Choke mountain Tour and Travel Agent

Choke mountain Tour and Travel Agent It is a tour and travel agents for personal and group local and international tourists whose needs t

Blue nile fall is always new
29/07/2023

Blue nile fall is always new

Today's enjoyable best trip at Blunile fall
29/07/2023

Today's enjoyable best trip at Blunile fall

20/01/2023

Timket

20/01/2023
Epiphany at Gonder
19/01/2023

Epiphany at Gonder

19/01/2023

ገነትን ከሚያጠጡት አራቱ አፍላጋት መካከል አንዱ በሆነ በግዮን ወንዝ ዳር የጥምቀት በዓል አከባበር

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለታላቁ የከተራ እና የጥምቀት ክብረ በዓል በሰላም እና በጤና አደረሳችሁ።
18/01/2023

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለታላቁ የከተራ እና የጥምቀት ክብረ በዓል በሰላም እና በጤና አደረሳችሁ።

05/01/2023

ኑ! የገናን በዓል የድንቅ ተፈጥሮ ባለቤት ከሆነው ጮቄ ተራራ ላይ ከሚገኘው የሙሉ ባህላይ መዝናኛ እናክብር

የጮቄው የዓለም ድንቅ የቱሪዝም መንደር (Best Tourism Village) ተሸላሚ ሆኖ መመረጡን ተከትሎ፤ በምረጫው በመደሰት እና Mulu Ecolodge 'ን በማመስገን፤ እንደአጠቃላይ ስለጮ...
22/12/2022

የጮቄው የዓለም ድንቅ የቱሪዝም መንደር (Best Tourism Village) ተሸላሚ ሆኖ መመረጡን ተከትሎ፤ በምረጫው በመደሰት እና Mulu Ecolodge 'ን በማመስገን፤ እንደአጠቃላይ ስለጮቄ ተራራ እና ተፋስስ ካነበብነው እና ካታዘብነው እንዲኽ ለመጻፍ ወደድን!

በክልላችን ከሚገኙ ብሔራዊ ፖርኮች እና ጥብቅ ሥፍራዎች መካከል፤ አሥረኛ ሆኑ የተመዘገበው የጮቄ የማኅበረሰብ ጥብቅ ሥፍራ 6 ሺህ 24 ሄክታር ስፋት የሚሆነውን፤ 6 ወረዳዎችን እና 22 ቀበሌዎችን እንደሚያዋስን ተገልጾ፤ በክልሉ ምክር ቤት አዋጅ ወጥቶለት የተመዘገበው ሚያዝያ 10/2011 ዓ.ም ነበር። የጮቄ ተራራ ጠቅላላ ስፋት 53,558 ሄክታር መሆኑን ልብ ይሏል። ነገር ግን፤ እስከ ዛሬ ድረስ የተጠቀሰው ሄክታር ከሰው እና ከእንስሳት ንክኪ ነጻ ሆኖ እየተጠበቀ አይደለም። ለጥብቅ ሥፍራው የጽ/ቤት ኃላፊ ከተሾመለት፣ በጀት ከተመደበለት እና አንዳንድ ባለሙያዎች ከተቀጠሩለት ከዓመት በላይ ቢቆጥርም፤ እዚህ ግባ የሚባል መሬት የነካ ሥራ አልተሠራም።

የጮቄ ተራራ በባዮ-ዳይቨርሲቲ የበለጸገ hotspot area ነው። ጮቄ የላይኛው የጥቁር ዓባይ ተፋሰስ የውኃ ማማ ሲሆን ከ60 በላይ ወንዞች እና 270 ምንጮች ከጉያው ይፈልቃል። የጮቄ ተፋሰስ ስድስት የተለያዩ የአግሮ-ኢኮሎጂ ዞኖች ያሉት ሲሆን የተለያዩ ባዮ-ዳይቨርሲቲዎች ያሉት እና የበርካታ ገባር ወንዞች ምንጭ ነው። ጥናቶች እንደሚያሳዩት አብዛኛው ክፍል የተሸፈነው በተራራ እና በገደል ነው። ጮቄ የአብዛኛው የጥቁር ዓባይ ገባር የሆነ የወንዝ ውኃ ምንጭ ነው። የጮቄ ተራራ በራሱ ከ10% በላይ የሚሆነውን የዓባይ ውኃ የሚያዋጣ ሲሆን ሥርዓተ-ምህዳሩ ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለታችኞቹ ተፋሰስ ሀገራት የሚሰጠው ጥቅምም በዋጋ የማይገመት ነው።

በምስራቅ እና በምዕራብ ጎጃም ዞኖች የሚገኘው እና ዘጠኝ ወረዳዎችን የሚዋስነው ጮቄ ተራራ ከ53 ሺህ ሄክታር በላይ ሰፋት ሲኖረው፤ አካባቢው 333 ኪ.ሜ ከአዲስ አበባ፣ ከዞኑ ዋና ከተማ ከደብረ ማርቆስ 38 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ይገኛል። ጮቄ በ10°420′ N ኬክሮስ እና በ372°52′ መካከል ይገኛል። አካባቢው የተለያየ መልክዓ ምድራዊ አቀማመጥ ያለው ሲሆን፤ ከ2800 እስከ 4088 mas ከፍታ፣ አማካይ የሙቀት መጠን ከ0 ዲግሪ ሴንቲ ግሬድ እስከ 30 ዲግሪ ሴንቲ ግሬድ እና ከ200 እስከ 2200 ሚሊ ሜትር ዝናብ መጠን ያገኛል።

ጮቄ የተለያዩ አስደናቂ መልክዓ ምድራዊ አቀማመጦች አሉት። ለጎብኚዎች ዓይንን በጣም የሚስበው አባጅሜ ጫካ ከስናን ወረዳ/ሮብ ገበያ ከተማ በ8 ኪ.ሜ ርቀት ላይ የሚገኝ ጫካ ነው። በጫካው ውስጥ አስታ (Erica arborea) ዋነኛው የእፅዋት ዝርያ ነው። ኮሼሺላ (acanthus sennii)፣ ኔቻቴ (helichrysum citrispinum)፣ ጅብራ (Lobelia rhynchopetalum) እና አምጃ (hypericum revolutum) የእፅዋት ዝርያዎችም ይገኛሉ። እንደ ቡሽ አሳማ፣ ጦጣ፣ ጃካል እና ጅብ ያሉ ብዙ የዱር እንስሳት ይገኙበታል።

በጮቄ ውስጥ 41 የወፍ ዝርያዎች እንደሚገኙ ጥናቶች ይጠቁማሉ። አካባቢው የወፍ ተመልካቾችን ለመሳብ ትልቅ አቅም አለው። በጮቄ ተራራ እና በውስጡ 16 የዱር እንስሳት ዝርያዎች ይገኛሉ። ለምሳሌ፦ ነብር (ፓንቴራ ፓርዱስ)፣ ወርቃማ/የጋራ ጃካል (ካኒስ ኦውሬስ)፣ የጋራ ቡሽ ጀርባ (Tragelaphus scriptus)፣አቢሲኒያ ኮሎቡስ፣ የጋራ ዱይከር፣ ስፖትድድ ጅብ (crocuta)፣ አኑቢስ ባቦን (ፓፒዮ አኑቢስ)፣ ቡሽ አሳማ (ፖታሞኮሮርስስ) እና የመሳሰሉት ይገኛሉ።

ልቅ ግጦሽ እና ወረራ፣ ደን መጨፍጨፍ፣ ሕገ-ወጥ የማኅበረሰብ ሰፈራ፣ ገደብ የለሽ ዘላቂነትን ያላማከለ አጠቃቀም፣ የመንግስት ፖሊሲ ድጋፍ እጥረት፣ የባለድርሻ አካላት ደካማ ትብብር፣ ማኅበረሰቡ ስለ ቱሪዝም ያላቸው ግንዛቤ አናሳ፣ ግልጽ ያልሆነ የጮቄ ወሰን ማስከበር (Demarction) እና መድረሻ አለመታወቅ የጮቄ ተራራ ዋና ተግዳሮቶች ናቸው ።

አንዳንድ ጥናቶች ላይ የጮቄ ተራራ 11 የተለያዩ የቱሪዝም አቅሞች እንዳሉት ተገልጿል። የጮቄ ተፋሰስ እምቅ የቱሪዝም ሀብት ያለው በመሠረታዊ የቱሪዝም መሠረተ ልማት ተቋማት እና አገልግሎቶች መደገፍ ያለበት እና በዘላቂነት ማልማት ያለበት ቦታ ነው። ስለሆነም፤ ጮቄን የቱሪስት መዳረሻ ለማደረግ የተለያዩ የመጠለያ ተቋማትን ማሻሻል እና ማቋቋም፣ የመንገድ እና የመጓጓዣ ስርዓቶችን ማሻሻል፣ የሕዝብ እና ተቋማዊ መገልገያዎች እና አገልግሎቶች (የጤና ጣቢያዎች፣ ኤሌክትሪክ፣ የመጠጥ ውኃ፣ ፍሳሽ፣ የስልክ መስመር፣ የመብራት፣ የስልጠና፣ ባንክ እና ወዘተ) በአካባቢው ውስጥ መሰጠት አስፈላጊ ነው።

በተጨማሪ፤ የቱሪስት መረጃ ማዕከላት፣ የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን፣ የጉብኝት እና የጉዞ መገልገያዎች፣ መመሪያ አገልግሎቶች፣ የመዝናኛ ማዕከሎች፣ የገበያ እና የንግድ ተቋማት፣ የማስታወቂያ ሰሌዳዎች እና ምልክቶች ፣ ካርታዎች እና ሌሎች መገልገያዎች ሊኖሩ ይገባል። በተለያዩ የማስተዋወቂያ መሳሪያዎች እና ሰፋ ያለ መሆን አለበት፣ ለሰፊው ማኅበረሰብ የግንዛቤ ፈጠራ ፕሮግራም ማካሄድ ያስፈልጋል። የጮቄን እምቅ ሃብት ለኢኮቱሪዝም ልማት ለማዋል እና ሥነ ምህዳሩን መልሶ ለማቋቋም ያለውን አቅም መገምገም እና ማስተካከል ያስፈልጋል። የጮቄ ተራራ አካባቢ ማኅበረሰብ እንግዳ ተቀባይ እና ተግባቢ ነው። አካባቢውን የገበኙ ሰዎች "የሺህ ፈገግታ ምድር” ብለው ይጠሩታል።

የጮቄ ተፋሰስ ብዙ እምቅ የቱሪዝም አቅሞችን ያካተተ ሲሆን የእፅዋት፣ የእንስሳት እና የአእዋፍ ዝርያዎች የሚዳሰሱና የማይዳሰሱ የቅርስ ቱሪዝም ግብዓቶች (አባጅሜ ጫካ፣ የአራት መከራከር ሰንሰለታማ ተራራ፣ ሞላሌ ዋሻ፣ ባሕረ-ጊዮርጌስ ሐይቅ፣ ደብረ ወርቅ ማርያም ገዳም፣ ዲማ ገዳም ጊዮርጊስ እና ዋሻ ጊዮርጊስ ፍልፍል ቤተ ክርስቲያን) ተጠቃሽ ሲሆኑ፤ የበላይ ዘለቀ ታሪክ እና ተያያዥ ቱባ ታሪክ፣ ባሕል እና እሴቶችና መጥቀስ ይቻላል። ሆኖም፤ የመሠረት ልማት እና የመንገድ ችግር በቂ ያልሆነ መስተንግዶ፣ ደካማ መሠረተ ልማት፣ በቂ ግንዛቤ አለማግኘት፣ ደካማ የአካባቢ ጥበቃ ሥራ፣ የባለድርሻ አካላት ቅንጅት እና አጋርነት ደካማነት፣ ደካማ እድገት እና የሕዝብ ቁጥር መጨመር ዋና ተግዳሮቶች ናቸው። ጮቄን የቱሪስት መዳረሻ ለማድረግ እነኝኽን ተግዳሮቶች መቅረፍ የመጀመሪያው እርምጃ ነው።

ሌላው፤ ማኅበረሰብ አቀፍ ኢኮቱሪዝም ለጮቄ ተራራ መጠበቅ እና አካባቢው ሕዝብ ኑሮ ማሻሻል አስፈላጊ ነው። በተጨማሪም የአካባቢው ማኅበረሰብ የመኝታ አገልግሎትና የጉብኝት አገልግሎት መስጠት እንዲችል ማድረግ፣ የግብርና ምርቶችን (እንደ ሥጋ፣ የዶሮ እርባታ፣ የወተት፣ ማር፣ የአትክልትና ሌሎች የሰብል ምርቶችን) ማቅረብ፣ የእደ ጥበብ ውጤቶችን በማምረት እና የተለያዩ የባህል ትርኢቶችን እንዲያቀርብ ማድረግ፤ ማኅበረሰቡ ከጮቄ የግጦሽ ጥገኝነት እንዲላቀቅ የተሻሻሉ የበግ፣ የእንስሳት ዝርያዎችን እንዲላማድ ማድረግ፣ አካባቢው ከፍተኛ የባሕርዛፍ እና የቀርክኽ ምርት ያለ በመሆኑ ፋብሪካ መክፈት፣ በጥቃቅን እና አነስተኛ እያደራጁ ለወጣቱ ሥራ መፍጠር፣ በተመሳሳይ በአካባቢው ድንች እና ጥራጥሬ ምርቱ ከፍ ያለ ስለሆነ እሴት እየጨመሩ የሚሸጥበት ሰንሰለት መፍጠር፣ በቦታው ጎብኝዎችን የፈረስ እና የበቅሎ tour guide የሚደርጉ ወጣቶችን ማደራጀት፣ በአካባቢው Lodge and Resort መገንባት፣ ፋብሪካዎችን መገንባት (የሃይላንድ ውኃ፣ የሽቶ) እና መሰል ፋብሪካዎችን፤ በሽቶ ምርት የሚታወቅ አንድ የፈረንሳይ ካምፖኒ በጮቄ ከሚገኘው ከሚባለው Shurb ሽቶ ለማምረት ጥናት ሲያደርግ እንደነበረ ሰምቻለሁ።

በተጨማሪ፤ ላይ ከተጠቀሱት አማራጮች በተጨማሪ ጮቄን Community based ecotourism development method በመጠቀም፤ ማን ምን ያድርግ የሚሉትን መንገዶች ለመነሻ ያኽል እንደሚከተለው እንጠቁማለን።
1. የአካባቢው ማኅበረሰብ፦ የአካባቢውን ሃብት በመጠበቅ እና በመንከባከብ ንቁ ተሳታፊ ንቁ ተሳታፊ እንዲሆን ማድረግ፤ ልቅ ግጦሽ እንዲቀር ማድረግ፣ የ'reforestation ሥራ እንዲሰራ ማድረግ፣ ማኅበረሰቡ የባለቤትነት እና የተቆርቋሪነት ስሜት እንዲሰማው ማድረግ እንዲሁም ለአካባቢው Buffer zone እንዲኖር ለማስቻል ጥግ ያሉ ሰዎችን relocate ማድረግ እና ቦታውን protect ማድረግ።
2. ሚዲያዎች፦ የግልም ይሁን የመንግሥት ሚዲያዎች የፕሮሞሽን እና የአድቨርታይዝመንት ሥራዎች እንዲሠሩ ማድረግ፤
3. የትምህርት ተቋማት፦ በዋናነት የደብረ ማርቆስ፣ የባሕርዳር እና የእንጅባራ ዩንቨርስቲዎች ቦታው ላይ research, ሥልጠና እና ልምድ ልውውጥ፣ የግንዛቤ ፈጠራ ሥራዎች ከቱሪዝም ኢንዱስትሪው ጋር አያይዘው እንዲሠሩ ማድረግ፤

በመጨረሻ፤ መንግሥት፣ የግል ቢዝነስ ኢንትርፕራይዞች እና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት በመተባበር እንዲሠሩ በማድረግ እንዲሁም ጮቄን የቱሪስት መዳረሻ በማድረግ የአካባቢውን ሥነ-ምኅዳር በመጠበቅ የአየር ንብረት ለውጥን መከላከል እና ልማትን እና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን ማምጣት የሚቻል መሆኑን መጠቆም እንወዳለን። ሰላም!

21/12/2022

#እንኳን ደስ ያላችሁ ፤ እንኳን ደስ ያለን!

ጎጃም ጮቄ ተራራ የአለም ድንቅ ቱሪዝም መንደር Best Tourism Village ውድድር አሸናፊ ሆኖ ተመርጧል።

(ሙሉ ኢኮ ሎጅና የማህበረሰብ ተኮር ቱሪዝም) የ2023 የአለም ድንቅ የቱሪዝም መንደር Best Tourism Village ተሸላሚ ሆኖ ተመርጧል።

በውድድሩ ከ150 ሀገራት በላይ ተሳትፈውበታል። ሽልማቱን ከUNWTO በሳውዲ ሀገር በቀጣይ ወር ከUNWTO General Secretary እንቀበላለን። የማህበረሰቡ ተወካዮችም እውቅናውን ከቱሪዝም ሚኒስቴር ጋር በመሆን ይቀበላሉ።

መረጃው የምስራቅ ጎጃም ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ነው፡፡

HOSAENA Holiday at the place of Hosaena
16/04/2022

HOSAENA Holiday at the place of Hosaena

ለክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለበዓለ ሆሳዕና በሰላም አደረሳችሁ
16/04/2022

ለክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለበዓለ ሆሳዕና በሰላም አደረሳችሁ

At  mount chokie
29/03/2022

At mount chokie

12/10/2021
12/10/2021
Years ago at mount chokie
13/09/2021

Years ago at mount chokie

When you go to mulu Eco lodge found at chokie mountain the society will received you with their cultural tradations
03/09/2021

When you go to mulu Eco lodge found at chokie mountain the society will received you with their cultural tradations

ወደ ጮቄ ተራራ ቢመጡ በዚህ ተፈጥሮ ባደለውና ባማራኪው የሙሉ ኢኮ ሎጂ ያማረ የደስታ ጌዜ ያሳልፋሉ
19/07/2021

ወደ ጮቄ ተራራ ቢመጡ በዚህ ተፈጥሮ ባደለውና ባማራኪው የሙሉ ኢኮ ሎጂ ያማረ የደስታ ጌዜ ያሳልፋሉ

የጮቄ ተራራ ቱርፋቶች
19/07/2021

የጮቄ ተራራ ቱርፋቶች

Artists and popular singer   Demessie,Gash Abera molla ,senior journalist Getu Temesgen and others are visiting   Eco Lo...
19/07/2021

Artists and popular singer Demessie,Gash Abera molla ,senior journalist Getu Temesgen and others are visiting Eco Lodge Which is community based sustainable tourism .The lodge is found at dega damote woreda parts of chokie mountain ጠዓሜ kebel .From Adiss Abeba to denbecha drive 350km and denbecha to ጠዓሜ 54km then you will get yourself at this attractive area's and community .The lodge will deliver fully services with its organic and locally preparation by the community .we are inviting all of you to have a very nice time at chokie mountain .

Address

Around Snt George
Bahir Dar

Telephone

+251912692779

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Choke mountain Tour and Travel Agent posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Choke mountain Tour and Travel Agent:

Videos

Share