኑ በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡

የኢትዮጵያ ሆቴል ባለሙያዎች ማህበር

Address

Mexico
Addis Ababa
00000

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethiopian Hotel Professionals Association -EHPA posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Videos

Share

Our Story

Ethiopian Hospitality Professionals’ Association EHPA Is The First Professional Association In Ethiopia Which Is Designed To Encourage All Hospitality Professionals (Tourism & Hotel) To Discuss Common Issues, To Share Experiences, Communicate Opportunities, Contribute To The Sector And More,

Nearby travel agencies