11/02/2021
የአዳር ጉዞ ወደ አስደናቂው ወንጪ ሐይቅ እና ነጋሽ ሪዞርት
ወንጪ ከአዲስ አበባ ከተማ በስተምዕራብ 160 ኪሎ ሜትር በወሊሶ እና በአምቦ ከተማ መካከል ላይ የሚገኝ ከሺህ አመታት በፊት በተከሰተ እሳተ ገሞራ ፍንዳታ ምክንኛት የተፈጠረ ውብ ሐይቅ ያለበት ቦታ ነው። የወንጪ ሐይቅ በውስጡ ለአሳ ምግብነት የሚጠቅሙ ነገሮች ባለመኖራቸው ብዙ የአሳ ዝርያ የለበትም፣ በውስጡ አሳ አለመኖሩ ደግሞ ሐይቁ በጣም ንፁህ እና ከየትኛውም አይነት የውሃ ጠረን የፀዳ አድርጎታል። የወንጪ ሐይቅ ዙሪያውን ቀልብን በሚስቡ እና በሚማርኩ የተፈጥሮ ሐብቶች የታደለ ቦታ ነው- ለአብነት ያህል ጨዋማ ነጫጭ ድንጋዮች፣ በሰልፈር የቀሉ ረግረጋማ ቦታዎች፣ የሚፍለቀለቁ ትኩስ የታቆሩ ውሃዎች፣ የፈላ የፏፏቴ ውሃ እንዲሁም የተፈጥሮ ጋዝ ያለው የሚፈልቅ የምንጭ ውሃ ይገኝበታል::
በ 90,000 ስኩር ሜትር ቦታ ስፋት ላይ የከተመው ነጋሽ ሪዞርት በኦሮሚያ ክልል በወሊሶ ከተማ ይገኛል:: የነጋሽ ሪዞርት በተፈጥሮ ከታደለው ፍል ውሃ በተጨማሪ አገር በቀል ዛፎችን: አህዋፋትን እና እንስሳትን በውስጡ አቅፎ ይዟል: : በተጨማሪም የሪዞርቱ ሌላኛው መለያው ደግሞ የተለያዩ ብሔር ብሔረሰቦችን የቤት አሰራር ወካይ የሆኑ መኝታ ክፍሎች ከብሔረሰቡ መገልገያ ቁሳቁሶች፣ አልባሳትና ሌሎች የማንነት መገለጫዎቹ ጋር አካቶ የያዘ መሆኑ ነው::
🗓የጉዞ ቀን- የካቲት 6 እና 7 /2013 (February 13 & 14/2021)
🕓 የቆይታ ጊዜ- 2 ቀን / 1 ሌሊት
🛣 የቦታ ርቀት- 160 ኪሜ
🏞 የወንጪ ከፍታ ከባህር ጠለል በላይ- ከፍተኛው 3300 ሜትር (10827 ፊት) ካላ የሚባለው የጉዞ መነሻ ቦታ ሲሆን ዝቅተኛው 2500 ሜትር (8202 ፊት) ሐይቁ የተኛበት ቦታ ነው::
🏞 የጉዞ አስቸጋሪነት- ለጀማሪ በመጠኑ ከበድ ያለ ሊሆን ይችላል:: ሆኖም ልምድ ላለው/ላላት ተጟዥ ቀላል የሚባል አይነት ነው::
💵 የጉዞ ጥቅል ዋጋ- 2000 ብር በሰው
** ለጥንዶች: እንዲሁም በግሩፕ ሆነው ለሚመጡ ሰዎች የ 5% ቅናሽ አድርገናል::
ዋጋው ምን ምን ነገሮችን ያካትታል?
• የደርሶ መልስ ትራንስፖርት ምቾት ባለው ቱሪስት ባስ 🚍
• የወንጪ ሐይቅ መግቢያ ክፍያ (Entrance fee)💴
• አስጎብኝ (Tour Guide)🧑🏾
• የውሃ ላይ መጓጓዣ ታንኳ(canoe)🛶
• ቀለል ያለ ቁርስ (አንድ ጊዜ- ቅዳሜ) 🍩💧
• ጣፋጭ ምሳ ከውሃ ጋር (ሁለት ጊዜ- ቅዳሜ እና እሁድ) 🥗
• እራት ባርቤኪው ከወይን ወይም ውሃ ጋር (አንድ ጊዜ- ቅዳሜ) 🥗
• 🛌ደረጃውን የጠበቀ መኝታ ከቁርስ ጋር በነጋሽ ሪዞርት- ማረፊያ ባለ ደብል(Double Bed) ወይም ባለ ጥንድ አልጋ (Twin Beds) ክፍሎችን በመጋራት ሲሆን: ባለ ነጠላ አልጋ(Single Bed Room) ክፍል ለሚፈልጉ ተጨማሪ ብር 500 ይከፍላሉ::
መገናኛ ቦታ፡ ሜክሲኮ ዲአፍሪክ ሆቴል ጋር
የመገናኛ ሰዓት: ከንጋቱ 12:30
የመኪና መነሻ ሰዓት: ጠዋት 1:00
ለመመዝገብ እንዲሁም ለተጨማሪ መረጃ በሚከተሉት ቁጥሮች ይደውሉልን::
📲 0911691538, 0966724726, 0980494714
ለአዳዲስ መረጃዎች የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ:: በተጨማሪም በኢንስታግራም ገጻችን ይከተሉን::
t.me/happyfeethiking
Instagram